ማሽኑ የተሰራው መልካም ስብዕና ና የሙያ ተሰጦ ባለቤት በሆነው በኢንጅነር ሙላት ባስዝነው ፈንቴ ነው። ኢንጅነር ሙላት ከልጅነት ጀምሮ በቶርኒዩና ማሽነሪ ስራ ለረጅም አመታት እያገለገለ በዚሁ ስራው የተለያዪ ለህዝብ ትራንስፓርት ና ለዓሳ ማስገር አገልግሎት የሚውሉ ጀልባዎችን በራሱ ዲዛይን በማድረግ በመስራት ለገበያ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ ለህዝብና ለመንግስት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን በጣና ና አባይ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ማሽን (በውሃ ላይ የሚሳፈፍ ማሽን) በመስራት ከባህር ዳር ዪንቨርስቲ ጋር ውል ፈጽሞ ስራውንም አጠናቆ አስረክቦል።
ይህንን ማሽን ለመስራት ወደ አሜሪካ ና አውሮፖ ተዘዋውሮ ማሽንኑን ከሚያመርተው ድርጅት በራሱ ወጭ በቂ የሙያ ልምድ ቀስሙል በተግባርም በመተግበር በጥረቱ ውጤታማ ሆኖዋል።
ለአገራችን በማሽነሪ ግዥ ሊያስወጣ የሚችለውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረትና አባይና ጣናን ለመታደግ ማሽኑን በመስራት ከኢትዮጵያ ዓዕምሮዊ ንብረት ጽ/ቤት የእውቅና ሰርተፍኬት አግኝቷል ተብሏል።
የባህር ዳር ዪንቨርስቲ የኢንጂነሪንግ ፋካሊቲ ትኩረት በመስጠት ሙያዊ እገዛ አድርጎለታል።
ሁላችንም የኢንጅነር ሙላት ባሳዝነውን
የሙያ ስኬት እና መልካምነት ለአማራ ወጣቶችም ይሁን ለአገራችን ወጣቶች በማስተላለፍ፣በማሳወቅና በመደገፍ የእርሱን ፈለግ በመከተል ውጤታማ እንሁን።
ጣና እና አባይን በህዝቦች የተባበረ ክንድ ከአደጋ እናድናቸዋለን!!!
ተዋቸው ደርሶ
Manufactured by mulat industrial engineering Plc
ይህ ህዝብ ልዩ ነው ስላችሁ!!!
No comments:
Post a Comment