Wednesday, August 12, 2015

የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9507#sthash.ywoxeBIT.dpuf

የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄያቸው ያቀረቡት እነዚህ አካላት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የያዙበት ሁኔታ አሳሳቢ እና በሀገሪቱን ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚነጥል እንደሆነ ገልጸዋል። በአሜሪካ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል እና የካሊፎርኒያ የሪፕብሊካን የምክር ቤት አባል በሆኑት ዳና-ሮህራባቸር ስም የተፈረመው ይኸው ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብት ላይ የያዘውን አካሄድ በጽኑ መተቸቱን አል-ጀዚራ በሪፖርቱ አትቷል።
የብሪታኒያ ምክር ቤት አባላት ጀርሚ ኮርቢንና ኤሚሊ ቶርቤሪ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አና ጎሜስ፥ ሪቻርድ ሆዊትና ሌሎች ታዋቂ የፖለቲካ አመራሮች ደብዳቤውን በጋራ መጻፋቸውን ታውቋል ። ያሉበት ሁኔታና ቦታ የማይታወቀው አቶ አንዳርጋቸው በቤተሰቦቻቸው እንዳይጎበኙ ተደርጎ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ የሚገኘው የብሪታኒያ ኢምባሲ ተወካዮች እስካሁን ሶስት ጊዜ ብቻ መጎብኘት ችለዋል። የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አቶ አንዳርጋቸው በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙና የህግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች ጥያቄ ቢያቀርቡም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተወአንዳርጋቸው ጽጌሰደ እርምጃ አለመኖሩን አልጀዚራ በዘገባው አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment