Wednesday, August 12, 2015

ከዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ – “ያለነጻነት ፍትሕ የለም”

በኢትዮጵያ አገራችን ፍትሕ ትንሽ ትልቁ ሙስሊም ክርስቲያን ሳይል ጥማቱን ከንግግር አልፎ በየአብያተ ክርስቲያናት ጸሎታቸውን ፣ በየመስጊዶች ሶላታቸውንና ጸሎታቸውን የሚያሳርጉት ስለ ፍትሕ በመጮህ ነው።የጥንቱን ታሪክ እንዳለ ብናቆየው እንኳ ባሳለፍነው ከሬት የመረረ ወያኔያዊ ስርዓት ፍትሕ በእውን ተከስታ ልትታይ ቀርቶ በዳሰሳና በሽታ እንኳ ደብዛዋ ጥፍቶ የ፺ ሚሊዮን ህዝብ የምኞት መዝሙር ሆና ፳፭ አመታትን አስቆጠረች። ዛሬም የፍትሕ ያለህ የሚለው የህዝባችን ጥያቄ ከዳር እስከ ዳር ቀጥሏል።
Ginbot 7
በርካቶች ህግ በማይከበርበት ፍርድ ቤት በወያኔ ተከሰው በወያኔ ተመስክሮባቸው በወያኔ ዳኛች፣ በወያኔ አቃቤ ህጎች፣ በወያኔ የግፍ ሰንሰለት አሳራቸውን የበሉ በዚያውም ያሸለቡ ደብዛቸው የጠፋ ቤቱ ይቁጠራቸው ለማለት ተገደናል። ለአሁኑ ግን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ሰሞኑን የተጠበቀ ምክንያቱም ወያኔ ከሚዘውረው ፍርድ ቤት ፍትህ ስለማይጠበቅ ነገር ግን የኮሚቴውን ንጹህነት የሚያውቅና ኮሚቴውን ነጻ ከማሰናበት ሌላ ላልጠበቀ ህዝብ በጣም አስደንጋጭ ነው። ስለሆነው በንጹሃን የ
ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎች ላይ የተበየነውን ፍርደ ገምድል ብይን ለመቃወም እናም ለተበየነባቸው ጀግኖቻችን ሳይሆን ላንተ ይብላን ወያኔ ለማለት እንወዳለን። ከ፺፯ ዓመተ ምህረት ምርጫ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በኋላ በሃይል ተጨፍልቆ ብልጭ ብልጭ ሲል የከረመው ህዝባዊና ኢትዮጵያዊ ወኔ ድንገት ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ ከዓወሊያ ተቋም ገንፍሎ ምድሪቷን ያጥለቀለቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ስንቃኘው እንደዜጋ አድናቆት ስንቸረው በመብት ትግሉ ህይወት ያስከፈላቸውን አሳሳ፣ገርባ፣ኮፈሌዎችን፣እንዲሁም በፈሪ በትር የተቀጠቀጡትን አካል የጎደለባቸውን፣ ባኑዋር መስኪድ የጥቁር ሽብር ሰለባ የሆኑትን፣ለፍትሐዊ ትግሉ በህዝብ ተወክለው ህዝቡ ለጠየቀው ፫ ጥያቄዎች ከ፯ እስከ ፳፪ አመት ከመድረክ ጀርባ በተዘጋጀው የቀልድ ቲያትር መጋረጃ የሀሰት ፍርድ ለተወሰነባቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ታላቅ ወገናዊ አክብሮት እንሰጣቸዋለን።
ትግሉ የጋራ ነው ድሉም እንደዚሁ፤ እኛ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የምንገኝ የጋራ ግብረ ሃይል በዚህ ሳምንት የሰማነው በባህሪው እውነት ከማያውቀው የወያኔ ፍርድ ቤት የጠበቅነው ነውና ባንደነቅም ሆኖም ግን እንዲህ አይነት በ፺ ሚሊዮን ህዝብ ላይ የተቀለደ ቀልድን በቀላሉ አንመለከተውም፤እንዲሁም ለጀግኖቹ ንጹሀኖች ፈጣሪ ያበርታቸው፣ቤተሰቦቻቸውን አምላክ ያጽናናቸው ስንል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ባጠቃላይ አብሽሩ የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን።
ፍትሕ የተዘነበለችው ባጠቃላይ በኢትዮጵያውያኖች ላይ ነውና ለዚህ ሁሉ አብነቱ የፍትሕ ያለህ የሚል ጩኸታችን የሚቆመው ይህ ጸረ እስላም፣ጸረ ክርስቲያን፣ ጸረ አገር የሆነው ሰይጣናዊ ስርዓት በጸሎትም፣ በሁለገብ ትግልም፣ በተባበረ ህዝባዊ እምቢታም ተመንግሎ ነጻነታችንን ስንጎናጸፍ ብቻ ነው ብለን እናምናለን።ለዚህም በኛ በኩል ሰላም ላጣው ህዝባችን፣ፍትሕ ለጠፋበት ወገናችን፣በኩልነት ለምታኖረን ኢትዮጵያችን፣ ለሀይማኖት ክብራችን ባስገባን ቀዳዳ ሁሉ ገብተን የመጨረሻዋ እስትንፋሳችን እስክትቆም ድረስ አብረን ተባብረን ለመታገል በጋራ እንነሳ እንላለን።
ፈጣሪያችን አገራችንን ይጠብቅልን!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል dcjointtaskforce@gmail.com
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45729#sthash.LVKe81dv.dpuf

No comments:

Post a Comment