ሕወሃት ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ሲያካሂድ የከረመው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር አድርጓል።ሕወሓት በኢትዮጵያ ዋናውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስልጣን የተቆጣጠረው፣በአገሪቱ እየደረሰ ላለው ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ፣ በስም ፌዴራሊዝም የሚቀልደው ሌሎችን ድርጅቶች እንደ አሽከር በማየት የራሱ ታዛዥ በማድረጉ አልፎ አልፎ በኢህአዴግ ውስጥ የጉምጉምታ መነሻ የሆነው ድርጅት ማን ሊቀመንበሩን ይይዛል የሚለው የስልጣን ሽኩቻ በመቀሌና የአዲስ አበባ ቡድን በሚል ውስጥ ውስጡን ከጉባዔው በፊት በይፋ በጉባዔው ሂደት የተስተዋለ ሲሆን የመቀሌው ቡድን አስቀድሞ እንደተዘገበው አባይ ወልዱን የወቅቱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሊቀመንበር ለማድረግ የጀመረው ትግል በበላይነት ተጠናቋል። የክልሉን ፖለቲካ ትኩሳት በቅርበብ የሚከታተለው አምዶም ገ/ስላሴ በተደጋጋሚ ለህብር ሬዲዮ የስልታን ሽኩቻውን አስመልክቶ በሰተው ቃለ ምልልስ ሁለቱም ቡድን በየበኩሉ እስከ ቀበሌ ካድሬ ከጉባዔው በፊት ሲያደራጅ ቆይቷል። አንዱ የአንዱን ቡድን ደጋፊ ለመጣል በልብነትና አልፎ አልፎም በአረና ወገንተኝነት ሲከሱ ቆይተዋል። የአባይ ቡድን ከፌደራለል እነ በረከትን ከብአዴን የያዘ ሲሆን ወ/ሮ አዜብን በሕወሓት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ማስመረጡ ቀድሞም ሲባል እንደነበረው <<የመለስ ራዕይ የመለስ ራዕይ >> የሚለው መዝሙሩን አጠናክሮ የሚወጣ መስሏል።በጉባዔው በአንደኝነት ከአንድ ሺህ ድምጽ በላኢ አግኝተው የተመረጡት ዶ/ር ደብረጽዮን የሳቸው ሳይሆን የአባይ ቡድን ገኖ የሠጣበት ፖሊት ቢሮ ተመርጣል።
ዶ/ር ደብረጽዮን ም/ሊቀመንበር ሆነዋል። ሰውዬው በፌዴራሉ ከፓርቲው ቀጥሎ በግለሰብ ደረጃ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ሲሆን ለስም ከተቀመጡት አቶ ሀይለማርያም በታች ባብዛኛው የሚያሽከረክር የነበረው በአንድ ለአምስት አደረጃጀት እነ አባይ ወልዱ መቀሌ ላይ በጉባዔው የዘረሩት የአዲስ አበባ የሕወሓት ቡድን ነው። አዲሱን የስልጣን ድልድል የሀይለማሪያም የደህነት አማካሪ አለቃ ጸጋዬ በርሄን ጨምሮ እነ አባይ ጸሐዬን ከድርጅቱ የፖለቲካ ስልጣን በ<<ክብር>. አሰናበትኩ ብሏል።
አስቀድሞ በተሳታፊነት እግራቸውን አስገብተው በጉባዔው የድምጽ ስልጣን የተሰጣቸው ከአዲስ አበባው ቡድን ጀርባ የተሰለፉት እነ ስብሃት እና አርከበ መቀሌው ቡድን በአብዛኛው ማንበብ መጻፍ ጭምር የማይችሉ የጉባዔ ተሳታፊዎችን በአንድ ለአምስት ጠርንፎ ያሰበውን አሳክቷል።
አባይ ወልዱን መልሶ የድርጅቱ ሊቀመንበር ያደረገው ሕወሓት ለሕወሓት እና ለድርጅቱ ስራ አስፈጻሚነት ዘጠኙን መርጧል።
1) ኣባይ ወልዱ”ኣባይ ደራ” ሊቀ መንበር 2) ዶክተር ደብረፅየን ገ/ሚካል ምክትል ሊቀመንበር 3) ጌታቸው ኣሰፋ 4) ዶክተር ኣዲስ ኣለም ባሌማ 5) ፈትለወርቅ ገ/ዝሄር(ሞንጀሪኖ) 6) ኣለም ገብረዋህድ 7) በየነ መክሩ 8) ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም
9) ኣዜብ መስፍን ኣባላት ሁነው ተመረጡ።
ሕወሓት ከቀደሙ አመራሮችና አባላት መካከል የፖሊት ቢሮ አባላት መካከል አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አባዲ ዘሞ፣ አቶ ቴድሮስ ሐጎስና አቶ ፀጋይ በረኼ በመተካካት ሸኝቷል፡፡ ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ፣ አቶ ተወልደ ብርሃን በርኼና አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በፈቃዳቸው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለቀዋል፡፡ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት 50 አባላት ታጭተው 45 አባላት የተመረጡ ሲሆን፣ የአቶ ዓባይ ወልዱ ባለቤት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ክንደያ ገብረ ሕይወት ሳይመረጡ ከቀሩት አምስት አባላት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በተካሄደው 11ኛው የሕወሓት ጉባዔ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ከተመረጡት ውስጥ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ሳይቀጥሉ ቀርተዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር አዳዲስ አባላት ሆነው ገብተዋል፡፡
በጉባዔው አስቀድሞ በተሳታፊ ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ባለድምጽ ከሆኑት በመተካካት ቀድሞ ተሸኝተው ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ ከዚህ ቀደም አቶ መለስ እሳቸውን ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ አሰኝተው ሚስታቸውን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ሲያስመርጡ <<ሕወሓት>> ቀሚስ ለብሷል ድርጅቱን ቀሚሱን ማስወለቅ አለብን የሚል የውስጥ የፖለቲካ አግቦ በየደረሱበት ሲያንጸባርቁ ይሄው ለአደባባይ መብቃቱ ይታወሳል። አቶ ስብሃት በሕወሓት የተንኮል ሴራ በግንባር ቀደምትነት ቀያሽና አስፈጻሚነት ተደጋግመው የሚጠቀሱ ሲሆን የመቀሌው ቡድን ወ/ሮ አዜብን ጭምር ይዞ የጠሉትን የአባይ ቡድን ዛሬም በቀሚስ ለባሽነት ይክሰሱት አይታወቅም። የአዲስ አበባው ቡድን <<ትግራይ አለማችም>> <<ትግራይ መጭ ተጠቀመች ለእድገት እንቅፋቱ ያልተማረውና ሌባው የአባይ ብድን ነው የሚል ቅስቀሳው በጉባዔው ላይ በተወሰነ ደረጃ መንጸባረቁን የሚናገሩ ወገኖች አባይ ወልዱ አንድ ለአምስት አስቀድሞ ከተነገረው ውጭ አልሰማም በማለት ተልዕኮውን የተወታ መስሏል።የሕወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ አገሪቱ ከዚህ አመራር ተጨማሪ አደጋ እንጂ ለውጥ እንደማይመጣ አመላካች ሲሆን አቶ ሀይለማሪአምን በአሻንጉሊትነት ለማስቀጠል የወሰነው ሕወሃት የመቀሌው ቡድን ስኬት ሀሳቡን ያስለውጠዋል በቀጣዩ ወር የሚታይ ይሆናል።
በአዲሱ ምርጫ መሰረት የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት
- ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 2. ወ/ሮ አዜብ መስፍን 3. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር(ሞንጆሪኖ) 4. አቶ ጌታቸው አሰፋ አቶ አባይ ወልዱ(የመቀሌው ቡድነን) መሪና ዶ/ር ደብረጽዮን የአዲስ አበባው ቢድን መሪ 5. አቶ አባይ ነብሶ 6. ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም 7. ወ/ሮ አረጋሽ በየነ 8. ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ 9. አቶ በየነ ምክሩ 10. አቶ ኪሮስ ቢተው 11. ዶ/ር አብርሃም ተከስተ 12. ወ/ሮ ያለም ፀጋይ 13. ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም 14. አቶ ሀዱሽ ዘነበ 15. አቶ ተወልደብርሃን ተስፋዓለም 16. አቶ ሚኪኤለ አብርሃ 17. አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን 18. አቶ ጎይትኦም ይብራህ 19. አቶ ጎቦዛይ ወ/አረጋይ 20. አቶ አባይ ወልዱ 21. ዶ/ር ገ/ህይወት ገ/እግዚአብሄር 22. አቶ ተስፋአለም ይሕደጐ 23. አቶ ሀጐስ ጎደፋይ 24. አቶ ዓለም ገ/ዋህድ 25. አቶ እያሱ ተስፋይ 26. አቶ ሃይለ አስፍሃ 27. አቶ አፅብሃ አረጋዊ 28. አቶ ብርሃነ ፅጋብ 29. ወ/ሮ ሙሉ ካሕሳይ 30. አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም 31. አቶ ዳንኤል አሰፋ 32. አቶ ጌታቸው ረዳ 33. አቶ ሃፍቱ ሀዱሽ 34. አቶ ገ/መስቀል ታረቀ 35. አ/ሮ ዘነበች ፍስሃ 36. አቶ ኢሳያስ ገ/ጊዮርጊስ 37. ወ/ሮ ኪሮስ ሃጐስ 38. አቶ ሽሻይ መረሳ 39. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ 40. አቶ ኢሳያስ ታደሰ 41. አቶ ነጋ በርሀ 42. አቶ ማሙ ገ/እግዚአብሄር 43. አቶ ተኽላይ ገ/መድህን 44. ወ/ሮ ቅድሳን ነጋ 45. አቶ ይትባረክ አመሃ
ይህ በእንዲህ እንዳለ አስቀድሞ በህብር ሬዲዮ ህወሓት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዘገብንበት ወቅት የህወሓት ታዣዥ የሆኑት የብአዴንና የኦህደዴድና የዸህዴግ አመራሮችን ሁለቱም ቡድኖች የየራሳቸውን ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲሚክሩ ተስተውሏል። ህወሓት በ1993 ለሁለት የተከፈለ ሲሆን የአቶ መለስ ቡድን ከባድመ መልስ ሊዘምትበት ተነሳውን ቡድን አንጃ የሚል ስም ለጥፎ ማባረሩ የሚታወስ ሲሆን ከተባረሩት ውስጥ አቶ አባይ ጸሐዬ ይቅርታ ጠይቀው ሲመለሱ አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ ተባረው የቀሩ እንደ አቶ ስዬ በሙስና ታስረው የወቱ ነበሩ።
የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ህወሓት ተከፍሎ የነበረ ሲሆን ጠላቶቻችን ብሎ የፈረጀው ሌላው የኢትዮጵአ ሕዝብ ስልታን ሊያገኝ ይችላል በሚል ጉዳዩን በሽምግልና ፈቶ አብሮ በክልልና በፌዴራል ዋና ዋናውን ስልታን ተቆጣጥሮ የቆው ሀይል ለዘንድሮውም ክፍፍል ተመሳሳይ <<ሽምግልና>> ሊአካሂድ ይችል ይሆናል። የቀሩት የይስሙላ ስልጣን የሚይዙ የሌሎች ድርጅት መሪዎች እንደተለመደው አሸናፊውን ቁጭ ብለው መጠበቃቸው አንዳንዶችን ማስገረሙን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩበ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።
No comments:
Post a Comment