ረዲን በሃልቢ
ኢትዮጵያኖች ዕድላችን ሆነና ሀገር አዳኝ ሙከራ የሚያደርጉትን ማቀፍ ሲገባን ለብቻቸው መከራን እንዲቀበሉ ትተን፤ አጋፍጠን ከተለዩን በኋላ ማልቀስ መቆጨቱ ዕጣችን ሆኗል። በአስፈላጊው ጊዜ ከአርበኞቻችን ጎን ብንቆም ኖሮ ስንቱን ስቃይና መከራ ባስወገድን ነበር ያሰኛል ። አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወደ ሀገር ዘልቆ ከወያኔ መፋለም ሲጀምር እልልታ ፈንታ ወገዛና ነቀፌታ መደመጡ ማሳዘኑ አልቀረም ። ግን እነማን ናቸው ይህን አሉታዊ ኡ ኡታ የሚያሰሙት?
ሁናቴው በትልቁ የጠቀመን ተደብቀው የነበሩትን የወያኔ ሰራተኞች ሁሉ ራሳቸውን ማጋለጥ መገደዳቸው ነው። የውቤው ልሳን፤ ከዚህ ቀደም የነጻነት ራዲዮ አባል የነበረው ኢሳያስ ደርግነቱን እንደያዘ ወያኔነቱን ደግሞ በሕዝባዊ ኃይል ላይ በነዛው የሀሰት ዘመቻ አጋልጧል። ደምስ በለጠ ከሁሉም ቀድሞ ወደ ሻዕቢያ ነጉዶ ዛሬ ተመልሶ ግን በፊት ደብቆ የነበረውን ሁሉ ሰበር ዜና ብሎ ከወያኔ ሳይቀር አድናቆትን አትርፏል። የደምስ የመደብ ጀርባ ሳይሆን የታሪክ ጀርባ የሚያሳየን ጸረ ሕዝብ የገራፊንና ባንዳዊ ሚና ነው። ዛሬም ቢሆን ያኔ የገረፋቸውን አልረሳምና ሕዝባዊ ኃይሉን ሕልውና ሲነሳው እነሱንም ወረፍ ከማድረግ አለተቆጠበም። ደምስ ወያኔ የሚያደንቀውን ተልዕኮ ሲወጣ ምነዋ ብሎ ትንሽም መጠየቅ ለምን ተሳነውስ፤ለምንስ ህሊናውን (ካለው!) መጠየቅ አቃተው? ሌላው ወያኔ የኮለኔል ልጅ ብሎ የሚያቆላምጠው ኤልያስ ክፍሌ ማንነት ለአንዴም ለሁሌም ቁልጭ ብሎ ተጋልጧል ። የፕሮፌሰር ብርሃኑን ተጋድሎ ሲያክቸለችል የራሱን ሚዛንና ሚና ግን ሊያከብድ አልቻለም ብንል ተገቢ ነው ። ኤልያስ ከኢሳያስ ጎን ተለጥፎ ሲያናፋ ያልሰማ ነበርን ? ሻዕቢያ ወይ ሞት ያለው ከሁሉም በፊት ማን ነበር ? ኤልያስ የኢትዮጵያ ብሐራዊ የሽግግር ቆንስላ ባለስልጣን ነው። ይህ ተቋም ለምን በነጻ ሊፏልል ዘንድ ፈቀደለት ። ኤልያስ በግንቦት 7 መሪዎች ይቀናል ፡፤የኢሳት በሰፊው ተቀባይነትን ማግኘትና የእሱ ሬቪው አንባቢ ማጣት ይከነክነዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሲከበሩ ኤልያስ ግን በሄደበት ዓይንህን ላፈር መባሉ ሊዋጥለት አልቻለም፤ የስለላ/ኢንተሊጀንስ/ መረቤ ይህን ያን የተደበቀ ሀቅ ፈልቅቆ አወጣ ወዘተ እያለ አሉባልታን አንግሶ ስም ሲያጠፋ የታዘብነው ኤልያስ ሰሚ ቢያጣ ጥፋቱ የራሱ እንጂ የሌላ አይደለም። በራሱ ላይ መነሳት ሲገባው ማለትም መታረም ሲኖርበት በግንቦት 7 ላይ መዝፈኑን ነው የመረጠው። እውነትም አጥፊና ግብዝ ገልሰብ።
አላርፍ ያለች ጣት እንዲሉ ባለ ራዲዮው አበበ በለውም መስመር ለቆ በህዝባዊ ሀይሉ ላይ ማጓራት ለማያዉቁት ሊያስገርም ይችላል። ግን ይህ ግለሰብ ከወያኔ ጎራ መሰለፍ ከጀመረ ውሎ አድሯል። የሱቅ ስርቆት ጉዳይ እያነሱ አንገት ይያስደፉታል የሚሉም አሉ። ድርጊቱንና ቅስቀሳውን በሚገባ ከመረመርነው ሚናው ግልጽ ይሆናል ። ወዳጁ ቤን ኢትዮጵያ ፈርስት በጊዜው በአዲስ አበባ ስለሰራው ቪላም አሳውቆን እያለና በጸረ ሕዝባዊ ኃይል አቅዋሙ ወያኔ እያደነቀው እያለ ወያኔ የሚፈራው አንድ ራዲዮ ካለ የእኔን አዲስ ድምጽ ነው ብሎ ባለፈው እሁድ ሲፎክር ሰማን ። ያ ገንዘብ አሳዳጅ፤የመላኩ ተፈራ ቀኝ እጅ፤ ዕቁብ ዘራፊ፤ ስም አጥፊ ለፍላፊ ምርጫው ስንሻው ደግሞ ስንቱን በየመስኩ ሲያታልል ሲዘርፍ ከርሞ አንዳንድ የዋሆች ጸረ ወያኔ የሆነ መስሏቸው ጆሮአቸውን ሰጠውት ነበር ። ለመሆኑ 4 ሰዓት ሙሉ በራዲዮ ሊለፈልፍ ማን ገንዘብ ሰጠው ብሎ ለምንስ አልተጠየቀም ። ስንቱን ድርጅት ሲያወግዝና ለከፋፋዮች መድረክ ሰጥቶ ሲያጠቃ፤ ወያኔን ከመተቸት ይልቅ በግንቦት 7 ላይ አተኩሮ በየሳምንቱ ሲጮህ በዚሁ አቅዋሙ ማንነቱን ያጋለጠ ግለሰብ ነበር፡፤ እነሆ ዛሬ ለወያኔው ስናር ለቤን/ብንያም ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ በሕዝባዊ ኃይሉ ላይ ዘመቻ ከፍቷል ። ወያኔም በሽልማት መልክ የሁለት ሰዓት ራዲዮ መክፈት እንዲችል ገንዘብ ለግሶታል ።
እነዚህና መሰሎቻቸው ናቸው በግንቦት 7 ና በአርበኞች ሀይል ላይ ዘመቻ የከፈቱት ፡፤ የፍርሃትን መጋረጃ ከፍተውና ቀደው ወያኔን በክላሺን ሊያነጋግሩት የተነሱትን ጀግኖች የሚያክቸለችሉት ። ባይመቱበት እንኳን ያስፈራሩበት ይላል የህገራችን ሰው ፡፤ ሕዝባዊ ኃይል ምንም ሌላ አማራጭ ብቅ ባላለበት ባለው አቅም ሊፋለምልን ተነስቶ ኑ ደግፉኝ ሲል መደገፍ እንጂ መቃወም ወያኔን መጥቀም ብቻ ነው ግቡ ። ፕሮፌሰር ሙሴና አቶ መልኬ ያላቸውን ቁርሾ እናውቃሳለንና ብዙም ትችት አይጠይቅም ። መጠየቅ ያለበት ግን ያ ጸረ ሻእቢያ ነኝ፤ዲምህት ነበርኩ ባዩ አብርሃም ያዬ አሉታዊ መለዕክትን በስልክ ማስተላላፍ ጀምሮ እያለ ምነው መሰብሰባ ማስጮህ እንዳቃታቸው ነው ። ዝንብ ቢሰባሰብ መሶብ አይከፍትም ነው ነገሩ ። ቢባልም በዝምታ ማለፉ ጉዳት አለውና ሳንታክት ጸረ ትግላችን የሆኑትን ማጋለጥና መፋለም አስፈላጊ ይሆናል ። ግባቸው ምንድነው?
1ኛ. ሕዝብ ለግንቦት7ና አርበኞች ግንባር ምንም ድጋፍ እንዳይሰጥ መቀስቀስ፤
2 ኛ. የተጀመረውን ጦርነት ውሸት ነው በሚል ድጋፍ ማሳጣት፤
3 ኛ. በድፍረት የመሪነት ቦታቸውን ተረክበው ልጆችና ምጮትን ትተው ወደ ትግሉ ሜዳ ያቀኑትን ማሳጣትና ከህዝብ መነጠል
4 ኛ. ታመነም አልታመነም ወያኔን መርዳት ።
ስለ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ድፍረትና ተዋጊነት ከእኔ በላይ የሚያውቋቸው መስክረዋልና የምጨምረው የለኝም ። ከታጋዮች ጋር ሆኜ የመጣውን ሁሉ እቀበለላሁ ብለው ሄደዋል ። የሚያኮራ ነው ። ተራው ጽዋው፤ማነህ ባለሳምንቱ ለሕዝባዊ ኃይል ደርሷልና በቆራጥነት ግዳጁን ተቀብለውታል ። የሚያኮራንና ተስፋ የሚሰጠን ነው፤ መሆንም አለበት ። በርግጥ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ የምንቆረቆር ከሆነ ። ፍልሚያው በወያኔና በሕዝባዊ ኃይሉ መሀል ነው ። ሕዝብ የሚቆመው ከልጆቹ እንጂ ከጠላቱ እንዳልሆነም እናምናለን ። ጠፍቶ የከረመውን የመሪ ድርጅት ቦታ ግንቦት7 ና አርበኞች ሞልተውታልና በርቱ በርቱ የሚያሰኘን ነው ። አንዳንድ ጸሃፊዎች ረጅም አረፍት ነገር ይዘረጉና በንባቡ አንባቢው ውሉ ይጠፋዋል ። ነቃፊ ሆነው ለፋፊዎቹና ጸሓፊዎቹ (ፕሮፌሰር ሙሴ ለምሳሌ) ምን ሊናገሩ እንደሚፈልጉ ማወቅ ስይሆን መገመት እስኪያቅተን ድረስ ያደርሱናል ። አይገባም ፡፡ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም ነውና ያለው ሁኔታ በግልጽ መቅረብ አለበት ። ይህ ማለትም
ህ/ ሕዝባዊ ኃይል ታጋዮች በኢትዮጵያ መሬት ወያኔን እየተፋለሙ ነው ።
ለ/ የሀይሉ መሪዎች ወደ ትግሉ ሜዳ ዘልቀዋል።
ሐ/ ሁኔታው ወያኔና ደጋፊዎቹን ብርክ አስይዟል ።
መ/ ድያስፖራው በተለይ ለሕዝባዊ ኃይሉ ድጋፍ ሊስጥ ይገባዋል ።
ሰ/ የወያኔ ጀሌዎች ተጋልጠዋል ።
ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ። ነገ ሀቁ ቁልጭ ብሎ የሚታየው በወያኔ መፍረክረክና ውድቀት ነው።
No comments:
Post a Comment