Wednesday, August 12, 2015

የሕወሓት መንግስት ቅንጅትን ለማፍረስ የተባበሩትን አቶ አየለ ጫሚሶን እንደሸንኮራ መጦ ጣላቸው - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45802#sthash.uoNFngpG.dpuf

የሕወሓት መንግስት በሚዲያዎቹ በኩል እንደዘገበው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የፓርቲውን ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶንና የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ አስረስ በትረን ከአመራርና አባልነት ማስወገዱን ገልጿል:: እንደ መንግስት ሚዲያዎች ዘገባ በፓርቲው ስም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ በሚል ደብዳቤ የላኩ ግለሰቦች በህገወጥ ድርጊትና ወንጀል ከፓርቲው የተሰናበቱ መሆናቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶ አሳወቁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ችግራቸውን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንበ መሠረት እንዲፈቱ አሳሰበ። ይህ የምርጫ ቦርድ ተግባር በአንድነት ፓርቲ ላይ የተለመደ አካሄድ ነው ሲሉ ፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ:: የሕወሓት መንግስት ያደራጃቸው የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በፓርቲው ዋና ፀሐፊ፣የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ሳሳሁልህ ከበደ ሰሞኑን ለኢህ አዴግ ሚድያዎች በላከው የውሳኔ ማሳወቂያ ደብዳቤ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች ከፓርቲና ከሥልጣናቸው እንዲወገዱ የተደረገው በፓርቲው ህገ ደንብ መሠረት ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መካከል አንደ ሦስተኛው ስብሰባ እንዲደረግ ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት ስለሚቻል በዚሁ መሠረት ስብሰባው የተካሄደ መሆኑን ያስረዳል። በፓርቲው ውስጥ ህገ ወጥ አሠራሮች የተስፋፉበት፣ውጫዊና ውስጣዊ ወንጀሎች እየተበራከቱ የመጡበት ሁኔታ መኖሩን ፣በህጋዊ ፓርቲ ሽፋን ከፓርቲው አቋም ውጪ መንቀሳቀስ የሚሉና ሌሎች ችግሮች ከታዩ በኋላ ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅና ፓርቲውን ለማዳን ሲባል እርምጃው መወሰዱን ያትታል። የስብሰባው ቃለ ጉባኤና ውሳኔም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መላኩንም ያስረዳል። የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስመልክቶ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ «በፓርቲው ስም የውሳኔ ሃሳብ በሚል የሚያቀርቡት ግለሰቦች ህገወጥ ድርጊትና ወንጀል ፈፅመው በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከአመራርነትና ኃላፊነት የተባረሩ ናቸው» ቢሉም ክርክራቸው ጉንጭ አልፋ ነው የሚሉ በርካታ ናቸው:: አቶ አየለ ጫሚሶ ከሕወሓት መንግስት ጋር የነበራቸው ፍቅር ያለቀ ሲሆን እንደሸንኮራ ተመጠዋል:: እኚህ ፖለቲከኛ የቅንጅትን ትልቅ ትግል ገደል ለመክተት የተባበሩና ለጥቅም ያደሩ በመሆኑ ዛሬ እንደሸንኮራ ተመጠው ወያኔ ባዘጋጃቸው ሰዎች ቢጣሉም የሚቆረቆርላቸውም የለም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amh
chamiso ayelearic/archives/45802#sthash.uoNFngpG.dpuf

No comments:

Post a Comment