የወያኔ ብሔራዊ መረጃ የተባለ ጽንፈኛ ቡድን የነጻነት ታጋዮችን ስም በተልያየ መንገድ ለማጥቃት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።በተለይም በዉጭዉ አለም ላይ የሚገኙ ስደተኞችን ቀንደኛ ተጠቂ ለማድረግ የተነሳዉ የብሐራዊ መረጃ ቡድን በትናንትናዉ እለት መጋለጡን የዉስጥ ምንጮች ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ብሎ በደረሰን መረጃ መሰረት ህዝባዊ ወያኔ ሔርነት ትግራይ ብሔራዊ መረጃ ቡድን የነጻነት ታጋዮችን ለማጥቃት ከሚጠቀምባቸዉ መንገዶች ዋነኞቹ።
- ሂዉማን ትራፊኪንግ በመጠቀም የነጻነት ታጋዮችን በሐሰትና በተለያየ መንገድ በዚሁ ዙሪያ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ለአለም አቀፍ ኢንተርፖል መረጃዎችን በመስጠት ማጥቃት ዋነኛዉ ሲሆን
- በዱባይና በቻይና እንዲሁም በተለያየ አለም አቀፍ ሐገራት ለንግድ የሚንቀሳቀሱ ስደተኛ በተለይም ተቃዋሚ ሐይሎችን በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በተለይም ባለ ነግድ ምልክት እቃዎችን በማዘዋወርና በማሻሻጥ እንዲሁም በተላያዩ መንገዶች በመወንጀል መረጃዎችን በተመሳሳይ ለኢንተርፖል በማቅረብ።
- ከአለማቀፍ አሸባሪ ሐይሎች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ለማስባልና መረጃ ሊሆኑ የሚችሉ የሐሰት ምስክሮችን ወይም በተዘዋዋሪ ንክኪዎችን ሊፈጥሮ ከሚችሉ ሐይሎች ጋር በማዛማድ ለመወንጀልና ለማስከሰስ።
- ለንግድና በተለያየ ሁኔታ ከሀገር ሐገር የሚንቀሳቀሱ ስደተኛ ተቃዋሚ ግለሰቦችን በህገ ወጥ የገንዘብ ዝዉዉር (money transit) በማስከሰስ ለሚመለከታቸዉ ሐገራት መረጃዎችን በማቅረብ ማስከሰስ ።
- በተለያየ ሐገር የሚኖሩ ቀንደኛ ተቃዋሚዎችን በተለይም የአርበኞች ግንቦት 7 አባላቶችን በስም ዝርዝር በጠቀሰ መልኩ የኢትዮጵያ ፓርላማ ተብዬ በአሸባሪነት የፈረጀበትን ሰነድ ባያያዘ ሁኔታ ለሚኖሩበት ሐገር የጸረ ሽብርተኝነት አካል ሪፖርት በማድረግ ስደተኞቹ ተላልፈዉ እንዲሰጡት መጠየቅ። ሲሆኑ፡>>>>>>>>
የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ብሐራዊ መረጃ የተባለ ቡድን በአለም አቀፍ ዙሪያ ያደረገዉን ሴራ በተመለከተ በትናንትናዉ እለት 11/08/2015 የአለም አቀፍ የጸረ ሽብር ሐይሎች ክትትል ቡድን እያንዳንዱ የፍሪካ ለሎች ሐገራት በጸረ ሽብር ተሳትፎ ዙሪያ የበረከተዉንና ሊያበረክት የሚገቡ ተሳትፎዎችን በተመለከተ በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ባደረገዉ ዉስጣዊ ስብሰባ ላይ የተገኙ የተለያዩ ሐገራት የጸጥታ ሐይሎች የኢትዮጵያ መንግስት በሰጣቸዉ መረጃ መሰረት ያደረጉት ክትትል በሙሉ ፍሬ አልባ የሆነና ጥቆማዎቹ ያነጣጠሩባቸዉ ግለሰቦች ባጠቃላይ ከምንም ወንጀል የራቁ ነገር ግን የኢትዮያን መንግስት ፖለቲካዊ አካሄድ የሚቃወሙ መሆናቸዉን ገልጸዋል “” ዉስጥ አዋቂ ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ በተለይም የደቡብ አፍሪካዉ የጸረ ሽብር ክትትል ቢሮ ባመረረ መልኩ የኢትዮጵያ መንገስት በስደተኛ ተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገዉ የሐሰት ዉንጀላ ምክንያት ላልተፈለገ ወጪና ኪሳራ ተጋልጠናል በግንባር ድረስ ሄደን የመረመርናቸዉ ስደተኞች እረጅም አመት በሐገራችን የኖሩና የፖለቲካ ጥገኞች ናቸዉ ብሏል።
በዱባይና አካባቢዉ ዙሪያ የጸጥታ ሁኔታ በመከታተል የሚንቀሳቀሰዉ የጸረ ሽብር አካል አስደግፎ የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳተና የተዛባ መረጃ ብዙዉን ጊዜ የሚያነጣጥረዉ በራሱ ዜጎች ላይ ከመሆኑ የተነሳ ከእነርሱ የሚደርሰንን መረጃዎች በተለየ መልኩ ነዉ የምንመለከተዉ አንዳንድ ሐገራት የገዛ ዜጎቻቸዉን ለመጉዳት የሚጠቀሙትን ዉንጀላ ማስተናገዱ በራሱ ሌላ ስራ እየፈጠረ ነዉ። የሚል ማሳሰቢያ ቢጤ ሰጥተዋል። የነጻነት ታጋዮችን በሐሰት በመወንጀል ትግላችን ማደናቀፍ አይቻልም!!!
የነጻነት ታጋዮች
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9522#sthash.xw3ETFQv.dpuf
No comments:
Post a Comment