Friday, December 29, 2017

አገራችንን ከተደቀነባት አደጋ መታደግ የሚቻለው የሥርዓት ለውጥ በማምጣት ብቻ ነው። (የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ)

December 29, 2017
የአገራችንን ሉአላዊነት እና የህዝባችንን አንድነት ድርና ማግ ሆኖ አቆራኝቶ ለዘመናት ያቆዩትን እሴቶች ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ህወሃት እንደ ድርጅት መሪዎቹም አንደ ቡድን ልዩ ጥቅም እናገኛለን በሚል የፖለቲካ ስሌት ላለፉት 27 አመታት ረጅም ርቀት ተጉዘዋል። በዚህም የተነሳ አብዛኞቹ አመራሮች እና ለአመራሩ ቀረቤታ ያላቸው ካድሬዎች እስከነ ዘመዶቻቸው የአገሪቱን ፖለቲካ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውንም በበላይነት ለመቆጣጠር ዕድል አግኝተዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያቤት ውስጥ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚንስትር እና በተለያዩ አገሮች የአገራቸው አምባሳደር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የኖሩት ሚስተር ሄርማን ኮሄን ሰሞኑን ለሚዲያ በሰጡት ምስክርነት ይህንን ሃቅ በይፋ በማጋለጥ የህወሃት የበላይነት የፈጠረው ችግር የበደሉ ገፈት ቀማሽ ከሆነው ህዝችባን አልፎ በምዕራባውያን ወዳጆቹ ዘንድም እንደሚታወቅ አረጋግጥዋል።

Thursday, December 28, 2017

Prof Berhanu Nega says, "Brave and Kinder Heart needed to defeat TPLF"

መአዛ ብሩና አቶ አብዱ የኢሃዲግን ፖሊሲዎች ክፉኛ አብጠለጠሉት || እስካሁንም ያልተባላነው ሕዝቡ የመቻቻል ባህል ...

Do not feed the TPLF Killer beast_Amharic 2

የአገራችንን ትንሳኤ ዕውን ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄ የነደፈውን ሁሉን አሳታፊ የሽግግር መንግስት መመስረት ብቻ ነው(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

December 28, 2017
የኢትዮጲያን ፖለቲካ በቅርብም ሆነ በሩቅ ለሚከታተል አንድ ዕውነት ፍንትው ብሎ እንደሚታየው ግልጽ ነው። ለ27ዓመታት አገራችንን በጨለማ ጉዞ ይመሯት የነበሩት በትግራይ ስም የተደራጁት ጥቂት አፋኝ ቡድኖች የስልጣን ዕድሜአቸው መገባደጃው አፋፍ ላይ መድረሱን ነው።
 ኢትዮጲያዊ ውስጥ በአሁን ሰዓት በርግጥ መንግስትና ህግ አለ ወይ ሊያስብል በሚችል ደረጃ የሕዝባችን የፖለቲካውም ሆነ የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ ህይወቱ እጅግ አደገኛና በማንኛውም ጊዜ ወደ ስርዓተ አልበኝነት ሊቀየር የሚችልበት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕዝባዊ ዕምቢተኝነቱ፣ በየቦታው በህወሃት/ወያኔ ጠንሳሽነት የሚለኮሰው የብሄር ግጭት፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ከቀዬው መፈናቀል፣ ጣሪያ የነካው የኑሮ ውድነት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላሰለሰ ተቃውሞና የዩኒቨርሲቲዎቹ መዘጋት፣ የአንደኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች የሚያሳዩት ሰላማዊ ሰልፍ፣ በመከላከያውና በደህንነቱ መሃል እየሰፋ የመጣው የስልጣን ሽኩቻና የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች በግልጽ የሚያብቁት ሕወሃት ይህንን ህዝባዊ ማዕበል እንደ ቀድሞው በማስፈራራትም ሆነ በአስመሳይ የመግለጫ ጋጋታዎች ማለፍ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ነው። ይህ የህዝብ ማዕበል ግራና ቀኝ ክፉኛ እያላጋውና ጥልቅ ተሃድሶ ብሎ የቆፈረውም ጉድጓድ ራሱን መልሶ እየቀበረው ነው።  ከዚህ ሁሉ ይበልጥ ግን አገዛዙ ምን ያህል እንደተሽመደመደና የሞት ቀነ ቀጠሮውን ቆጭ ብሎ እንደሚጠብቅ ግዑዝ አካል ያስመሰለው ራሱ መርጦና አስመርጦ ያስቀመጣቸው የፓርላማ አባላት ለረዥም ዘመን ይጫወቱ የነበረውን የአጨብጫቢነትና የሁሉን አጽዳቂነት ሚና አልፈው ዛሬ ጥያቄ ማቅረብና የአገዛዙን ፈላጭ ቆራጭ የህወሃት ሹመኞች ማፋጠጥ መጀመራቸው ነው።  ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ ደግሞ ፓርላማ እንደማይገቡ ሲያስታውቁና አይናችን እያየ ፓርላማው ሲፈርስ ያኔ የህወሃት/ወያኔ አንድ እግር በርግጥም ወደ መቃብሩ መግባቱን ያለጥርጥር አሳይቶናል። የኢሕአዴግ እንቅልፍ የዛፍ ላይ እንቅልፍ መሆኑ ቀርቶ አሁን ከዛፉ ላይ ተፈጥፍጦ ወድቋል። በዚህ ኢሕአዴግ በተባለው ድርጅት ሆድና ጀርባ ላይ ለአመታት ተመቻችቶ ተኝቶ የነበረው ሕወሃት አሁንም ድረስ ከዕንቅልፉ የነቃ አይመስልም። በሙት መንፈስ የሚንከላወስ አደገኛ ዞምቢ ሆኗል። በጊዜ ካልታገተ የሀገር መፍረስና የፍጹም ስርዓተ አልበኝነት መንገስ የነገው ዕጣ ፈንታችን ሊሆን ይችላል።

የአገራችንን ትንሳኤ ዕውን ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄ የነደፈውን ሁሉን አሳታፊ የሽግግር መንግስት መመስረት ብቻ ነው። (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የኢትዮጲያን ፖለቲካ በቅርብም ሆነ በሩቅ ለሚከታተል አንድ ዕውነት ፍንትው ብሎ እንደሚታየው ግልጽ ነው። ለ27ዓመታት አገራችንን በጨለማ ጉዞ ይመሯት የነበሩት በትግራይ ስም የተደራጁት ጥቂት አፋኝ ቡድኖች የስልጣን ዕድሜአቸው መገባደጃው አፋፍ ላይ መድረሱን ነው። ኢትዮጲያዊ ውስጥ በአሁን ሰዓት በርግጥ መንግስትና ህግ አለ ወይ ሊያስብል በሚችል ደረጃ የሕዝባችን የፖለቲካውም ሆነ የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ ህይወቱ እጅግ አደገኛና በማንኛውም ጊዜ ወደ ስርዓተ አልበኝነት ሊቀየር የሚችልበት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕዝባዊ ዕምቢተኝነቱ፣ በየቦታው በህወሃት/ወያኔ ጠንሳሽነት የሚለኮሰው የብሄር ግጭት፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ከቀዬው መፈናቀል፣ ጣሪያ የነካው የኑሮ ውድነት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላሰለሰ ተቃውሞና የዩኒቨርሲቲዎቹ መዘጋት፣ የአንደኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች የሚያሳዩት ሰላማዊ ሰልፍ፣ በመከላከያውና በደህንነቱ መሃል እየሰፋ የመጣው የስልጣን ሽኩቻና የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች በግልጽ የሚያብቁት ሕወሃት ይህንን ህዝባዊ ማዕበል እንደ ቀድሞው በማስፈራራትም ሆነ በአስመሳይ የመግለጫ ጋጋታዎች ማለፍ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ነው። ይህ የህዝብ ማዕበል ግራና ቀኝ ክፉኛ እያላጋውና ጥልቅ ተሃድሶ ብሎ የቆፈረውም ጉድጓድ ራሱን መልሶ እየቀበረው ነው። ከዚህ ሁሉ ይበልጥ ግን አገዛዙ ምን ያህል እንደተሽመደመደና የሞት ቀነ ቀጠሮውን ቆጭ ብሎ እንደሚጠብቅ ግዑዝ አካል ያስመሰለው ራሱ መርጦና አስመርጦ ያስቀመጣቸው የፓርላማ አባላት ለረዥም ዘመን ይጫወቱ የነበረውን የአጨብጫቢነትና የሁሉን አጽዳቂነት ሚና አልፈው ዛሬ ጥያቄ ማቅረብና የአገዛዙን ፈላጭ ቆራጭ የህወሃት ሹመኞች ማፋጠጥ መጀመራቸው ነው። ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ ደግሞ ፓርላማ እንደማይገቡ ሲያስታውቁና አይናችን እያየ ፓርላማው ሲፈርስ ያኔ የህወሃት/ወያኔ አንድ እግር በርግጥም ወደ መቃብሩ መግባቱን ያለጥርጥር አሳይቶናል። የኢሕአዴግ እንቅልፍ የዛፍ ላይ እንቅልፍ መሆኑ ቀርቶ አሁን ከዛፉ ላይ ተፈጥፍጦ ወድቋል። በዚህ ኢሕአዴግ በተባለው ድርጅት ሆድና ጀርባ ላይ ለአመታት ተመቻችቶ ተኝቶ የነበረው ሕወሃት አሁንም ድረስ ከዕንቅልፉ የነቃ አይመስልም። በሙት መንፈስ የሚንከላወስ አደገኛ ዞምቢ ሆኗል። በጊዜ ካልታገተ የሀገር መፍረስና የፍጹም ስርዓተ አልበኝነት መንገስ የነገው ዕጣ ፈንታችን ሊሆን ይችላል።
አምባገነን መንግስታት የህዝባቸውን ፍትሃዊ ጥያቄ መመለስ ሲያቆሙ ሊከሰት የሚችለውን መጨረሻ የሌለው ስርዓተ አልበኝነትና እንስሳዊ ኑሮ ከቅርባችን ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ የመንና ሊቢያ መማር ትልቅ አዋቂነት ነው። ከነኚህ አሳዛኝ ሀገራት ትምህርት ሊወስድ የሚያስችል አቅምም ሆነ ፍላጎት የሌለው አንድ ሀይል ቢኖር የደናቁርት ስብስብ የሆነው ሕወሃት ብቻ ነው።ኢትዮጲያ በርግጥም መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት።ይህ ሁኔታ ላገራችን ኢትዮጲያ ትልቅ ፈተና ቢሆንም በአግባቡና በስርዓቱ ከተያዘ ግን ትልቅ ታሪካዊ ዕድል የመሆንም ተስፋ አለው።
በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ መካከል የተፈጠረው ልዩነትም ይሁን በፓርላማ አባላቱ ላይ የሚታየው ለህወሃት ጥቅምና ስልጣን አናገለግልም የሚለው ደፋር ውሳኔ ጊዜውና ህዝቡ የሚጠይቀው አበረታች እርምጃ ቢሆንም መዳረሻው ግን አይደለም። ለውጥ ፈላጊ የሆኑ የአገዛዙ አካላት አሁንም በድፍረት ከህዝባቸው ጋር ዕምቢ ለወያኔ/፣ ዕምቢ ለዘረኝነትና ላንድ ብሄር የበላይነት በሚለው አቋማቸው እስከመጨረሻው በጽናት ይገፉበት ዘንድ አደራ እንላለን።
እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል አህያዊ ፍልስፍና የሞት ሞታቸውን ለሚፍገመገሙ የህወሃት/ወያኔ ባለስልጣናት ይህ የህዝብ ምሬትና ወረዱልን የሚለው ድምጽ እያየለ በመጣ ቁጥርና ስልጣነ መንበራቸው መነቃነቅ ሲጀምር ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አንዳንድ ፍንጮችን አይተናል። የብሄር ግጭቶችን በመለኮስ የርስ በርስ ፍጅቶችን፣ የህዝብ መፈናቀሎችን፣ ህጻን ሽማግሌ፣ ወንድ ሴት ሳይል ንጹሃን ዜጎችን ባደባባይ መረሸን፣ የተለመደ እርኩሳዊ ባህሪያቸዉ እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል። የኛ ሃላፊነት መሆን ያለበት ደግሞ ይህንን ወያኔ ለ27 አመታት ካጠረልን ክልላዊ ቅዠትና ወሰናዊ አስተሳሰብ አልፈን እንደ አንድ ሀገር ልጆች መተያየትና ችግሮቻችንን በትዕግስት፣ በመቻቻልና በፍጹም ቅንነት የመፍታት ፍላጎትና ችሎታን ማዳበሩ ላይ ነው። የኦሮሞ ኢትዮጲያ፣ ወይም የወላይታ ኢትዮጲያ፣ የአማራ ኢትዮጲያ ወይንም የሶማሌ ኢትዮጲያ፣ የዚህ ወይንም የዚያ ኢትዮጲያ የሚባል ነገር የለም። የሁለችንም እናት፣ የሁላችንም ቤት የሆነች አንድ ኢትዮጲያ ብቻ ናት ያለችን። በአጥፍቶ መጥፋት ዕብደት የተለከፈው ሕወሃት/ወያኔ ደግሞ እኔ ከሌለሁ እናንተም ኢትዮጲያም አትኖሩም በሚል የደንቆሮ ዕብሪት ይቺን አንድ የጋራ ቤታችንን ሊያወድማት ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህንን ዕብደቱን አስቁመን አገራችንን ማዳንና ህወሃትንም ወደሚገባው የፍትህ ሆስፒታል ወስደን ማሳከም ጊዜው የሚጠብቅብን ታሪካዊ ሃላፊነት ሆኗል። በምንም አይነት መንገድ በኢትዮጲያ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ቁማር አንጫወትም። ለጊዜያዊ ጥቅምና ስልጣን ሲሉ ከወያኔ ጋር ቁማሩን ሊጫወቱ የሚፈልጉትን ሃይሎችንም ተው፣ አያዋጣም ልንላቸው ግድ ይላል።
የኢትዮጲያ ሕዝብ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፣ እያደረገም ነው። አሁን ከፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ ከሀገር ወዳድ ልሂቃን ብዙ ይጠብቃል። በራሳቸው ተነሳሽነት በከባድ መሳሪያ ከታገዘ ነፍሰ በላ የአጋዚ ጦር ጋር ባዶ እጃቸውን ሲፋለሙ የወደቁት የኦምቦ፣ የባህርዳርና የጨለንቆ ህጻናት ደም ትግላችንን አደራ እያለ ከመቃብር ባሻገር ይጠራናል። ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ እንዳይቀር የወደቁለትን የነጻነትና የዲሞክራሲ አላማ ከግብ ማድረስ የሁላችንም ሃላፊነት ነው። በለውጥ ፈላጊ ኃይሎች መካከል ያለውን የተለያየ ያስተሳሰብ ልዩነትና ከንቱ የጎንዮሽ መጓተት ወደጎን አድርጎ ይህን አስከፊ ስርዓት ማስወገድ ቅድሚያ ልንሰጠው ይገባል። ሁሉም ተቃዋሚ ሀይል በተቀናጀ መልኩ በሕወሃት/ወያኔ ላይ በህብረት ይዘምት ዘንድ ንቅናቄአችን ጥሪውን ያቀባርል። የንቅናቄአችን የመጨረሻ አላማ ምንድነው ብላችሁ ለምትጠይቁ መልሳችን አንድና አንድ ብቻ ነው። የሕወሃትን አገዛዝ ከስር መሰረቱ ገርስሶ አንድነቷ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ላይ የተገነባች አዲስ ኢትዮጲያን ማየት ብቻ ነው! ይህን ዕውን ማድረግ ደግሞ የምርጫ ወይንም የልሂቃን ቅንጦት ሳይሆን እንደሀገር የመኖርና ያለመኖር ሕልዉናችንን የሚወስን ብቸኛ አማራጭ ስለሆነ ብቻ ነው።የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄ ለዚህ አላማ መሳካት ግብዓት ይሆን ዘንድ የሽግግር መንግስት ሰነድ አዘጋጅቷል።
ይህንን የህወሃት/ ወያኔን ሁለንተናዊ ድክመትና አገር የማስተዳደር አቅም ማጣት ተከትሎም ሀገራችን ኢትዮጲያ ወደ አልተፈለገ የርስ በርስ ግጭት ከማምራቷ በፊት መፍትሄ መፈለግ አለበት እያሉ የሚጎተጉቱ ድምጾችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሰማን ነው። በተለይም ደግሞ የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ መንግስት ህወሃት/ወያኔ ከሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥና መደራደር አለበት ሲሉ ተደምጠዋል። በድህረ ደርግ ዘመን ህወሃቶችን ለስልጣን ያበቁትና በኢትዮጲያ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የነበሩት አሜሪካዊው ዲፕሎማት ሚስተር ኸርማን ኮኸንም ከሰሞኑ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ስለወያኔ ያላቸውን ስጋት ሲገልጹ ከርመዋል። ዲፕሎማቱ ሲናገሩም በጥቂት ዘረኞች መዳፍ ውስጥ የወደቀው የኢትዮጲያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የፈጠረው ሁለንተናዊ ቀውስ ባስቸኳይ የፖለቲካ መፍትሄ ካልተገኝለት ያገሪቱ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ጠንከር ባሉ የማስጠንቀቂያ ቃላቶች ገልጸዋል። ባጭሩ አነጋገር ምዕራባዊያኑ በአንድ ወቅት ይተማመኑበት የነበረው የ11 % የኢኮኒሚ ዕድገትም ሆነ አሸባሪዎችን መዋጋት የሚለው የህወሃት ፕሮፓጋንዳ የተደማጭነት ዋጋውን አጥቷል። ለ27 ዓመታት ምለው የተገዘቱበት ዲሞክራሲን የማስፈንም ሆነ ድህነትን የመቅረፍ ወሬ ምዕራባዊያንን ከማጭበርበርና ከማሳሳት ያለፈ ምንም አይነት ፋይዳ እንደሌለው ጌቶቻቸው የተገነዘቡት ጉዳይ ሆኗል። ለዚህም ነው በቅርቡ እንደአማራጭ የቀረበውን የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄን የሽግግር መንግስት ፍኖተ መንገድ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ዶክተር ዲማ ነገዎንና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአውሮፓ ፓርላማ የጋበዛቸውና የሽግግር መንግስት ራዕያቸውን እንዲያስረዱ የጋበዟቸው። ለዚህም ነው የአሜሪካን መንግስትም ይሁን ዕዉቅ ዲፕሎማቷ ሁሉን አቀፍ ስለሆነው የሽግግር መንግስትና ድርድር በየመግለጫዎቻቸው ለያሳስቡ የተገደዱት።
ንቅናቄአችን አርበኞች ግንቦት 7 ባሁን ሰዓት በመንደርና በዘር ተሰባስበው ራሳቸውን ህወሃት በማለት አገራችንን ወደማትወጣው አዘቅት እየወሰዷት ባሉት የፋሺስት ጥርቅሞች ላይ ክንዳችንን አስተባብረን እንረባረብባቸው የሚለው። እነኚህ ወሮበሎች ሀገር መምራት አለመቻላቸውን ብቻ ሳይሆን በነሱ ድክመት እየፈራረሱ ያሉ የተለያዩ መንግስታዊ መዋቅሮች ባሉበት በአሁን ሰዓት የተቃዋሚ ሃይሎች በሙሉ ሀገራችን ኢትዮጲያና ህዝባችን ከተጋረጠባቸው የስርዓተ አልበኝነትና የርስ በርስ የመጠፋፋት ዕልቂት አፋፍ የማዳን ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብሎ ያምናል። ለሀገርም ሆነ ለህዝብ ደንታ ቢስ የሆነ አገዛዝ የኢትዮጲያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወደጨለማ በሚያመራበት ጊዜ ዝም ብለን ቆመን ማየት የታሪክ ተወቃሾች ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የአገዛዙ ተቃዋሚ ነኝ የሚል ሃይል የሚስማማበትን የዲሞክራሲና የፍትህ ስርዓት የመገንባት ተስፋውንም ፍጹም ስለሚያጨልመውም ጭምር ነው። ሀገርና ህዝብ ከሌለ ማናቸውን አይነት የፖለቲካ ስርዓት የመገንባት ህልም ከንቱ ቅዠት፣ ባዶ ተስፋ ብቻ ሆኖ ይቀራልና ። መንግስትና ህግ በሌለበት ሁኔታ ራሳችንን እንደመንግስት ቆጥረን፣ አስፈላጊውን ሃላፊነት በትከሻችን ላይ አስቀምጠን፣ በሀገራችንና በህዝባችን ስም መደረግ ያለበትን ሁሉ እናደርግ ዘንድ አደራ እንላለን።
ይህን አለም አቀፍ ትኩረት የሳበውንና የመጨረሻ መፍትሄ ተብሎ የተወሰደውን የሽግግር መንግስት አማራጭ መንገድ ሁሉም ተቃዋሚ ሀይሎች ትኩረት እንዲሰጡትና እንዲደግፉት ንቅናቄአችን ያሳስባል። ከዚህ መፍትሄ በመለስ ያሉት አማራጮች በሙሉ ከዚህ በፊት ባንድም ሆነ በሌላ የተሞከሩና ያልሰሩ መሆናቸውን እዚህ ላይ መተንተኑ ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብናል። የኢትዮጲያ ህዝብ እየጠየቀ ያለው የስርዓት ለውጥ መሆኑን ከግምት አስገብቶ በከፍተኛ ጥንቃቄና አርቆ አስተዋይነት የተዘጋጀው ይህ የሽግግር መንግስት ሰነድ የለውጥ ፈላጊ የሆኑ ያገዛዙ አካላትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ የሚያተርፍበትና ሀገራችንና ህዝባችን ካንዣበበባቸው የርስ በርስ ግጭት የሚያድናቸው ሰነድ መሆኑን ስንገልጽ በሙሉ መተማመንና የህዝባችንን ሙሉ ትብብር ከግምት አስገብተን ነው።
በአሁን ሰዓት ከወያኔ/ህወሃት ጨካኝ አገዛዝ ጋር እየተፋለመ ያለው ህዝባችን ከዚህ የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄ ካዘጋጀውና በቅርቡ በተለያዩ ያገራችን ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለውይይት የሚቀርበውን የሽግግር መንግስት ፍኖተ መንገድ ከልብ ተቀብሎ በንቃት እንዲወያይበት፣ እንዲከራከርበትና አዳዲስ ሃሳቦችን እያመነጨ ይህንን ሰነድ በማዳበሩና በማጠናከሩ ረገድ የራሱን ሚና ይጫወት ዘንድ አደራ እንላለን። እኛ የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄ አካላት ለዚህ የሞት ሽረት የነጻነት ትግል የሚገፋፋን ፊት ለፊታችን ባሉት ጨለምተኞቹና ጸረ-አንድነት በሆኑት ሕወሃቶችና ጉጅሌዎቻቸው ላይ ያለን ምሬትና ጥላቻ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ለሀገራችንና ለሕዝባችን ያለን ጥልቅ ፍቅርና የህዝባዊነት ስሜት ነው። ይህን ፍቅርና ህዝባዊነት የሚያረጋግጥልን ደግሞ ብዙ አገር ወዳድና ህብረ ብሄራዊ የሆኑ ምሁራን በብዙ ድካምና ጭንቀት ያዘጋጁትን ሁሉን አሳታፊ የሆነውን የሽግግር መንግስት ፍኖተ መንገድ ሰነድ ስናጤነውና ስንረዳው ብቻ ነው። ስለሆነም ባገር ውስጥም ሆነ ካገር ውጭ ያላችሁ ኢትዮጲያዊያን በዚህ የሽግግር መንግስት ሰነድ ላይ ውይይት እንድታደርጉበትና ወደተግባር በመቀየር ሂደቱም ውስጥ በገንዘብ፣ በሃሳብ፣ በደምና በጸሎት ከኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄ ጎን እንድትሰለፉ አርበኞች ግንቦት 7 በትህትና ይጠይቃል።

Monday, December 25, 2017

ESAT Daily News Amsterdam December 25,2017

Tamagne Beyene released after 4 hours of detention - Abbay Media

Professor Berhanu Nega Seattle

Prof Berhanu Nega says, "Brave and Kinder Heart needed to defeat TPLF"

የአፈናው መዋቅር አባላት መጋለጣቸው ቀጥሏል !! (አቶ ሀብታሙ አያሌው)

ከላይ እስከ እታች በአድዋ ተወላጆች የተዋቀረው አፋኝ ቡድን ቁንጮውን ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ከእይታ ተሰውረው መኖራቸው ለሁሉም ግልፅ ነው። አሁን ስውሩ ገመና እየተጋለጠ ስም ቢቀይሩ እንኳን የማይቀየረው ሙሉ ገፅታቸው ለአደባባይ የሚውልበት ጊዜ መጥቷል። እነዚህ ጉጅሌዎች ሁለንተናዊ የአድዋ ትግራይ የበላይነት ለማስፈን በመንግስት ስልጣን የተሰየሙ የሌላ ብሔረሰብ አባላትን ሲሰልሉ የኖሩ፤ በውጭ ሀገራት የሚመደቡ የአምባሳደሮችን እንቅስቃሴ እና ዳያስፖራውን አጥንተው መረጃ ሲያደራጁ የኖሩ፤ የአደዋ ትግራይ ወጣቶችን እየመለመሉ ቻይና አውሮፖና አሜሪካ በመላክ በትምህርትና በሃብት የማበልፀጉን ሂደት ያሳለጡ። ህወሓት እንዲደህዩ የፈረደባቸውን የሌላ ብሔረሰብ አባላት የሆኑ ነጋዴዎችን ከገበያው አስወጥተው ያደህዩ፤ በሞት ያስወገዱ፤ ያሰደዱ ፤ ሀብት እየወረሱ ለአድዋ ምልምል ባለሃብቶች ያስረከቡ ግፈኞች የአቤል ደም የሚያሳድዳቸው ቃኤሎች…ይህው ፎቶአቸው… አሁን በር ዘግተው 'አወይ ተጋሊፅና' እያሉ ግምገማቸውን ይቀጥሉ፤ ማጋለጡም ይቀጥላል።Image may contain: 2 people, people smiling, people sitting and indoor

Thursday, December 21, 2017

ወያኔን ማፍረስ አገራችንን ከመፍረስ መታደግ ነው! (የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ)

December 21, 2017
የወያኔው ጦር በጨለንቆ በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ባደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋና እንዲሁም በምዕራብ ሃረርጌ ሃዊ ጉዲና እና ዳሮ ወረዳዎች ውስጥ በኢትዮጵያ ሶማሊ ወገኖች ላይ በደረሰው እልቂት ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት7 የተሰማውን ከፍተኛ ሃዘን ለመግለጽ ይወዳል። ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህይወት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠውና ለዜጎች የህይወት ዋስትናና ነጻነት እውን መሆን ሌት ተቀን የሚታገለው ድርጅታችን፣ እንዲህ አይነት የጅምላ ጭፍጨፋ መርዶዎችን ሰምቶ በዝምታ ለማለፍ የሚያስችለው ትዕግስት የለውም።

የአለም ህዝብ አገራችንን በድህነቷ ይወቃት እንጅ፣ ድህነት ያልበታተነው የህዝብ አንድነትና ፍቅር ያላት አገር መሆኗንም ጠንቅቆ ያውቃል። ይህ በዘመናት የተገነባው ፍቅርና አንድነት የውዷ አገራችን ልዩ መለያ እሴቷ ነው። ይሁን እንጅ ይህ እንቁ እሴት ካለፉት 26 ዓመታት ወዲህ፣ በተለይም ደግሞ በቅርቡ እየተራከሰና ዋጋ እያጣ በመምጣቱ በአገራችን ህልውና፣ በህዝባችን ሰላምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋ ይዞ መጥቷል። ይህ የአንድነትና የፍቅር ማተባችን እየተበጠሰ ያለው በማንኛውም የውጭ ሃይል ወይም በየትኛውም ድርጅት ሳይሆን፣ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ በሚገኘው የወያኔ ቡድን መሆኑ ስጋታችንን አባብሶታል። በየትኛውም አገር የመንግስት ታሪክ የመንግስት የመጨረሻውና ቀላሉ ስራ የዜጎችን ደህንነትና ህልውና ማስጠበቅ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ለዘመናት የተገነባ ፍቅርና አንድነት ባለባቸው አገሮች የሚገዙ መንግስታት፣ የዜጎቻቸውን ደህንነትና ሰላም ማስጠበቅ ካለባቸው ሃላፊነቶች ሁሉ እጅግ ቀላሉ መሆኑን ከታሪክ መማር ይቻላል። ዜጎች ለዘመናት የገነቡትን ፍቅርና አንድነት ከትውልድ ትውልድ እያሸጋገሩ ህልውናቸውንና ደህንነታቸውን አስጠብቀው እንዲጓዙ፣ ፍትሃዊ አስተዳደር መመስረት ግድ ነው። እንደ ጣሊያን የመሳሰሉ የውጭ ወራሪዎች አገራችንን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ያልቻሉት ይህን ዘመን የማይሽረውን የአንድነትና የፍቅር ማተብ ለመበጠስ ባለመቻላቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው። ወያኔ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ይነሳብኛል በሚል ፍርሃት፣ ህዝባችንን እርስ በርስ በማጋጨት በየቦታው የዜጎች እልቂት እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑ ፣ በአለም የመንግስታት ታሪክ ልዩ ያደርገዋል። ይህ ህዝብን እርስ በርስ እያጨፋጨፉ ለመግዛት የሚደረግ ሙከራ፣ ዛሬ ሆድን ሞልቶ ለማደር የጠቀመ ቢመስልም፣ የሁዋላ ሁዋላ ግን “መሬት ተከፍታ በዋጠችኝ” የሚያስብል አደጋ በገዢዎች ላይ ይዞ መምጣቱ የማይቀር መሆኑን ከሊቢያው መሪ ጋዳፊ እና ከየመኑ አህመድ ሳላህ የቅርብ ጊዜ ታሪክ መማር ይቻላል።
በሃዊ ጉዲናና ዳሮ ወረዳዎችም ይሁን በጨለንቆ፣ ከዚያ በፊትም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱ እና አሁንም በመካሄድ ላይ ያሉ ጭፍጨፋዎችና ግጭቶች በህዝብ መካከል የሚካሄዱ ሳይሆኑ ወያኔ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል የሚለኩሳቸውና የሚያራግባቸው መሆኑን ህዝባችን የሚያውቀው ሃቅ ቢሆንም፣ ዛሬም ይህን ሃቅ ልናስታውስ እንወዳለን። ወያኔ በስልጣን ላይ እንዲቀጥል እስከፈቀድንለት ድረስ በዘመናት የተገነባው የፍቅርና የአንድነት ማተባችን ተበጣጥሶ አሁን ከሚታዬውም በላይ እጅግ አስከፊ ወደሆነ የእርስ በርስ ጦርነት እንደሚከተን የታወቀ ነው። ስለዚህ ይህን የአገር ጠላት ከስር መሰረቱ ነቅሎ በመጣል የአንድነታችንንና የፍቅር ማተባችንን መልሶ በማሰር የዜጎቻችንን ህልውና እና ደህንነት ማስጠበቅ ከእያንዳንዱ አገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ የሚጠበቅ ነው። ወያኔ እያንዳንዷን ቀን በስልጣን ላይ በቆዬ ቁጥር በህዝባችን ላይ የሚደርሰው አደጋም በተመሳሳይ መንገድ እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ ዳር ቆመን የምንመለከትብት ጊዜ እንዳበቃ ማወቅ አለብን።
አርበኞች ግንቦት7 ወያኔ በህዝባችን ላይ ያደረሰውን እልቂት ሲያወግዝ፣ የእልቂቶች ሁሉ ምንጭ የሆነውን የወያኔ አገዛዝ እንድናስወገድ የተለመደ ጥሪውን በማቅረብ ነው።
ድል ለኢዮጵያ ሕዝብ!!!

አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ
ታህሳስ 12 2010 ዓ.ም

ESAT Eletawi Wed 20 Dec 2017

ይድረስ ለደኢህዴን አባላት (ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) አባላት የሆናችሁ እና ማገናዘቢያ ልቦና ያላችሁ ወገኖች!በሕወታችሁ ውስጥ ትልቁን ውሳኔ መስጠት ያለባችሁ ወቅት ላይ ናቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ በራሳችሁ ስንፍና ምክንያት ተረጋግታችሁ ለማሰብ እንኳን በቂ ጊዜ እንዳይኖራችሁ አድርጋችኋል። ከሚከተሉት አማራጮች አንዱን መርጣችሁ ተግባራዊ ካላደረጋችሁ እየመጣ ያለው ማእበል ጠራርጎ ይወስዳችኋል፤ ቀሪ እድሜ ካላችሁ የፀፀትና የእፍረት ይሆንባችኋል፤ የታሪክ ጥላሸት ትቀባላችሁ።Resultado de imagen de ዶ/ር ታደሰ ብሩ
ወገኖቼ ከፊታችሁ የተደቀኑት ሁለት ምርጫዎች የሚከተሉት ናቸው። (1) የህወሓት አገልጋይነታችውን አጽንታችሁ ራሳችሁን ቤተሰቦቻችሁንና አገራችን ኢትዮጵያን መግደል መቀጠል፤ ወይም (2) እንደ ኦህዴድና ብአዴን ጓዶቻችሁ ለራሳችሁ ክብር በመስጠት የህወሓትን አምባገንነት በመገዳደር ሕዝባዊ ትግሉን ማገዝ።
የመጀመሪያው መምረጥ ማለት ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ባርነትን ለአገራችን ውድቀትና ውርደት መምረጥ ማለት ነው። ይህንን አማራጭ የሚያስመርጧችሁ በውስጣች ያለው አድርባይነት፣ ስግግብነት፣ አልጠግብ ባይነት፥ ፍርሃት፣ አቅመቢስነትና ጨለምተኝነት መሆናቸው ልብ በሉ። የህወሓት ምርጥ አገልጋይ ለመሆን የምታደርጉት መርመጥመጥ ለጊዜው “የሚያኖር” ቢመስላችሁም እጅግ ... እጅግ ... እጅግ ... እጅግ... እጅግ ... እጅግ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላችሁ እወቁ። የማይቀረው ማዕበል ሲመጣ ከህሊና ፀፀት በተጨማሪ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍላችሁ ካሁኑ እወቁት።
ሁለተኛው አማራጭ ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ የምትኖሩበት፤ እስካሁን የበደላችሁትን ሕዝብ የምትክሱበት አማራጭ ነው። ይህን አማራጭ ለመምረጥ የሚያስፈልጓችሁ ልበሙሉነት፣ ተስፋ እና በሕዝብ ኃይል መተማመን ነው። ይህ አማራጭ ለጊዜው አስቸጋሪ ይመስል ይሆናል ስትጀምሩት ግን በሩቅ ስታስቡት እንደሚያስፈራው እንዳልሆነ ትገነዘባላችሁ።
ደኢህዴን ራሱ ወጥነት የሌለው ድሪቶ ድርጅት እንደሆነ እገነዘባለሁ። ይህንን እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁት ሀቅ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ድሪቶ መተርተር ደግሞ ቀላል ነው።
በመጀመሪያ ደኢህዴን ራሱ በፈጠረው ፈለግ (ስንጥቅ) በትኑት። የሲዳማ ካድሬዎች የሲዳማ አንጃን ፍጥሩ። የወላይታ፣ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የጋሞ፣ የከፍቾ፣ የስልጢ ... ወዘተ የየራሳችሁን አንጃ በመፍጠር ደኢህዴንን አዳክሙት፤ ግደሉት። ከዚያ በኢትዮጵያዊነት ተሰባሰቡ። በዘር መደራጀት በሀገር ላይ የሚያመጣውን አደጋ ተገንዝባችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ፍጠኑ ጊዜ የላችሁም።

Wednesday, December 20, 2017

ESAT DC Insight Abebe Gellaw with Kate Parth August 15, 2017 Aharic Tran...

ጀርመን ድምፅ ሬድዮ ሰበር ዜና DEC,19/2017

ESAT Efeta December 20 2017

የዶክተር ደብረጺዮን ገመና ሲፈተሽ •••••••••••••••••••••••••••••••• በትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ይፋ ወጣ የተባለውና በፌስቡክ ላይ የተሰራጨው የዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ኢንተርኔት አጠቃቀም ታሪክ ብዙ ገመና አጋልጧል:: የወሲብ ፊልም እንደሚመለከቱ እና በየተጓዙበት ውጭ ሀገራት ሴተኛ አዳሪዎችን እንደሚያሳድዱ ከ200 በላይ አባሪ ማስረጃ ፎቶዎች የያዘው መረጃ ይዘረዝራል:: መረጃው መውጣቱ በራሱ በህወሓት ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ እንደነበረ ማረጋገጫም ሆኗል። በእነ አባይ ወልዱ እና ደብረጺዮን ካድሬዎች መካከል የቃላት መጠዛጠዝ እንደነበር ማህበራዊ ሚዲያን ለሚከታተል ግልጽ ነው:: የቢሮው ኃላፊ ገብረሚካኤል መለስ በደብረጺዮን ካድሬዎች ቡድን ከፍተኛ የውግዘት ዘመቻ ሲካሄድባቸው ማየትና ከዚያ በኋላ የተለጠፉት መረጃዎች መነሳታቸው እንዲሁም "በኔ ስም ሌላ ፌስቡክ ተከፍቶ ነው" በሚል እንዲያስትባብሉ መደረጉ ይብለጥ መረጃው ትክክል መሆኑን አረጋግጧል። ገጹ የሰውዬው ካልሆነ ስለምን እሳቸው ላይ መዝመት አስፈለገ? በእርግጥ መረጃው እንዴት ተዓማኒ ይሆናል? በኦሬገን ዩኒቨርስቲ በሚዲያ ላይ የድክትሬት ጥናቱን የሚያደርገው እንዳልካቸው ኃይለሚካኤል ተጨማሪ ማረጋገጫ አለኝ ይላል:: ዝግጅቱን ያደምጡ ዘንድ ጋብዘናል::

ዶክተር ታደሰ ብሩ ነጻ ተባሉ (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010)

በ8 ጉዳዮች በሽብር ወንጀል በእንግሊዝ መንግስት የተከሰሱት ታዋቂው ምሁርና ፖለቲከኛ ዶክተር ታደሰ ብሩ በተከሰሱባቸው ሁሉም ጉዳዮች ነጻ ተባሉ።
ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በሕዝብ በተመረጠ ዳኝነት/ጁሪ/ ዶክተር ታደሰ ብሩን በሙሉ ድምጽ ነጻ ናቸው ብሏል።
ዶክተር ታደሰ ብሩ ሂደቱን ሲከታተሉና ሲጨነቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል።
ዶክተር ታደሰ ብሩ የተከሰሱት የሽብር ወንጀሎች ለምርምርና ለነጻነት ትግል የተጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍትን ይዘህ ተገኝተሃል የሚልና በሽብር ማሰልጠኛ ቦታዎች ተገኝተሃል በሚል ነበር።
ጉዳዮቹ በክስ መልክ በእንግሊዝ አቃቢ ሕግ ቢቀርቡም በሀገሪቱ የፍትህ ስርአት ያለ በመሆኑ ሁኔታው ተጣርቶ ነጻ እንደሚሆኑ ብዙዎች ገምተው ነበር።
እንደተገመተው በሕዝብ በተመረጡ ዳኞች/ጁሪ/ሲታይ የነበረው የዶክተር ታደሰ ብሩ ክስ በ8ቱም ጉዳዮች ነጻ ተብሎ ውሳኔ አግኝቷል።
ዶክተር ታደሰ ብሩ ከውሳኔው በኋላ ለኢሳት እንደገለጹት በክሱ የቀረቡ 8ቱም ጉዳዮች ትክክል እንዳልነበሩ በመጨረሻ ተረጋግጧል።
ዶክተር ታደሰ ብሩ እስካሁን በነበረው የክስ ሂደት ጉዳዩ አሳስቧቸው ሲጨነቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያንም ምስጋና አቅርበዋል።
የዶክተር ታደሰ ብሩን በሽብር ወንጀል መጠርጠር መነሻ በማድረግ በሕወሃት የሚደገፉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ሲያራግቡ እንደነበር ይታወሳል።

Tuesday, December 19, 2017

በ8 ጉዳዮች በሽብር ወንጀል በእንግሊዝ መንግስት የተከሰሱት ታዋቂው ምሁርና ፖለቲከኛ ዶክተር ታደሰ ብሩ በተከሰሱባቸው ሁሉም ጉዳዮች ነጻ ተባሉ። (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010)


 ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በሕዝብ በተመረጠ ዳኝነት/ጁሪ/ ዶክተር ታደሰ ብሩን በሙሉ ድምጽ ነጻ ናቸው ብሏል። ዶክተር ታደሰ ብሩ ሂደቱን ሲከታተሉና ሲጨነቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል። ዶክተር ታደሰ ብሩ የተከሰሱት የሽብር ወንጀሎች ለምርምርና ለነጻነት ትግል የተጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍትን ይዘህ ተገኝተሃል የሚልና በሽብር ማሰልጠኛ ቦታዎች ተገኝተሃል በሚል ነበር። ጉዳዮቹ በክስ መልክ በእንግሊዝ አቃቢ ሕግ ቢቀርቡም በሀገሪቱ የፍትህ ስርአት ያለ በመሆኑ ሁኔታው ተጣርቶ ነጻ እንደሚሆኑ ብዙዎች ገምተው ነበር። እንደተገመተው በሕዝብ በተመረጡ ዳኞች/ጁሪ/ሲታይ የነበረው የዶክተር ታደሰ ብሩ ክስ በ8ቱም ጉዳዮች ነጻ ተብሎ ውሳኔ አግኝቷል። ዶክተር ታደሰ ብሩ ከውሳኔው በኋላ ለኢሳት እንደገለጹት በክሱ የቀረቡ 8ቱም ጉዳዮች ትክክል እንዳልነበሩ በመጨረሻ ተረጋግጧል። ዶክተር ታደሰ ብሩ እስካሁን በነበረው የክስ ሂደት ጉዳዩ አሳስቧቸው ሲጨነቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያንም ምስጋና አቅርበዋል። የዶክተር ታደሰ ብሩን በሽብር ወንጀል መጠርጠር መነሻ በማድረግ በሕወሃት የሚደገፉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ሲያራግቡ እንደነበር ይታወሳል።

ESAT Latest News Amsterdam December 19, 2017

Sunday, December 17, 2017

Ethiopia’s political crises and the oppositions road map displayed in Br...

ESAT Special news Dec 16 2017

Mamila Lukas - Zim New | ዝም ነው - New Ethiopian Music 2017 (Official Video)

አንድ ሬጂመንት የአጋዚ ኮማንዶ ሰራዊት ወደ ፌደራል ፖሊስ ተዛወረ *የጸጥታ ኃይሎች ዜና (ታህሳስ 7, 2010 ዓ.ም)

በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ፌደራል ፖሊስን ለማጠናከር በሚል በአጋዚና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ስር ከሚገኘው የአጋዚ ኮማንዶ አንድ ሬጂመንት ሰራዊት ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲዛወር ተደርጓል።Image may contain: one or more people and outdoor በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚፈጠሩ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ በፌደራል ፖሊስ የአቅም ውሱንነት ተፈጥሯል። ይህን ምክንያት በማድረግ ነው በመከላከያ ውስጥ የሚገኝን ሰራዊት ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲዛወር የደህንነቱ መስሪያ ቤት የጠየቀው። የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት 5 ሬጂመንት ሰራዊት ከመከላከያ ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲዛወር ጥያቄ ቢያቀርብም በጄነራል ሳሞራ የሚመራው መከላከያ ወደ ፌደራል ፖሊስ የሚዛወረው አንድ ሬጂመንት የአጋዚ ኮማንዶ ሰራዊት ብቻ እንዲሆን ፈቅዷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደ ፌደራል ፖሊስ የሚገቡ አዲስ ተመልማዮች ከመቼው ጊዜ በላይ ቁጥሩ ማሽቆልቆሉ ነባር የሰራዊት አባላትን ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲያዛውሩ ተገደዋል። ወደ ፌደራል ፖሊስ የሚዛወሩ የአጋዚ ኮማንዶ የሰራዊት አባላት በአሁን ሰአት ሃዋሳ ቶጋ በሚገኘው የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ካምፕ ውስጥ ልዩ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ። በስልጠናው ከነፍስ ከወፍ እስከ RPG ያሉ መሳሪያዎች በመጠቀም የተኩስ ልምምድ እየተደረገ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም ህዝባዊ አመጾችን እንዴት መበተን እንደሚቻል የሚያሳይና የከተማ የጸረ ሽምቅ ውጊያ ቴክኒኮችንም ያካተተ ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአጋዚ ኮማንዶ ሰራዊት በዚህ ያህል ቁጥር ቀጥታ ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲዛወር ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ መረጃውን ያስተላለፉት ወኪሎቻችን ይገልጻሉ። ፌደራል ፖሊስ በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀጥታ ቁጥጥር ስር ያለ እንደመሆኑ አቶ ጌታቸው አሰፋ ከመከላከያ የሚመጣበትን ማንኛውውም አደጋ ቀድሞ ለመከላከል እንዲያስችለው እየሰራ እንደሆነ ይታመናል። ፌደራል ፖሊስ ከህግ አግባብ ውጪ የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ተዋጊ ሃይል ሆኖ መወሰዱ በመከላከያ ውስጥ ቅሬታን የፈጠረ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል። የፌደራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኮሚሽነር አሰፋ አቢዩ ወደዚህ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት ለረጅም ጊዜ በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ሲሰራ እንደነበረ ይታወሳል።

የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚታገዱና የሚታሰሩ የኦህዴድ እና የብአዴን ባለስልጣናት ስም ዝርዝር ማዘጋጀቱ ታወቀ *የጸጥታ ኃይሎች ዜና (ታህሳስ 7, 2010 ዓ.ም)

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የሚደረጉ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ይህን ተቃውሞዎች ይደግፋሉ የሚባሉ የኦህዴድና የብአዴን ባለስልጣናትን ከሃላፊነታቸው የማንሳትና የተወሰኑትን ደግሞ ወደ እስር ቤት ለማስገባት የሚያስችል ስራዎች በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት በከፍተኛ ሚስጥር እየተከናወነ እንደሆነ ከደህንነት የተገኘ መረጃ ያመለክታል። Image may contain: 1 person, text and closeupየደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ለህወሃት ታማኝ አይደሉም ተብለው የሚጠረጠሩ በብአዴን እና በኦህዴድ ውስጥ ከመካከለኛ አመራር ጀምሮ ያሉ ግለሰቦች ስማቸው በዝርዝር ተቀምጦ በስውር ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል። በነዚህ የብአዴን እና የኦህዴድ ባለስልጣናትን ላይ በአሁን ሰአት እርምጃዎች የሚወሰዱ ከሆነ ሃገሪቱ ውስጥ ከተፈጠረው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ለሌላ ውስብስብ ችግሮች ልንጋለጥ እንችላለን በማለት እንደየሁኔታው ለወደፊቱ በተጠረጠሩ የብአዴን እና የኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የደህንንነቱ መስሪያ ቤት ውሳኔ አሳልፏል። ብአዴን እና ኦህዴድ፤ የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ሽብርተኛ ብሎ በሚጠራቸው ቡድኖች በተለይ የአርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ መጠቀሚያ ሆነዋል የሚል የትንተና ሪፖርት በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቧል። በዚህም ምክንያት ብአዴን እና ኦህዴድ እራሳቸውን ማጽዳት ይኖርባቸዋል በሚል በብአዴን እና በኦህዴድ ውስጥ ያሉ ከመካከለኛ አመራሮች ጀምሮ ያሉ ባለስልጣናትን ያካተተ ስም ዝርዝር በቀጣይ ለሚወሰድ እርምጃ ተዘጋጅቶ መቀመጡን ከደህንነት የተገኘው መረጃ ያስረዳል። የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ የሚነሱ ተቃውሞዎች የብአዴን እና ኦህዴድ እጅ አለበት ሲል ይከሳል። በደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚቀርቡ ሪፖርቶችም የሚያስረዱት በብአዴን እና ኦህዴድ ውስጥ ያሉ አመራሮች ከተቋውሞ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት ነው። በተቃራኒው በብአዴን እና በኦህዴድ ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት፤ የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ወኪሎቹን በመጠቀም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የእርስ በርስ ግጭቶች እንዲነሱ ይሰራል ሲሉ ይከሳሉ። የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት በክልሎቹ የስልጣን ጠገግ ውስጥ እንደፈለገ በመግባት ከህግ ውጪ ያሻውን እየፈጸመ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት ክልሎቹ የደህንነት መስሪያ ቤቱን ፍላጎት ማሟላት ሳይችሉ ሲቀሩ ደህንነቱ እርምጃዎችን እንደሚወሰድባቸውና የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት እራሱን የቻለ ስውር መንግስት እንደሆነ ይገልጻሉ። የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የክልሎችን የጸጥታ ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የሚያችለውን አሰራር ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይታወቃል።

Saturday, December 16, 2017

YETSETETA HAYELLOCH DECEMBER 16 2017

እነ ለማና የኢህአዴግ ስብሰባ (በጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

'የትግራይ የበላይነት' በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች የሰሞኑ ስብሰባ የፍጥጫ አጀንዳ ሆኗል። ኦህዴዶች ''የበላይነቱ'' እስከመቼ ሲሉ ወጠረው ይዘዋል። ብአዴኖች አጉረምርመዋል። ህወሀት ይህ ጥያቄ እንዴት ይነሳል ሲል እየፎከረ ነው። በቅርቡ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ 'የትግራይ የበላይነት የለም ብለን ከስምምነት ደርሰናል' ያሉት መግለጫ ውሃ ብልቶታል። በተቃዋሚው መንደር ለዘመናት ሲነገር የነበረው፡ የነጻነትና የዲሞክራሲ ሃይሎች ሲወተውቱ የከረሙት፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አደጋ እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ በስጋት ሲገለጽ የዘለቀው፡ 'የበላይነት' ዛሬ በኢህአዴግ ሰፈር ፈንድቶ ወጥቷል። ጊዜ ደግ ነው። ገና ብዙ ያሳየናል።Image may contain: 5 people
ሰሞኑን እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከፍተኛ ፍጥጫ የታየበት እንደሆነ ይነገራል። ህወሀት 'ውስጤን አጽድቼአለሁ። ተራው የእናንተ ነው' ብሎ የኦህዴድንና የብአዴንን ጉሮሮ አንቆ ይዟል። ሁለቱ ድርጅቶች አፍንጫህን ላስ ዓይነት ምላሽ እየሰጡት ናቸው። ህወሀት የለማንናን የገዱን ቡድኖች ጠራርጎ ለማስወገድ እንቅልፍ አጥቶ አድሯል። በሁለቱ ክልሎች ለተባባሰው ቀውስ ተጠያቂ አድርጎ እየጠዘጠዛቸው ሲሆን እነሱም የሚበገሩ አልሆኑም። በጸጥታና ደህንነት መስሪያ ቤቱ ውክልናችን አንሷል የሚል ጥያቄ በድፍረት ማንሳታቸው ይነገራል። ህወሀት ለሩብ ክፍለዘመን የዘለቀበት የጌታና ሎሌ ጨዋታ እያበቃ መሆኑ አስደንግጦታል። እንዳሻው የሚፈነጭበት፡ እንደፈለገ የሚፈነጥዝበት ዘመን ማክተሙን የሚያሳዩ ፍንጮችን ማየቱ ብርክ አሲዞታል።

Friday, December 15, 2017

ESAT Daily News Amsterdam December 15,2017

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መቀጠሉ ታወቀ። (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010)

 የደህንነቱ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲፈርስ ጠይቀዋል። ብአዴንና ኦህዴድ ራሳችሁን አጥሩ በሚል በሕወሃት የቀረበው ሃሳብም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህ ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለው ስብሰባ ሸምጋዮች እንዲገቡበት የቀረበው ሃሳብም ውድቅ ተደርጓል። ስብሰባው ረዥም ጊዜያትን እንደሚወስድም ተገምቷል። ሆኖም ስብሰባው ሳያልቅ የማረጋጊያ መግለጫ በቀጣዮቹ ቀናት ይወጣል ተብሎም ይጠበቃል። ማክሰኞ እለት በተጀመረው በዚህ የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቱ በተጨማሪ ነባር አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛል።No automatic alt text available. ከመከላከያና ከደህንነት የተወከሉ ግለሰቦችም በስብሰባው ላይ መገኘታቸውንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በሀገሪቱ ለቀጠለው አለመረጋጋት የብአዴንና የኦሕዴድ እጅ አለበት በሚል ከሕወሃት የቀረበውን ሃሳብ ሁለቱም ድርጅቶች ተቃውመውታል። የኦህዴድ አመራሮች አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን በስብሰባው ላይ መወረፋቸው ተመልክቷል። በአቶ ለማ መገርሳና በአቶ አባይ ጸሃዬ መካከል የነበረው አለመግባባት ከጭቅጭቅ ያለፈ እንደነበርም መረጃዎች አመልክተዋል። የኦህዴድ አመራሮች በሀገሪቱ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ተገቢ ውክልና የለንም በሚል ጥያቄ ማንሳታቸውም ይፋ ሆኗል። የሐገሪቱ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃላፊና የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ አሁን ያለው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ሀገሪቱን የመምራት አቅም ስለሌለው መፍረስ ይገባዋል በማለት አስተያየት ሰጥተዋል። እኚህ የደህንነት ባለስልጣን በስብሰባው ላይ በቋሚነት ባይሳተፉም ከደህንነት መስሪያ ቤት የመጡ ሰዎች ግን በቋሚነት እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል። በውዝግብና በጭቅጭቅ የቀጠለው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ልዩነቱ እየሰፋ መቀጠሉን ተከትሎ ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን የጨመረ ሸምጋይ ቡድን እንዲገባ የቀረበውን ሃሳብ ብአዴንና ኦህዴድ በመቃወማቸው ውድቅ ሆኗል። በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ የበላይነት አለ በሚል ከኦህዴድና ብአዴን የተነሳውን ሃሳብ ጨምሮ ውዝግብ የፈጠረው ስብሰባ ረዥም ጊዜያትን ሊወስድ እንደሚችል ታምኗል። ሆኖም አለመግባባቱ አደባባይ እንዳይወጣና ለመላምቶች በር ላለመክፈት በሚል የማረጋጊያ መግለጫ በቀጣዮቹ ቀናት ይወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የአውሮፓ ፓርላማ በጠራውና ኢትዮጵያን በተመለከተው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሽግግር ሰነድ ማቅረቡ ተገለጸ። (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010)

የሽግግር ሰነዱ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሽግግር ስርዓት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል። በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት ከዚህ ቀደም ይከተለው የነበረውን አካሄድ በመተው የለውጥ ሃይሎች የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ጠይቋል። Image may contain: 3 people, people sitting and indoorየአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የምክክር መድረክ ሲያዘጋጅ የዛሬው የመጀመሪያው አይደለም። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትኩሳት በተፈጠረ ቁጥር በተለይም ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ስብሰባ መቀመጥ የተለመደ ነበር። የዛሬው በአውሮፓ ፓርላማ የተዘጋጀው ስብሰባ ግን የተለየ ነው ይላሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አመራሮች። ከዚህ ቀደም የቀውሱ ፈጣሪ የሆነውን የህወሀት አገዛዝ በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚፈልጉት የምዕራብ መንግስታት መፍትሄውንም ከዚያው ከስርዓቱ የሚጠበቅ እንዲሆን ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ኢትዮጵያ የደረሰችበት የቀውስ ደረጃ የበፊቱን አካሄዳቸውን እንዲቀይሩ እንዳደረጋቸው በስብሰባው ላይ የተጋበዙት አካላት ለኢሳት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ እንደሚሉት የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያ ቀውስ ያሳሰባቸው በመሆኑ ቀውሱን ለመፍታት የቀድሞውን አካሄድ ለመተው መፈለጋቸውን ፍንጭ ያሳዩበት ስብሰባ ነው የዛሬው። ዶክተር ዲማ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ቀውስ ለናንተም ይተርፋልና አስቡበት የሚል ግልጽ መልዕክት ዛሬ ለአውሮፓዎቹ እንዲደርሳቸው አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት አሳሳቢ ቀውስ በስልጣን ላይ ባለው የህወሃት አገዛዝ መፍትሄ የሚገኝ እንዳልሆነ የተረዳው የአውሮፓ ፓርላማ ስርዓቱን ለመለወጥ የሚታገሉ ሃይሎችን በመጋበዝ ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ በተነጋገረበት በዛሬው መድረክ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ተባባሪ ሊቀመንበር እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአውሮፓ ፓርላማ በሁለት ምክንያቶች የዛሬው ስብሰባ እንደጠሩት ገልጸዋል። አንደኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ ትግል እያደረገ መሆኑን፣ የስርዓት ለውጥ ከመጣም ለኢትዮጵያ አደገኛ እንደማይሆን ለመፈተሽ ሲሆን ሁለተኛው በተቃዋሚዎች በኩል ከስርዓት ለውጥ በኋላ ያላቸውን ዝግጅት ለማወቅ የተዘጋጀ ስብሰባ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ ጠቅሰው በአውሮፓ ፓርላማ በተጠየቅነው መሰረት የሽግግር ሰነድ አቅርበናል ብለዋል። በስብሰባው ላይ የአውሮፓ ፓርላማም ሆነ ሌሎች የምዕራቡ መንግስታት ቢፈልጉም ባይፈልጉም የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረው ትግል ወደኋላ የማይቀለበስ መሆኑን በግልጽ እንዲያውቁት መደረጉን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አመራሮች ገልጸዋል። የአውሮፓ ፓርላማም እስከዛሬ በነበረው መንገድ መቀጠል ቀውሱን የሚያባብስ መሆኑን በመረዳት ከሌሎች አካላት ጋር እንደሚመካከርበት መግለጹን ለማወቅ ተችሏል። በስበሳባው ላይ የተካፈሉት የአውሮፓ ፓርላማ አባል ማዳም አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት በውጭ የሚገኙና ለፍትህና ነጻነት የሚሰሩ ሚዲያዎችን በገንዘብ ማገዝ ይኖርበታል ማለታቸው ተጠቅሷል። በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ሃይሎች የተወከሉ እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ላይ ከሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ድርጅቶች የተጋበዙ ተወያዮች ተገኝተውበታል።

የወያኔ አገዛዝ ካጠመደልን የእርስ በእርስ እልቂት ህዝባችንንና አገራችንን እንታደግ። የአርበኞች ግንቦት7 ርዕስ አንቀፅ December 15, 2017


የህወሃት አገዛዝ ለሥልጣን ዕድሜው መራዘም ሲል በአገራችን ያሰፈነው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የጋራ ታሪክ ባለቤት የሆነውን ህዝባችንን በባህልና በቋንቋ ሸንሽኖ አንደኛው ከሌላኛው ጋር ምንም የሚያቆራኘው ታሪካዊም ሆነ ወገናዊ ትሥሥር በመካከሉ እንደሌለ በመስበክ እያንዳንዱ በጥላቻና በጥርጣሬ እንዲተያይ የማድረግ ስልታዊ እርምጃ ነው።

ተደጋግሞ እንደተገለጸው ህወሃት የተጠቀመበት ይህ የአንድ አገር ዜጎችን በቋንቋና በባህል ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ አውሮፓዊያን አፍሪካን በቅኝ ግዛትነት በተቀራመቱበት ዘመን ከተጠቀሙበት ስልት የተቀዳ መሆኑ ግልጽ ነው። በዚያን ዘመን ቅኝ ግዛት ሥር የወደቁ የአፍሪካ አገሮች የቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ተጠቃለው ከወጡላቸውና በራሳቸው ዜጎች መመራት ከጀመሩ ወዲህ እንኳ ትተውባቸው ከሄዱት የርስ በርስ ክፍፍል መውጣት አቅቶአቸው ላለፉት 50 እና 60 አመታት በመገዳደልና አንዱ ሌላውን እንደጠላት በመቁጠር ሲናቆሩ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥቻለሁ ላለው ህዝባቸው ኑሮ መሻሻል አንዳችም ፋይዳ ሳያስገኙ በተቃራኒው የመከራ፤ የስቃይና አለመረጋጋት ምንጭ ሆነው ዘልቀዋል ።

Friday, December 8, 2017

ESAT Daily News Amsterdam December 08,2017

በአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የሚመራ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊላክ ነው (ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010)

አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ በማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የሚመራ የልዑካን ቡድንን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ መዘጋጀቱ ታወቀ።
ተቋሙ ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ የሚልከው በሀገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የኢኮኖሚው ሁኔታ እያሳሰበው በመምጣቱ መሆኑ ታውቋል።
የሀገሪቱ ተጠባባቂ የውጭ ምንዛሪ ወደ 700 ሚሊየን ዶላር የወረደ ሲሆን በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት በጅቡቲ የተከማቹ እቃዎችን ማንሳት እንዳልተቻለም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በወጭ ንግድ የተሰማሩም እስከ አንድ አመት ለውጭ ምንዛሪ ወረፋ እንደሚጠብቁም ታውቋል።
በኢትዮጵያ የተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረትበሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቅሴ ላይ ብርቱ ማነቆ ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህም በአመቱ ሊጀመሩ የታቀዱ በርካታ ፕሮጀክቶች መደርደሪያ ላይ የቀሩ መሆናቸውም ታውቋል።
ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ሊሰራ የታቀደው የ550 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በዚህ አመት ሊጀመር መርሃ ግብር ከተያዘለት በኋላ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተሰርዟል።
የሐገሪቱ ተጠባባቂ የውጭ ምንዛሪ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የሚገልጹት የኢሳት ምንጮች ለ3 ሳምንታት ብቻ የሚበቃ ሲሆን መጠኑም 700 ሚሊየን ዶላር እንደሆነም ተመልክቷል።
በዚህ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ኢትዮ-ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት ያለባቸውን ዕዳ ለመክፈል የውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግር እንደገጠማቸው በይፋ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ በብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠው የራሱ 100 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በተከሰተው እጥረት ሳቢያ ሊለቀቅለ እንዳልቻለም ይፋ ሆኗል።
የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ በነዳጅና በመድሃኒት ግዢ ላይ ጭምር ተጽእኖ ባመጣበት በአሁኑ ወቅት በወጭ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎችም የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ከፍተኛ ችግር ገጥሟቸዋል።
የውጭ ምንዛሪው ለነጋዴዎቹ እየተሰጠ ያለው በወረፋ ሲሆን የተሳካላቸው በ8 ወራት ውስጥ ሲያገኙ ያልተሳካላቸው እስከ አንድ አመት መጠበቅ እንደሚገደዱ የብሔራዊ ባንክ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።

ESAT DC Daily News Thur 07 Dec 2017

“ጌታቸው አሰፋ” የሰቆቃና ቶርቸር ዳይሬክተር ጄነራል (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)


ከአድዋ ስረወ መንግስት መሪዎች አንዱና ዋናው ነው። የደህንነት(የሰቆቃ) መስሪያ ቤት ዳይሬክተር፡ ገዳይ አስገዳይ፡ ገራፊ፡ አስገራፊ፡ የለየለት ጨካኝ። መልኩ ቀይ፡ ልቡ ጥቁር፡ ባህሪው ልስልስ፡ ተግባሩ እርኩስ፡ ድምጹ የማይሰማ፡ የጭካኔው ወሰን በኢትዮጵያ ምድር ጫፍ እስከጫፍ የደረሰ ፍጹም አረመኔ ሰው ነው። በቴሌቪዥን መስኮት ታይቶ አይታወቅም። የአደባባይ ሰው አይደለም። መድረክ፡ ስብሰባ ላይ አይታይም። ቢኖር እንኳን በፎቶና በቪዲዮ ራዳር ውስጥ እንዳይገባ ይደረጋል። እናቶቻችን 'ቀትረ ቀላል፡ ጥላቢስ፡' የሚሉት ዓይነት ሰው ነው።Bilderesultat for አቶ ጌታቸው አሰፋ
ማዕከላዊን ረገጠው ህይወታቸው ሳያልፍ የወጡ እድለኛ ታሳሪዎች በአንድ ቃል እንደሚናገሩት ሰቆቃ፡ ግርፋት፡ ግድያ፡ የሚፈጸሙት ትግርኛ በሚናገሩ ሰዎች ነው። የእነዚህ ሰዎች አለቃ፡ መሪ ደግሞ ይህ ሰው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 15 ዓመታት በተፈጸሙት ፖለቲካዊ ሰቆቃዎች፡ ግድያዎች፡ እስሮች፡ውስጥ ይህ ሰው ዋናው ተዋናይ ነው። ይህ ሰው የስንቱን የኢትዮጵያ ልጅ የቀን ብርሃን አጨልሟል፡፡ የስንቱን ወጣት ተስፋ ቀጥፏል፡፡ አያሌ ህጻናትን ያለአባት፡ ያለእናት አስቀርቷል። ስንቱን ቤተሰብ በትኗል።
ይህ ሰው ማዕከላዊ ሌሊቱን ሲገርፍ ሲያስገርፍ፡ ያድራል፡ ሲደክመው ዋሽንግተን ዲሲ መጥቶ ውስኪውን ይጎነጫል። የኢትዮጵያን ወጣት ዘቅዝቆ፡ በርበሬ እያጠነ፡ በሽንት የተነከረ ጨርቅ እያጎረሰ ወፌ ላላ እየሰቀለ፡ ብልት እያኮላሸ ሲያሰቃይ ይቆይና ለእረፍት ጣሊያን ሲሲሊያ የባህር ዳርቻ በረር ብሎ ይንፈላሰሳል። ድንቁርናው አይጣል ነው። በዊኪሊክስ እንደተጋለጠው ከሆነ ይህ ሰው አሜሪካንን አስፈራርቷል። ያማማቶ ለተባሉ የአሜሪካ አምባሳደር ''አሜሪካ የእኛን ተቃዋሚዎች መርዳት የማታቆም ከሆነ እኛም ለአሜሪካን ተቃዋሚዎች ድጋፍ እናደርጋለን'' ማለቱን ዊክሊክስ አስነብቦናል።
ህወሀት የአድዋን ስረወ መንግስት በሰየመበት በሰሞንኛው መድረክ ይህን ሰው ዳግም ከፍ ያለ ቦታ ሰጥቶታል። መልዕክቱ ግልጽ ነው። ለውጥ የለም። የነበረው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ቀጥቅጠን፡ ረግጠን እያኮላሸን፡ በኤሊክትሪክ ሽቦ ጡት እየተለተልን በጉልበትና በሃይል እንቀጥላለን የሚል መልዕክት መሆኑ ይገባናል። ህወሀት ተውሳኩን አስወግጄ መጣሁ፡ ታድሼ፡ ተወልውዬ በአዲስ መንፈስ ለለውጥ ተነሳሁ ያለው ይህን የዲያቢሎስ ቁራጭ፡ የሳጥናኤል ወንድም፡ ክፉና ነውረኛ ሰው ከስልጣን ማማ ላይ አስቀምጦ ነው።
ይህ ሰው በሰው ልጅ ላይ በፈጸመው ወንጀል፡ በዘር ማጥፋት፡ ወደር በሌለው የሰቆቃ ተግባሩ እጁ ወደ ኋላ ተጠርንፎ በፍትህ አደባባይ ቅጣቱን ማግኘት የሚገባው ሰው ነበር። ደግሞም አይቀርም። ይዘገይ እንደሁ እንጂ ፍትህ ይመጣል።

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የዕለተ አርብ ህዳር 29 ቀን 2010ዓ.ም. ፕሮግራሞቻችን
************************
የዕለቱ አርዕስተ ዜና
* በተለያዩ የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል ከተሞች የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ መሆኑ ተዘገበ።
* የህወሓት አገዛዝ ለጂቡቲ የንፁህ ውኃ መጠጥ ሊያቀርብ መሆኑ ታወቀ።
* በአርባምንጭ ከተማ ከግብር ጋር በተያያዘ ስድስት የህብረት ስራ ማህበራት አገልግሎት ማቆማቸው ታወቀ።
የሚሉትን ዜናዎችና
ቀጣዩ
፠የአርበኞች ማስታወሻ የተሰኘው መሰናዷችን ነው ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
Image may contain: sky and outdoor

Thursday, December 7, 2017

ESAT Insight Abebe Gellaw with David Steinman AMHARIC TRANSLATED, Aug 8...

የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ስለላ ሶፍት ዌር ተሰናከል Cyber bit crashed


የህወሃት ብሐራዊ መረጃ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎችን ለመሰለል ከእስራኤል ኩባንያ የተገኘ ማላዋሪ ( Malware ) የተሰኘ የስለላ ዘዴ ቢጠቀምም የስለላላ መረቡ ኢላማ በተደረጉ ተሰላዬች ቁጥጥር ስር ወድቋል.. ፒ.ኤስ.ኤስ.(PSS) ፒሲ ሰርቪሊያንስ ሲስተም ( PC Surveillance System ) ተብሎ የሚጠራ የዊንዶ ፕሮግራም የተጠቀመዉ የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ያሳበዉን ሳያሳካ አለማቀፋዊ ስህተት ዉስጥ እራሱን ከቷል።
( Cyber bit, an Israel-based cyber-security company ) ሳይበርቢት ከተባለ የእስራኤል የደህንነት ድርጅት የተገዛዉ ይህ አደገኛ የጠለፋ መሳሪያ በሐገር ዉስጥ እና በዉጭ ሐገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ለመሰለል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊዉል የታሰበ ነበር።
አንድ ሲትዝን ላብ ( Citizen Lab researchers promptly notified )የተባለ አጥኚ ቡድን እንዳተተዉ የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ህዝቦቹ ላይ ስለላ ሲያካሄድ ይህ የመጀመሪያዉ አለመሆኑን ገልጾ በቀጣይ ለኢትዮጵያ መንግስት አደጋ የሆኑ የስለላ ሚስጥሮች መዉጣትና በሀገር ዉስጥ በሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች ወይም ምሁራን ላይ የተደረገዉ የስለላ ደባ ስርአቱን ወደ ማይታመንበትና ወደ አዘቅት እንደሚከተዉ ፍንጭ ሰጥቷል 
በተለይም ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት ያገለላቸዉ እነ ሃኪንግ ቲም እና ጋማ ቡድን ( HackingTeam and Gamma Group ) የተባሉ ሁለት ሶፍት ዌር ካምፓኒዎች ከእስራኤሉ ሳይበር ቢት ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸዉ ለስጋቱ መበራከት አንዱና ዋናዉ ሲሆን በስለላ ስራዉ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ኮማንድ ኮንትሮል መቆጣጠሪያ ሲዋቅሩ በመሰናከላቸዉ ( command and control (C&C) server ) የስለላ ተቋሙ ሚስጥሮችና መረጃዎች መዝረክረካቸዉንም ፍንጮች አክለዉ አስቀምጠዋል። 
ይህ ምሥጢራዊ የስለላ ስራ ባለፈው ዓመት 2016 የተጀመረ ሲሆን የተለያዩ ድረ ገጾችን የፌስ ቡክ የዉስጥ መስመሮችን ኢሜሎችን እና የተለያዩ የመገናኛ አዉታሮችን ለመስበር ድህረ ጣቢያዎች ላይ የቪዲዮ ወይም ፒዲኤፍ ፋይሎችን ለማየት አዶቤ ፍላሽ ማጫወቻ ዝማኔ ወይም (Adobe PdfWriter ) የተባለ መተግበሪያ ሶፍት ዌሮችን ለማውረድ፣ የአይፒ አድራሻዎች ምዝግቦችን እና የመሳሰሉትን ለማረጋገጥ ታስቦ የነበረ ሲሆን የህወሃት የስለላ ቡድን አባላቶች የሐገር ዉስጥ እና ከሐገር ዉጭ በሚኖሩ ዜጎቻቸዉ ላይ ስለላ ለማካሄድ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
Ethiopian operatives make crucial mistake 
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

(አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የዛሬ የዕለተ ሓሙስ ህዳር 28 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን ፦
ዜና .... 
* በአንድ የሙርሲ ተወላጅ ላይ የደረሰ የመኪና አደጋ ተከትሎ በሙርሲና በጅንካ ብሄሮች መካከል ከፍተኛ ግጭት መድረሱ ተሰማ 
* በአፋር ክልል ውስጥ አንድ ጀርመናዊ ቱሪስት መገደሉ ተሰማ
* ሃረር ወይኒ ቤት ውስጥ በተነሳ ቃጠሎ አንድ እስረኛ ሲሞት በርካቶች መጎዳታቸው ታወቀ።
፠ባለፈው ሳምንት ከአክትቪስት መስፍን ፈይሳ ጋር የጀመርነውን ሁለኛውንና የመጨረሻውን ቃለ ምልልስ እናስደምጣችኋለን። ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው።
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Image may contain: sky and outdoor

Wednesday, December 6, 2017

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነባርና ታሪካዊ አካባቢዎችን ማፍረስ ጀመረ። (ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010)

ገዳም ሰፈርና ጌጃ ሰፈርን ጨምሮ አምስት ነባር ሰፈሮች ሙሉ ለሙሉ ይፈርሳሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2010 ከያዘው ከ40 ቢሊየን ብር አመታዊ በጀት ውስጥ 30 ቢሊየን ብሩን ከማዘጋጃ ቤትና ግብር ነክ ገቢዎችን ከሕብረተሰቡ በቀጥታ የሚሰበስበው መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ገቢ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻውን የያዘው ነባር መሬቶችን በማስለቀቅ መሬቱን በመሸጥ የሚያገኘው እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።Image may contain: outdoor
የቀድሞ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከተማ ልማት ቢሮ አማካሪ ዶክተር ግዛቸው ቴሶ ለኢሳት እንደገለጹት አገዛዙ ነባርና ታሪካዊ አካባቢዎችን የሚያፈርሰው በዋናነት የነዋሪውን ማህበራዊ ትስስር ለመበጣጠስ በማሰብ ነው ብለዋል። የህብረተሰቡ ዲሞግራፊ በተቀየረ ቁጥር አዲስ አበባ የስርአቱ ተቃውሞ ማዕከል መሆኗ ሊቀንስ እንደሚችል አጋዛዙ እምነት እንዳለው ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በከተማዋ ነዋሪ ተቃውሞና ቅሬታ ለሁለት አመት አቋርጦት የነበረውን ነባርና ታሪካዊ የመዲናይቱን አካባቢዎች ማፍረስ መጀመሩን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

ESAT News Analysis December 6 2017 on ARDUF

Forceful deportation of Ethiopians to a tyrant regime in Ethiopia is underway from Norway. This illegal act of deportation should be condemned. The deportees do not bear or require to carry a passport or any other legal travel document. The Norwegian police forcefully packed them simply into the direct flights of Ethiopian airlines from Oslo to Addis Ababa. All freedom loving Should condemn this illegal deportation procedure. This is an act of undermining the right of a human being and the least expected from a democratic country like Norway. Ethiopia is currently in a dangerous wave of public unrest.

በዶ/ር ታደሰ ክስ የቀረቡ ማሰረጃዎች ውድቅ ተደረጉ-በፕሬስ ጉዳይ የተጣለባቸውም እገዳ ተነሳላቸው!


#አስራ ሁለት አባላት ያለው ሸንጎ[ጁሪ]የክሱን ጭብጥ ዛሬ መስማት ጀመረ!
#በከሳሹ የእንግሊዝ መንግስት አቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ጥርጣሬ በሎንደን ተከሰው ጉዳያቸውን መከታተል የጀመሩት ዶ/ር ታደሰ ብሩ በዛሬው እለት ችሎት ውሎዋቸው ዳኛው የተጣለባቸውን ለፕሬስ የመግለጽ እገዳ እንዳነሱላቸው ባለደረባችን ከችሎት ዘግባል። በትናትናው የችሎት ውሎ በአቃቤ ሕግ በኩል የክሶቹ ማስረጃ መረጃዎች በማለት ለችሎቱ የተሰጠውን ከ300ገጽ በላይ ዶሴ ዳኛው “ለማስረጃነት ለመቀበል ይዘቱ ብቁ አይደለም” በማለት ውድቅ እንዳደረጉት ባለደረባችን ገልጻል።Image may contain: 1 person
በትናትናው ውሎ የተመረጡት ስድስት እንስቶችና ስድስት ተባእት የሸንጎ [ጁሪ ]አባላት ዛሬ ከጣቱ 11:20ሰዓት በሃላ በአቃቤ ሕጉ ሲነበብ የነበረውን ክስ ማዳመጥ መጀመራቸው ተገልጻል። በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ በእንግሊዝ መንግስት አቃቤ ህግ የተመሰረተውን ክስ እየተመለከተ ካለው ስናርስብሩክ ክራውን ፍርድ ቤት ሁለተኛ ቀን ውሎን ባልደረባችን ከስፍራው የዘገበልንን ሪፖርታዥ እንደሚከተለው አቅርበናል።
**ከ900በላይ ገጽ ያለው የክስ ዶሴ ለ12ቱ ሸንጎ አባላት ታድሎ መነበብ ተጀምራል- ዶ/ር ታደሰ ብሩ በከሳሽ አቃቤ ህግ ጀምሰን ከሳሽነት ከታህሳስ 2015 እስከ 2016 ድረስ ለበርካታ ግዜያቶች ወደ ኤርትራ በመመላለስ በለንደን የጸረ-አሸባሪ ፖሊስን እይታ ለመሳብ ችለዋል በማለት ከሳሹ የክሱን መነሻ ለማሳያት የጣረ ሲሆን “በመስከረም ወር ላይ ከኤርትራ ሲመለሱ ሂትሮው ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ በተያዙበት ሰዓት በርካታ ዶሴዎችን በእጃቸው ለማግኘት ችለናል”በማለት ለችሎቱ አስረድታል።
እንደ ከሳሽ አቃቤ ህግ ክስ አመሰራራት በግሪንዊች ዩንቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ሌክቸረር ከሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ስራና ሙያ ጋር ተያያዥነት የሌለው ዘርፈ ብዙ ዶሴ ከአስመራ ሲመለሱ በእጃቸው[በላፕ ቶፓቸው]መገኘቱን ገልጾ ዶሴውም ከአመጽና ሽብር ተግባር ጋር የተያያዘ በመሆኑ የኤርትራን ጉዞዋቸውን ምክንያት እንደተረዳ በመግለጽ ለችሎቱ አስደምጣል። ይህ የአቃቤ ህግ በዶ/ር ታደሰ ብሩ እጅ ላይ የተገኘው ዘርፈ ብዙ ዶሴ ምሁሩ ወደ ኤርትራ የሚመላለሱበት ዋና ምክንያት ብሎ እንዲያምን እንዳደረገው ከአገላለጹ መረዳት የተቻለ ሲሆን አገኘሁ ባለው ዶሴ ላይ ተመስርቶ ዶ/ሩን በ2000 እና በ2006 ላይ በጸደቀው የእንግሊዝ ጸረ ሽብር ህግ አንቀጽ 58እና 8መሰረት የሽብርተኛነት ክስ ሊከፍትባቸው እንደቻለ መረዳት ተችላል።
“በአንድ ወቅት እጅግ ወዳጃሞች የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ዛሬ የመረረ ጠላታሞች ሆነው ሳለና ዶ/ር ታደሰ ብሩም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሳለ ምን ሊያደርግ ነው ወደ አስመራ ሲመላለስ የከረመው”በማለት አቃቤ ህጉ ይጠይቅና እራሱ ሲመልስም “ምክንያቱም ዶ/ሩ በእጃቸው በተገኘው ዶሴ መሰረት በኤርትራ ያሸመቀውን ጸረ የኢትዮጵያ መንግስት አማጺን ለመርዳት ነው” ሲል እራሱ ይደመድማል።
አቃቤ ህግ በዶ/ሩ የግል ላፕቶፕ ውስጥ ተገኘ ያለው ዘርፈ ብዙ ዶሴ ከኢንተርኔት ላይ የተሰበሰበ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ለአንድ አማጺ ሃይል በወታደራዊ ስልትና ስልጠና፣በተለያየ ጦር መሳሪያ፣አደረጃጀትና አወቃቀር ደረጃ ጠቂሚ ናቸው ብሎ አቃቤ ህግ እንዳመነ በመግለጽ ዶ/ሩ ላይ የአሸባሪነት ክስ መክፈቱን ሲገልጽ ዶ/ር ታደሰ ብሩ አባባሉን በማስተባበል ሀሰት ሲሉ እራሳቸውን ተክላክለዋል።
አንድ የንግሊዝ ሚይል የተባለ ጋዜጣ ዛሬ ባወጣው ዜና ላይ አጠቃላይ የአቃቤ ህግን መክሰሻ ፋይል በመጠቀም ለአንባቢያን ሚዛኑን የሳተ ዘገባ ያቀረበ ቢሆንም ጋዜጠኛው የዶ/ሩን አሸባሪነትን ክስ ባስተጋባበት ላይ ‘Certainly, there was nothing to suggest a man involved in political violence or, to put it another way, a man involved in terrorism.በመሰረቱ ዶ/ሩ በማንኛውም አመጽም ሆነ ሽብርተኝነት የተሳተፉበት ሁኔታ መኖሩ መናገር አይቻልም ያልም ሲል ስለክሱ ዘግባል።
በችሎቱ የነበረው ባለደረባችን እንደዘገበው ከሆነ እንግሊዚዊው አቃቤ ህግ ጀምሰን አቀራረቡና ክሱን ያዋቀረበት ጭብጥ በኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ የሚያካሂደውን ክስና የማጥቃት ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ እየታየ ሲሆን ክሱ የእንግሊዝ መንግስት ነው ወይስ የኢትዮጵያ ክስ ነው ያሚያስብል እንደሆነ ከሂደቱ መረዳት ተችላል።
እስከአሁን በቀረቡትና በተሰሙት የአቃቤ ህግ ክሶችና ማስረጃዎች ላይ በአንዱም ገጽም ሆነ በአንዲትም ቃል ቢሆን በዶ/ር ታደሰ ብሩ የተፈጸመ ተብሎ የተነገረ የሽብር ጥቃትም ይሁን ተግባር እንደሌለ ማረጋገጥ ተችላል። ችሎቱ ነገም የሚቀጥል ሲሆን አቃቤ ህግ ለሸንጎዎቹ ዛሬ ማሰማት የጀመረውን የክሱን ዝርዝር ማሰማት ይቀጥላል ተብላል።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ በ2009 ወደ እንግሊዝ ሀገር የተሰደዱ ምሁርና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ የጥገኘት[ስደተኛነት]መብት ተሰጥቶዋቸው በግሪንዊች ዩንቨርሲቲ ኢኮኖሚክስና ቢዝነስ ዲፓርትመንት ውስጥ በሌክቸረርነት እየሰሩ ያሉ መሆናቸውም በችሎቱ ተገልጻል።

የአግ7 አርበኞች ለአጋዚ ወታደር አገልግሎት ሊውል በነበረ ነዳጅ ላይ ጥቃት ፈፀሙ

ህወሓት በጎን ለይምሰል ሱዳን ወረረችን እያለ በጓሮ በር እየተሞዳመደ ከሕዝብ ደብቆ ሊያስገባው የነበር ሸቀጥም በአርበኞች ወድማል ፡፡ የአግ7 አርበኞች እጅግ ጥበብ በተሞላበት ኦፕሪሽን ዛሬ ህዳር 26 2010 ዓ/ም ንጋት 10:40 ላይ በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር አካባቤ በህወሓት አጋዚ ታጅቦ ከሱዳን ካርቱም በመነሳት ወደ ኢትዮጲያ በመግባት ለአጋዚ ልዬ ኮማንዶ መቀሳቀሻ ሊሆን የነበረን በበርካታ ተሽከርካሪዎች የተጫነን ነዳጅ እና ሊላ ሸቀጦች ሙሉ በሙሉ አርበኞች አውድመውታል፡፡ በአሁኑ ሳዓት ሕዝብን ለማምታታት እና እየተደረገ ያለውን የነፃነት ትግል አቅጣጫ ለማስቀየስ በህወሓት አቀነባባሪነት የሱዳን ወታደሮችን ወደ ኢትዮጲያ በማስገባት ግዛታችንን በማስያዝ የተወረርኩኝ ፕሮፕጋንዳ እየነዛ ባለበት ወቅት ጨለማን ተገን በማድረግ ከሱዳን ነዳጅ እና የተለያዩ ሸቀጦችን ከህዘብ በመደበቅ እያስገባ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም ይህ ዘረኛ ስርዓት በአሁኑ ጊዜ ንፁሀን ዜጎችን በጠራራ ፀሀይ በአልሞ ተካሹ ቅልብ ኃይል በሆነው በአጋዚ ክፍለ ጦር እየጨፈጨፈ ይገኛል ለዚህ ገዳይ ኃይል ህወሓት የሚፈልገውን ሁሉ በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን ፡ ከሚቀርብለት ትልቅ ነገር አንድ እና ዋናው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ ነው ፡ ይህን የተረዱ አርበኞች ከአሁን ቀደምም ከካርቱም ተነስቶ ጭልጋን በማለፍ ጎንደር ሊገባ የነበረን ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ማውደማቸው ይታወሳል ፡፡ ዛሬም እጅግ አስደናቂ በሆነ ተጋድሎ በድጋሚ ታላቅ ስራ ሰርተዋል ፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሳል ፡ አርበኞችም በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል ፡፡ 
ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን እንገልፃለን ፡፡ 
ድል ለሕዝብ !!! 
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጵያ ዕዝ ፡፡No automatic alt text available.

Friday, December 1, 2017

ህዝባችን ለፍትህ እያካሄደ ያለውን ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ህወሃት የሚሸርበውን ሴራ ማምከን ጊዜ ሊሰጠው የማይገባው ተግባር ነው። (አርበኞች ግንቦት 7)

December 1, 2017
በመንደርና በዘር የተሰባሰቡ የትግራይ ልጆች ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወይም የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ሥም ተደራጅተው በነፍጥ የአገራችንን በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ላለፉት 27 አመታት ከኛ ወዲያ ላሳር በሚል እብሪትና ትዕቢት እያንዳንዱን ማህበረሰብ አዋርደው ገዝተዋል ፤ አሁንም እየገዙ ነው።

ህወሃት ህዝባችንን እያፈነ ፤ እየገደለና እያሰደደ ለዚህ ሁሉ ያህል ዘመን ሊገዛ የቻለው እያንዳንዳችንን በባህል ፤ በቋንቋና በሃይማኖት እየከፋፈለ እንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው “እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ፤ እርስ በርስ መተላለቅ አይቀሬ ነው” እያለም ትንቢት አይሉት ሟርት በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች እና በጥቅም ባሰባሰባቸው ጋሻ ጃግሬዎቹ አማካይነት ሲሰብከን ኖሮአል።
ሆኖም ግን ኦሮሚያ ውስጥ የዛሬ ሶስት አመት የተቀሰቀሰው እና ወደ አማራና ሌሎች ያገሪቱ ክፍሎች የተዛመተው የህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ ህውዓት ሃያ ሰባት አመት ሙሉ ገንብቼዋለሁ ብሎ የተማመነበትን ይህንን የጥላቻና የልዩነት ግንብ ሙሉ በሙሉ የናደና የህዝብን አንድነት ያረጋገጠ እንቅስቃሴ እንደሆነ ተረጋግጦአል። ዛሬ በሁሉም የሐገራችን ክፍል የሚገኘው ህዝብ የወያኔን የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት ለማስቀጠል የሚፈጸምበትን አፈናና ግዲያ ተቋቁሞ ከያለበት Down Down ወያኔ! ወያኔ ይውደም ! ወያኔ አይገዛንም ! የሚል መፈክሮችን በጋራ እያሰተጋባ ያለው የክፍፍልና የልዩነት ግንብ መፍረሱን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑ አያጠራጥርም ።
በተለይ ለህውሀት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ቅኝት እንዲመች ተደርጎ በተቀነባባረው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለአመታት በቅኝ ገዥነት እና በትምክህተኝነት የማሸማቀቅ ዘመቻ ሲካሄድበት የኖረው የአማራ ህዝብ ጎንደር ላይ የነ በቀለ ገርባን ፎቶግራፍ ይዞ በመውጣት “በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የኛም ደም ነው!” የሚል መፈክር ካሰማበት ዕለት ጀምሮ በመላው ኦሮሚያ እየተስተጋባ ያለው “አንከፋፈልም እኛ አንድ ነን” ድምጽ ህውሀት የቆመበትን የድጋፍ መሠረት እንዲደረመስ ከማድረግ አልፎ ፍርሃትና ድንጋጤን በድርጅቱ ውስጥ እንዲነግስ ዓይነተኛ ምክንያት ሆኖአል ። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ የተዘፈቀው ህውዓት የመንግሥት ሥልጣን ከእጁ እንዳያመልጥና የአገዛዝ ዕድሜው እንዲራዘም የመጨረሻው የሚመስለውን ሙከራ ለማካሄድ በግለሰቦች መካከል የሚነሱ ግጭቶችን ጭምር ወደ ብሄር ግጭት ለማዞር እየተቅበዘበዘ እና አቅም የፈቀደለትን ሁሉ ሴራ እየሸረበ ይገኛል።
ለአብነት ያህል በኢትዮጵያ ሱማሌና በኦሮሚያ አዋሳኝ ቦታዎች የሚኖሩትን ዜጎች ለማጋጨት የአገዛዙ ደህንነትና ከርሱ ጋር በቅርበት የሚሠሩ የክልሎቹ ሹሞች የተጫወቱትን ሚና ፤ በዝዋይ አንድ የወላይታ ተወላጅ ከአንድ ኦሮሞ ተወላጅ ጋር መጋጨቱን ተከትሎ ግጭቱ የብሄር መልክ እንዲይዝ ለማድረግ የተሞከረው ሴራ እና ባለፈው ሳምንት አጋማሽ አርሲ ነገሌ ላይ በግለሰቦች መካከል በተነሳው ጠብ አንድ ግልፍተኛ ግለሰብ ሌላኛውን ተኩሶ በመግደሉ ግጭቱን የአማራና የኦሮሞ ለማስመሰል የተሄደበት ርቀት ተጠቃሽ ናቸው። በእንዲህ አይነት የህወሃት መሰሪ ተንኮል ከዚህ ቀደም በአኝዋክና በኑዬር ፤ በአፋርና በትግራይ ፤ በወላይታና በሲዳማ ፤ በጉጂና በኮንሶ ፤ ቤንሻንጉል እና ኦሮሚያ ውስጥ “በአካባቢው ተወላጆችና መጤ” በተባሉት መካከል ሆን ተብሎ በተቀሰቀሱ ግጭቶች ምን ያህል የሰው ህይወት እንደጠፋ እና ምን ያህል ንብረት እንደወደመ ይታወቃል።
በእስከዛሬው የህወሃት የመከፋፈል ሴራ አልበገር ብሎ በጋራ በቆመው ህዝብ መካከል እንደገና የጥርጣሬና የስጋት መንፈስ ለመዝራት በደህንነት መስሪያቤቱ በኩል እየተካሄደ ካለው ሴራ በተጨማሪ ኦሮሚያ ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ህዝባዊ እምቢተኝነት አቅጣጫ ለማስለወጥ ሠልፈኛው ከቤቱ ይዞት ያልወጣቸውን መፈክሮችና አገዛዙ “በሽብርተኝነት” ከፈረጃቸው ድርጅቶች የአንዱ የሆነውን ድርጅት የትግል አርማ አሰርጎ በማስገባት የዘመናት ብሶትና በደል አንገብግቦት አደባባይ የወጣውን ህዝብ በምን ለመወንጀል እንደተሞከረም ተመልክተናል። የዚያ ውንጀላ ዋና ዓላማ ህወሃት እስከ ዛሬ በሚተማመንባቸው የመሳሪያ እና የጉልበት የበላይነት ሊጨፈልቅ ያልቻለውን የቄሮ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሌሎች ዘንድ በጥርጣሬ ዓይን እንዲታይ እና ድጋፍ እንዳይቸረው ለማድረግ በመሞከር የተቃውሞ ትግሉን ለመግደል ወይም ለመቆጣጠር እንደሆነ መገመት አያስቸግርም ።
በአርበኞች ግንቦት 7 የፖለቲካ ግምገማ ህወሃት ህዝባችን ለፍትህና ለእኩልነት ብቻ ሳይሆን ለራሱ ክብር እና ልዕልና የጀመረውን ትግል ለማስቆምም ሆነ ለመቆጣጠር የሚያስችለው አቅም ላይ እነዳልሆነ ተረጋግጦአል። ከአሁን ቦኋላ ያንን ያጣውን የበላይነት መልሶ ማግኘት የሚችልበት መንገድም አብቅቶአል ብሎ ንቅናቄው ያምናል። ይህንን ጸሃይ የሞቀውንና አገር ያወቀውን እውነታ ባለመቀበል ህወሃት ሊሄድበት ያሰበው መንገድም ሆነ ሐገራችን እንዲገጥማት የሚፈልገው አደጋ ህወሃትን እንደ ድርጅት ፤ ጉምቱ ባለሥልጣናቱንም እንደ ብቸኛ ተጠያቂ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል አደጋ ያዘለ መሆኑን ህወሃት የተረዳው አይመስልም።
አርበኞች ግንቦት 7 የህወሓት የግፍ አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ህዝብ እያካሄደ ያለዉን ትግል ለማጠናከር እና እየተከፈለ ያለዉን መስዋዕትነት ከዉጤት ለማድረስ በሙሉ ሃይሉ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በእብሪተኞችና በመንደርተኞች የተቀማውን ነጻነት ለማስመለስ ብሎም በነጻ እና ገለልተኛ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በሚቋቋም መንግሥት ለመተዳደር ህዝባችን እያካሄደ ያለው ትግል ከአሁን ቦኋላ በምንም አይነት የህወሃት ሰራሽ ሴራ እንዳይጨናገፍ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ለነጻነቱ ቀናዒ ከሆነው ህዝባችን ጎን በመቆም ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያስታውቃል።
የህዝብ ወገን የሆናችሁ የሐገሪቱ መከላኪያ ሠራዊት ፤ የፖሊስና የደህንነት አባላት የመንግሥት ሥልጣን የጨበጠው ህወሃት የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም ሲል በሚሸርበው ሴራ የገዛ ወገኖቻችሁን ለመግደል ፤ ለማሰርና ለማሰደድ የሚሠጣችሁን ትእዛዝ እንቀበልም በማለት ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙና የህዝብ አለኝታነታችሁን በተግባር እንድታረጋግጡ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ESAT News Analysis on Tplf Turmoil November 3012017

Thursday, November 30, 2017

Support ESAT by Signing Up for Monthly Subscription - Ethiopia

Tarik Yifreden ሻምበል በላይነህ

የዛሬ የዕለተ ሓሙስ ህዳር 21 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን ዜና .(አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

* በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች እንደቀጠሉ መሆኑ ተዘገበ
* ህወሓት የሥልጣን ሹም ሽር ማድረጉ በይፋ ተገለጸ
* በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንደገና ባገረሸው ግጭት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ታወቀ
፠የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 23 - 2010 ዓ/ም አውሮፓ ቤልጅም ውስጥ ኢትዮጵያ ወድየት በሚል ርዕስ ስር ድልድይ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ማህበር አንድ የመወያያ መድረክ አዘጋጅቷል ይህንን መድረክ አስመልክቶ ከተሳታፊዎቹ አንዱ የሆነውን አቶ አናንያ ሶሪ አነጋግረነዋል እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን፡፡
www.patriotg7.org
Image may contain: sky and outdoor

መሀል ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)


ፍርድ ቤት ውስጥ ህዝቡ በእንባ ይራጫል። አንድ ሰውነቱ በግርፋት የተዘለዘለ እስረኛ ልብሱን አውልቆ ''እዩት ሰውነቴን። አኮላሽተውኛል። ዘር እንዳይኖረኝ አድርገውኛል።'' እያለ ሲቃና ለቅሶ ባሸነፈው ድምጽ ይማጸናል። ''የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ''ም አለ። ፍርድ ቤቱ በሀዘን ክው ብሎ ቀረ። ሁሉም ተላቀሰ። አሁንም እዚያው አዲስ አበባ ወጣቷ ንግስት 10ሩም የእጆቿ ጥፍሮች ተነቅለው በኪሶቿ ይዛለች። የደረሰባት ቶርቸር መልኳን አገርጥቶታል። በጉጠት የተነቀሉት ጥፍሮቿን እንድትይዛቸውም አልተፈቀደም። በኋላም በህወሀት ገራፊዎች ተነጥቃለች። የሻሸመኔዋ ሸጊቱም ትናገራለች ''ጆሮዬ እስኪደማ ድረስ ተደብድቤ ተጎድቷል።ግራ እጄ ታሟል። በእግራቸው ነበር የሚረግጡኝ። ጸጉሬን እየጎተቱ ነበር የሚደበድቡኝ።''
ሁለቱ የዋልድባ መናኞች በማዕከላዊ የደርሰባቸው ስቃይና ድብደባ ቃላት አይገልጸውም። የህወሀት ደህንነቶች ሌሊትን አልፈዋቸው አያውቁም። እኚህን ዓለምን የተጠየፉትን መናኞች ዘቅዝቀው በመደብደብ፣ በመዝለፍ፣ በማንቋሸሽ ይህ ነው የማይባል ስቃይ እያደረሱባቸው ነው። ልብሰ ተክህኖአቸውን፡ ቆባቸውን እንዲያውልቁና የእስረኛ ዩኒፎርም እንዲለብሱ ነው ግርፊያውና ስቃዩ። ከዚህ ቀደም አበበ ካሴ አስሩንም ጥፍሮቹን በጉጠት ተነቅለዋል። ወ/ሮ እማዋይሽ ጡታቸው በኤሊክትሪክ ሽቦ ተተልትሏል። ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች በማዕከላዊ ተኮላሽተዋል። ተቀጥቅጠዋል። የስቃይ መዓት ቆጥረዋል። ከትላንት እስከ ዛሬ።
ሰሜን ኢትዮጵያ- መቀሌ
ዝሆኖቹ ረጅሙን ስብሰባ ተቀምጠዋል። የሚያስጨንቃቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ አይደለም። ጓዛቸውን አስጠቅልሎ ለሁለት ወራት መቀሌ የከተታቸው ስለኢትዮጵያውያን ተጨንቀው ተጠበው አልነበረም። የትግራይን የበላይነት ለተጨማሪ ዓመታት አስጠብቀን እንዴት እንቆያለን? የሚለው ላይ በአካሄድ ተለያይተው እንጂ። 77ቢሊየን ብር ዱቄት ያደረገውን አባይ ጸሀዬን መርቀው፡ አባይ ወልዱን ረግመው ዝቅ አድርገዋል። የማዕከላዊ ሰቆቃ እስር ቤት አዛዥ፡ ናዛዥ፡ ገራፊ አስገራፊ፡ የሆነውን ጌታቸው አሰፋን ሸልመው አዜብን ሸኝተዋል። በየነ ምክሩን አዋርደው፡ ጌታቸው ረዳን ከፍ አድርገዋል። ጉልቻ ቀያይረው፡ ከዝንጀሮ መሀል አንዱን ሊቀመንበር መርጠው፡ ወንበር ተለዋውጠው ከጨረሱ በኋላ ለኢትዮጵያ ህዝብ ''የምስራች፡ ምስር ብላ'' ሊሉት ተዘጋጅተዋል።

Wednesday, November 29, 2017

ESAT Daily News Amsterdam November 29,2017

Ethiopia: Thousands of university students left campus as protest continues ESAT News (November 28, 2017)

Protest by university students against the regime in Ethiopia continued as about 35,000 students of the Haromaya University left their campuses.
The students of Haromaya University had left their campuses a week ago but returned as the Aba Gedas, traditional leaders of the Oromos, promised to broker a deal and obtain a favorable response from authorities.
The students demand that the spy network of the regime in their campus should be abolished. Students say the “peace forum” as it is euphemistically called, is a group set up by the regime to spy on students.
Meanwhile, security forces locked down Jimma University to prevent students from leaving their campus.
In another development residents of Sawla town in Gamu Gufa Zone had burnt down the local tax office in protest against tax hikes. The locals say they would not give their money to a regime that tortures and kills citizens.
In the eastern commercial town of Aweday, residents blocked highways while in Wollega, in the towns of Mendi and Bigg, protesters demand regime’s army to leave their towns. They accused that the army had carried out extrajudicial killings.

Monday, November 27, 2017

ህወሀት ጉልቻ እየቀያየረ ነው። (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)


የፊት ለውጥ ይዞ ሊመጣ መሆኑ ታውቋል። አዜብ መስፍን ባፋንጉሎ ተብላለች። የኢትዮጵያን ህዝብ ደም የመጠጠው ኢፈርት የተሰኘው ድርጅት የንትርኩ ማጠንጠኛ ይመስላል። እነአዜብና በየነ ምክሩ ከዚሁ ድርጅት ጋር በተያያዘ አይናቸው ደም በለበሰባቸው በእነስብሃት ነጋ ብጫና ቀይ ካርድ ተሰጥቷቸዋል። እነስብሃት ለጊዜው በለስ ቀንቷቸዋል። የመለስ ሌጋሲን ከመለስ ጋር እንዲቀበር የፈለጉት እነስብሃት የሌጋሲውን አቀንቃኞች በጠረባ እያሏቸው ነው። ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መግለጫው መቅደሙ ግን ገና ጦርነቱ ያላበቃ መሆኑን ያሳያል።
እነኣዜብ ኢፈርትን ለነስብሃት አስረክበው ቤታቸው ይገባሉ? የመለስ ዜናዊ አምላኪ የሆነው ሳሞራ የኑስ ምን ብሎ ይሆን? ኢፈርትን የተቆጣጠረ ሻምፒዮን ይሆናል። የኢኮኖሚ ጡንቻ የሚሰጠው ኢፈርት ለፖለቲካው የበላይነት የጀርባ አጥንት መሆኑን አቦይ ስብሃት ልቅም አድርገው ያውቁታል። እናም የመለስን ሌጋሲ ከነአስጠባቂዎቹ መንግሎ ለመጣል መንገዱን በኢፈርት ጀምረውታል። በፖለቲካው ቀጥለዋል። እነአዜብ እጃቸውን አጨብጭበው ኢፈርትን ካስረከቡ የመልስን ሌጋሲ ብቻ ታቅፈው ይቀራሉ።
ፈረንጆቹ the bottom line ይላሉ። ዋናው ጉዳይ እንደማለት ነው። እናም ዋናው ጉዳይ የአዜብ መወገድና የስብሃት ማንሰራራት አይደለም። ጉልቻ ቢቀያየር ትርጉም የለውም። ወጥ አያጣፍጥም። ኢትዮጵያን አይቀይርም። ሌሎችንም ቱባ ባለስጣናት በማባረርና በእስር የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በመፍታት ይህቺን የምጥ ጊዜ ለመሻገር ህወሀት ተዘጋጅቷል። ፊት በመቀየር፡ ጉልቻ በመለወጥ ህወሀት የሚድን ከመሰለው ተሳስቷል። ህወሀት ከነግሳንግሱ፡ ከነኮተቱ፡ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ፡ አንድም ትራፊ ሳያስቀር ካልተወገደ በቀር ለውጥ አይኖርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናፍቀው ያንን ነው።Image may contain: 1 person

Bekebero Gudguad ሻምበል በላይነህ

Enough hereafter by Hanisha Solomon

Sunday, November 26, 2017

የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላትና የብአዴን ማአከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አለምነው መኮነን መካከል ግጭት መፈጠሩ ታወቀ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ተኛ ዙር 3ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ተኛ መደበኛ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በባህርዳር የተጀመረ ሲሆን ከጅምሩ አፈ ጉባኤው ከአቀረቡት አጀንዳ በተጨማሪ የምክር ቤት አባላት በአጀንዳነት መያዝ አለባቸው በማለት በርካተ ርዕሰ ጉዳዬችን በማንሳታቸው በተለይም በኢትዮ ሱዳን ድንበር ፡ በትግራይ እና በሰሜን ጎንደር በኩል ያለው የአማራ ድንበር ፡ በትግራይ እና በወሎ በኩል ያለው የአማራ ደንበር ፡ በእኩል ተጠቃሚነት በኩል ከኢንዱስትሪዎች እና ኢንቨስትመንቶች ፡ እንዲሁም ከህወሐት የበላይነት ወዘተ ጋር የመሳሰሉት በአጀንዳነት ሊያዙ ይገባል የሚሉ ጉዳዬች በመነሳታቸው በስብሰባው አዳራሽ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቷል ፡፡ ከዚያም የብዓዴኑ ሹም ገዱ አንዳርጋቸው ጣልቃ በመግባት መጀመሪያ በቀረቡት የስራ ክንውኖች ላይ እንወያይና በቀጣይ በቀረቡት ነጥቦች እንመክራለን በሚል በሰነዘረው ሀሳብ ስብሰባው መጀመር ከነበረበት ሰዓት እጅግ ዘግይቶ ተጀመረ እንዲያም ሆኖ በትምርት ዙሪያ በቀረበው ሪፖርት ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ ፡ ይሄን መረጃ ለሌላ ጊዜ እናቆየውና በምክር ቤቱ አባላትና በአለምነው መኮነን መካከል ግጭት ወደ ተፈጠረበት መረጃ እንለፍ በማለት ተስማምተው ፡ የምክር ቤቱ የቀን ውሎ እንዳበቃ 12:00 ሰዓት ሲሆን ከሰሜን ጎንደር ዞን ፡ ከሰሜን ወሎ ዞን እና ከዋግ ህምራ ዞን የመጡትን የምክር ቤት አባላት ከአዳራሹ እዲቆዩ በማድረግ አፈ ጉባኤውና ገዱ አንዳርጋቸው ከመድረኩ ወርደው በመድረክ ወንበር ላይ አለምነው መኮነን እና ምግባሩ ከበደ በብአዴን ውስጥ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ወኪል ሆኖ እየሰራ ያለው ተቀመጡ ፡፡ ከዚያም አለምነው እናንተን ነጥለን ወደ ኃላ እድትቆዩ ያደረግነው በጥዋቱ የምክር ቤት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከድርጅታችን ብአዴን አቋም ውጭ የሆኑ ሀሳቦችን ስታነሱ ሰምተናል ፡ እናንተ ወደ እዚህ ምክር ቤት የመጣችሁት ብአዴንን ወክላቹሁ እና ህዝቡም ለብአዴን ድምፅ ሰጥቶ ስለመረጣቹሁ ነው በመሆኑም በድርጅታችን የዲስፕሊን መመሪያ መሰረት ነው ልትንቀሳቀሱ የምትችሉት ፡ በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ባሉ ድንበሮች የነበሩ ችግሮች ሁለቱ ድርጅቶች እና የአካባቢው ህብረተሰብ ተወያይቶ መፍትሔ የሰጠበትን አሁን ከዚህ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ማንሳት ተገቢ አይደለም ፡ ከሱዳን ጋር ያለውም ቢሆን ፀረ ሰላም ኃይሎች ከሚያራግቡት ውጭ ነው ሰላማዊ ነው ወዘተ እያለ እነዚህን የምክር ቤት አባላት ለማሳመን ቢሞክርም የምክር ቤት አባላቱ ንግግሩን አቋርጠው አንድ የምክር ቤት አባል ድንበርን በተመለከተ የትኛው ህዝብ ነው የተወያየውና የተስማማው ? ህወሓት ይዞት የቀረበውን አጀንዳ ካልተቀበልንም በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተፈርጀን በአሸባሪነት እንጠየቃለን ፡ በዚህ ሁኔታ የሁለቱ ድርጅቶች ግንኙነት መሻከር የለበትም ፡ወዘተ... ተብሎ ማስፈራሪያ ቢሰጥም ይሄን ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው የተከራከሩትን በማሰር በኃይል የተሰጠ ነው በማለት ተናገሩ ሌላም የምክር ቤት አባል በወሎ በኩል ምን መፍትሔ ሰጥታቹሁ ነው እንደዚህ የምትሉት ? እኛ እኮ ከህዝብ ጋር ነው ያለነው ህዝቡ የሚለውን ነገር በሙሉ በቅርበት የምንሰማው እኛ ነን በማለት ሲናገሩ ጉዳዩ ወደ ስድብና ንትርክ ሲያመራ ምግባሩ ከበደ ደግሞ " ይሄ አይነት ሀሳብ ከናንተ የመጣ አይደለም ሁላቹሁም የምትሉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አሸባሪው ቡድን ሀሳብ እና የትምክህተኞች ሀሳብ ነው ይሄ ደግሞ በህግ ያስጠይቃል " በማለት ሲናገር እኛ የምንለውን እናውቃለን እስከ መቼ ባሪያዎች ሆነን እንቀጥላለን ማስፈራራቱን እናየዋለን በማለት ቀድሞም ወደ ኃላ ቅሩ ብላቹሁ እኛን ነጥላቹህ ማስቀረታችሁ ህገ ወጥ ነው እኛ ተጠሪነታችን ለመረጠን ህዝብ እንጂ ለናንተ አይደለም በማለት መድረኩን ረግጠው ወጥተዋል ፡ አሁን ባለው ሁኔታ ውጥረቶች በርትተዋል፡፡

Support ESAT by signing up for monthly Subscription

Saturday, November 25, 2017

ESAT Latest News Sat 25 NOv 2017

በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያቤት እና በጄነራል ሳሞራ የሚመራው መከላከያ መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት በግልጽ የሚታይበት ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል። በመከላከያ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚያቀርበው መረጃ፤ ታእማኒነት የሌለው ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማል። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል የሚወስዳቸው እርማጃዎች ቀጥታ ከጄነራል ሳሞራ ጋር እንዳጋጨው መረጃዎች ያመለክታሉ። Image may contain: 2 peopleጄነራል ሳሞራና የእሱ ደጋፊ የሆኑ የጦር አዛዦችን ለመቆጣጠር በሚል አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ለሱ የሚታዘዝ መረቦችን ለመዘርጋት ያደረገውን ሙከራ ተከትሎ በሁለቱ የህወሃት ቁንጮዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ ያለመግባባት ተፈጥሯል። በመከላከያ ውስጥ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ ጥሩ ምልከታ አላቸው የሚባሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ላይ በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ስር የሚገኘው በመከላከያ ጸረ መረጃ መምሪያ አማካኝነት ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል። በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጄነራል ሳሞራ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ በሚል ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ለማሸማገል ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን ከመከላከያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሚመራው የደህንነቱ ዋና መስሪያቤት ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ይታወቃል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል አሁን በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ከሆኑት ሜ/ጄነራል ገብሬ ዲላ በፊት በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ እንደነበሩ ይታወሳል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከጄነራል ሳሞራ ጋር ባላቸው አለመግባባት ምክንያት ነው ከዚህ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገው። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋና ጄነራል ሳሞራን ለማስታረቅ ያደረጉት ሙከራም የከሸፈው መጀመሪያውኑ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል እና ጄነራል ሳሞራ የሚግባቡ ባለመሆኑ ነው። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ የሚኖረውን ተጽኖ ለማስፋት ከሚጠቀምባቸው ሰዎች አንዱ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል እንደሆነ ይነገራል። ጄነራል ሳሞራ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ከደህንነቱ ዋና መስሪያቤት ጋር ያላቸውን ቅርርብ ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል ከዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ከደህንነቱ መስሪያ ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል። አቶ ደብረጺዮን መከላከያው ውስጥ ባለው በጎ ግንኙኑነት የተነሳ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋ በዶ/ር ደብረጺዮን በኩል ነው፤ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀሰው ሲሉ በደህንነት ውስጥ ያሉ አካላት ይገልጻሉ። ዶ/ር ደብረጺዮን በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ምክንያት በማድረግ አቶ ጌታቸው አሰፋን እና ጄነራል ሳሞራን ለማግባባት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ ታውቋል። ጄነራል ሳሞራ አቶ ጌታቸው አሰፋ መከላከያን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም በሃይለ ቃል መናገሩ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ። በተጨማሪም የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚያቀርበው ሪፖርቶች በአብዛኛው በውሸት የተሞሉ በመሆናቸው ከደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚመጣን ማንኛውም ሪፖርት በጥንቃቄ እንዲታይ ጄነራል ሳሞራ ትእዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ አቶ ጌታቸው አሰፋን ያስቆጣ ጉዳይ ሆኗል። በአሁን ሰአት ከፍተኛ የጦር አዛዦች ከደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚመጣን ማንኛውንም የመረጃ ሪፖርት ከመጠቀም ይልቅ በመከላከያ ስር ባለው የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ በኩል የሚመጡ መረጃዎች ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ሆኗል። በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ፤ የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የስራ ክልል በሆነው በሲቪል መረጃ ስራዎች ውስጥ መግባቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ለተፈጠረው ያለመግባባት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለውን ያለመግባባት ለመፍታት በሚል ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም እስካሁን ድረስ በጄነራል ሳሞራና በአቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል ያለው ግንኙነት እንደሻከረ ይገኛል።

Thursday, November 23, 2017

በኮማንደር ደሳለኝ ላይ ለተፈጸመው ግድያ አርበኞች ግንቦት7 ሃላፊነቱን ወሰደ (ኢሳት ዜና፣ ህዳር 14 ቀን 2010 ዓም )

በባህርዳር ከተማ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ በሆነው ኮማንደር ደሳለኝ ልጃለም ላይ ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4:45 በመኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ለተፈጸመው ግድያ ንቅናቄው ሃላፊነቱን ወስዷል። ግንባሩ ባወጣው መግለጫ የፖሊስ አዛዡ በከተማው ተካሂዶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ከህወሀት የተሰጠውን መመሪያ በማስፈጸም ለበርካቶች ግድያና ስቃይ ተጠያቂ ነበር።
የኮማንደሩ አስከሬን ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ምርመራ ቢደረግለትም እጅግ ጥበብ በተሞላበት ድምፅ በሌለው መሳሪያ ጭንቅላቱ ላይ ሁለት ቦታ ተወግቶ ሊሞት ችሏል ። ኮማንደሩ በ ብአዴን 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ከልዩ እንግዶች ጋር የራት ግብዣ ላይ ተገኝቶ ካመሸ በሁዋላ የስንብት እርምጃ እንደተወሰደበት ግንባሩ ገልጿል።
ግንባሩ አክሎም፣ የመከላከያ የደህንነት የከተማ ምድብ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረ፣ የህወሓት የደህንነት አባል ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4:15 ሲሆን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 04 ከአንድ ጭፈራ ቤት ሲዝናና በነበረበት ሰዓት በአርበኞች አባላት ታፍኖ ከተወሰደ በኃላ በባህርዳርና በመሸንቲ ከተማ መሃል የግድያ እርምጃ እንደተወሰደበት አስታውቋል። ይህ የህወሓት ወታደራዊ መረጃ መኖሪያውን ባህርዳር አየር ኃይል ምድብተኛ ግቢ በማደረግ ለአለፉት 3 ዓመታት በባህርዳር ከተማ የመረጃ ኃላፊ ሁኖ በርካቶችን ያስገደለ እና በተለይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጄኔራል ፍሳሀ እና የጄኔራል ተስፋዬ ዋና አማካሪ በመሆን በርካታ ግፎችን መፈጸሙንም ጠቅሷል። ግንባሩ ተመሳሳይ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
ግንባሩ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ የክልሉን ፖሊስ ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ESAT Zegabi Modern Ethiopia Full Version 23 November 2017

ESAT Efeta Nov 22 2017

Tuesday, November 21, 2017

- ሰበር ዜና - በረከት ስምኦን - ሰለ አማራ ክልል ጠገዴ ምስጥር አወጡ !! Nov.. 21/2017

Jacky Gosee 2017 coming soon - Menalegn yenate - ምን አለኝ የናቴ

ሜቴክ ከተቋቋመበት ስልጣን ውጪ በአቶ አርከበ እቁባይ ውሳኔ ከኢሉ አባቦራ ያዩ ወረዳ የድንጋይ ከሰል እያወጣ መሸጡ...

ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸዉ ለቀቁ

ለ ፫፯ ዓመታት በዙምባቡዌ ስልጣን ላይ የቆዩት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸዉ መልቀቃቸውን አሥታዉቀዋል። የአገሪቱ ም/ቤት ሙጋቤን በሕግ ለመጠየቅ እየመከረ ባለበት ሠዓት ነበር ሙጋቤ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸዉን ለአፈ ጉባኤዉ ያስገቡት።
ዝርዝር ይኖረናል።
Image may contain: 1 person

የአማራ ክልል የደህንነት መዋቅር እንደገና ቀየሩ (ኢሳት ዜና ህዳር 11 ቀን 2017 ዓም)

በባህርዳር ከተማ በ ዳግማዊ ዮሃንስ ሆቴል ላይ የቦንብ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ አቶ አለምነው መኮነን በከተማዋ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት ምክንያት ምንድነው በማለት የደህንነት አባላቱን ሰብስበው ጥያቄ ማቅርባቸውን የገለጹት ምንጮች፣ ችግሩ ያለው በደህንነቱ አባላት ላይ ነው በማለት አንዳንድ አባላቱን በማንሳት ሌሎችን ሹመዋል። Image may contain: 1 person
አቶ አለምነው “የአማራ ደህነት ቢሮ ብዙ መዋቅራዊ ለውጥ ቢደረግበትም ምንም ለውጥ ማምጣት አልቻለም፣ በዚህ ከተማ ፀረ ሰላም ሀይሉ በተደጋጋሚ እንደልቡ እየፈነጨበት ነው፣ የዚህ ከተማ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ነው” በማለት የክልሉን የደህንነት አባላት አጥብቀው የወቀሱ ሲሆን፣ እርሳቸውና አስተዳደራቸው በደህንነት ተቋሙ ላይ እምነት ማጣታቸውን ተናግረዋል።
በአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ የመረጃ ክፍል ሃላፊ የነበረውን አቶ አየለ አናውጤን በማንሳት በምትኩ አቶ የማነ ታደሰ የተባለ የህወሃት አባል ሀላፊ አድርገው መሾማቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አለምነው በቅርቡ አቶ ፍሰሃ ወ/ሰንበትን በማንሳት አቶ እዘዝ ዋሴን የክልሉ የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አድርገው ሾመው ነበር። አቶ አለምነው በደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ የአማራ ተወላጆችን እያስወጡ ቦታውን ህወሃቶች እንዲይዙት እያደረጉ ነው የሚል ከፍተኛ ወቀሳ እየቀረበባቸው ነው።

ESAT Special Interview with Professor Birhanu Nega Part two November 2017

ESAT Menalesh Meti, Mimi Sebhatu radio on Azeb Mesfin and Al - Amoudi

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


የዛሬ የዕለተ ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ዜና .... 
* የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች የህወሐት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ሰርገው በመግባት ጥቃት ፈፀሙ፡፡
* በሻኪሶ ሰሞኑን ትልቅ ህዝባዊ ተቃውሞ መካሄዱ ታወቀ፡፡
* የደቡብ ክልል የጸጥታ አካላት ለደህንነት አካላት ቀጥታ ሪፖርት እንድያደርጉ ታዘዙ፡፡
ከዕለቱ ዜና በማስቀጠል፡-
የድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮና ለኢሳት አፋን ኦሮሞ እንዲሁም ለኢሳት የትግረኛ ፕሮግራም በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ እናቀርባለን ፡፡ ትከታተሉን ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

Image may contain: 5 people, people sitting