Thursday, August 13, 2015

የክረምት ዝናብ ዘግይቶ መጀመሩ አሳሳቢ ሆኗል፤ በአፋርና ኢሳ አካባቢዎች ለ5ወራት የዝናብ እጥረት ተከስቷል - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9542#sthash.JrJi1u2x.dpuf

VOA
በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ በእጅጉ ዘግይቶ በመጀመሩ፤ በከብት እርባታ የሚተዳደሩ የአፋርና ኢሳ አካባቢዎች መጎዳታቸውን የማህበረሰቦቹ ተወካዮች ገለጹ።
በድርቁ የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች  የሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካታ እንስሳት መሞታቸውን፤  የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከአፋርና ኢሳ ማህበረሰቦች መሪዎች ካገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
የፌዴራልና የክልል ባለስልጣንት በአንዳንድ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የከብት መኖ ማቅረብ መጀመራቸውን ለመረዳት ተችሏል። ስርጭቱ ግን አሁንም በስፋት በድርቁ የተጠቁ አካባቢዎች ያዳረሰ አይደለም።
  

4835A12F-B64D-49D7-BB4D-886F3E204E6A_w640_r1_s

የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በዘንድሮው ክረምት ባብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት መከሰቱን ሰኞለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህንኑ መነሻ በማድረግም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ኮሚቴ መቋቋሙ ተገልጿል። የዝናቡ እጥረት በሰዎችና በእንስሳት ላይ ያደረሰው ጉዳት ስለመኖሩ መንግሥት እስካሁን ባለው ጊዜ የሰጠው ዝርዝር መግለጫ የለም።
ያሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ያነጋገራቸው የአፋርና የኢሣ ማህበረሰብ መሪዎች ግን ሰዎችና በርካታ ከብቶች መሞታቸውን ገልጸው የክልልና የፌዴራል መንግሥት እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ተማጽነዋል።
  04:00             04:52  

No comments:

Post a Comment