Wednesday, August 12, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ተልዕኮ


የአርበኞች ግንቦት 7 ተልዕኮ
ራዕይ

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የተከበረበት፣ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅባራዊ ፍትህ የሚያገኙበት፣ የዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት ሃገር እንዲኖረው ማድረግ ነው።
ተልዕኮ
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ ቀዳሚ ተልዕኮ የመንግስትና የፖለቲካ ስልጣን በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትንና የሃገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበትን ብሄራዊ ሥርአት እንዲገነባ ማገዝ ነው።
መሰረታዊ ዕሴቶችና መርሆዎች

  • የግለሰቦችና የህዝብ መብቶች መከበር የአዲሱ ፖለቶቲካዊ ሥርአት የሚዕዘን ድንጋይ ነው፣
  • የአዲሱ ፖለቲካዊ ስርአት የጀርባ አጥንት በመሆን የአምባገነን መንግስታትንም ሆነ ፓርቲዎችን፣ እንዲሁም ፖለቲከኞችን መረን ያጣ ሥልጣን ለመቆጣጠር፣ ነፃ መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት ምሥረታና መጠናከር አስፈላጊነቱን በማመን፣ ነፃ የፖሊስና የመከላከያ
  • ሃይል፣ ነፃ የምርጫ ቦርድና ነፃ ፕሬስ እንዲመሰረቱና እንዲጠናከሩ መታገል፣
  • የሃይማኖት፣ የዘውግ፣ የባህልና የመልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ልዩነቶች የሚያደምቁን ውበቶቻችን እንጂ፣ የርስ በርስ መጠቃቂያ መሳሪያዎች አለመሆናቸውን በማመን፣ ይህንን ውበት ያላበሱን ልዩነቶቻችንን የሚያከብር በሃገራዊ አርበኛነት ላይ የቆመ ጠንካራ ህብረተሰብ መገንባት፣
  • ዜጎች ከሚጋሩት ህይወት፣ ህልምና ተስፋ እንዲሁም በታሪክ ካዳበሩት የጋራ ትስስር ይልቅ፣ የዘውግ፣ የሃይማኖትና ባህላዊ ልዩነቶቻቸውን ለአጭር ጊዜ የፖለቲካ ጥቅም የሚቆምሩ ፖለቲካዊና ተውፊታዊ ጎታች ሃይሎችን መታገል፣
  • ዜጎች በዘውግ ጀርባቸው፣ በሃይማኖታቸው፣ በቋንቋቸው፣ በባህላቸው፣ በእድሜያቸው፣ በጾታቸው ወይም በመልክአ ምድራዊ ልዩነቶቻቸው ወይም በግላዊ አቅመ-ደካማነታቸው የተነሳ አድልኦ የማይፈጸምባቸውና የዜግነት የእኩልነት መብታቸው የሚከበርበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ማመቻቸት፣
  • ሃገሪቱን ለማገልገል የቆረጡ፣ ታታሪ፣ ብሩህ፣ አርቆ አሳቢና ሆደ-ሰፊ፣ ለዜጎች አርአያ የሚሆኑ መሪዋች እንዲፈጠሩ ማገዝ፣
  • የመልካም አስተዳደር፣ የተጠያቂነትና የግልፅነት መርሆዎች፣ ህዝብን ማዕከል ካደረገ የውሳኔ አሰጣጥ ጋር ተሳስረው በተግባር የሚተረጎሙበትን ሥርአት መመሥረት፣
  • በጥረት የሚገኝ ውጤት የሚከበርበት፣ ሃገርን ማገልገል ድንቅ የሚባልበት፣ ችሎታና ታታሪነት ብቻ የሽልማት መስፈርቶች የሆኑበት፣ ዜጎች በፖለቲካ ትስስራቸውና በዘውግ ማንነታቸው ሳይሆን በአበርክቶአቸው የድካማቸውን ውጤት የሚያገኙበትና የሚወደሱበት ፖለቲካዊ ሥርአት መመሥረት፣
  • ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝባዊ ግንባሮች ጋር ቅንብርና ትብብር በመፍጠር፣ በመሃላቸው ያለውን ውጥረት ማርገብ፣ ብሎም፣ ሁሉን በአካተተ፣ ሰፊ የፖለቲካዊ ስርአት አማካይነት ብሄራዊ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር፣
  • ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የህዝብ ግንባርና እንዲሁም መብትና ጥቅሜ አልተጠበቀም የሚል ቡድን፣ በፖለቲካ ዕምነቱም ሆነ ፕሮግራሙ የተነሳ የማይገለልበትን፣ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሥርአት ማቋቋም ነው።

No comments:

Post a Comment