Monday, February 16, 2015

ወያኔ ጋር የሚፈላ ደም እንጂ የሚያስተውል ልቦና እንደሌለ አወቅን።!!!
ዛሬ በዚህ ቦታ ላይ በአገራዊ ፍቅር፣ በኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ስለአገራችን ለመሰባሰብ ምክንያት የሆነን የኢትዮጵያው ብርሃን አንዳርጋቸው ጽጌ ነው። አገር ወዳድ እና ጀግና ሰዎች  ብርሃናዊ ስራቸውን  እራሳቸውን እያቀለጡ አብሪ ስራቸውን ይለኩሱታል። ኢትዮጵያ ብዙ ጀግኖች ያፈራች የምታፈራ አገር ነች ።ዛሬ በክብር ልደቱን የምናከብርለት አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ጀግኖች አንዱ ነው።ጀግኖች የሰሩት ብርሃናዊ ስራ ሁሌም ሲያበራ ይኖራል ። አንዳርጋቸው ዛሬ 60ኛ አመት የልደት ሻማህን ስንለኩስ ሻማ እራሱን እያቀለጠች ለሌላው ብርሃን እንደምትሆነው ሁሉ አንተም እራስህን መሰዋት አድርገህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብርሃን የሆንከን ጀግናችን ነህ ብለን እናከብረዋለን።ኢትዮጵያ በጀግንነትህ የምትዘክርህ የኢትዮጵያ ጀግና ነህ። በዚህ አጋጣሚ እኔም ለወያኔ መልዕክቴን እንዲህ አስተላልፋለው።

ግፉ በአስቸኳይ  ይቁም። በየአካባቢው ያለ  ምክንያት የሚገደሉ ዜጎች አይኑሩ። በየመንደሩ ማዋከብ ይቁም። እስር ቤቶች የንጹሃን ዜጎች ማሰቃያ  አይሁን። እውነትን በሐሰት ለመለወጥ አትሞክሩ... ወርቅን በጠጠር እንደ መለወጥ ነውና። ምክንያት እየፈጠራችሁ ግፍና  በደልን አትፈጽሙ.... ፈሪ ሃይልን ያበዛልና... ሃይልን ከመጠቀም እና የከፋ  በደል ከመስራት ተቆጠቡ። ዛሬ ለጥቂቶች ብርሃን ቢመስላቸውም ነገ እንደሚጨልምባቸው እወቁ። ዛሬ ለጥቂቶች ብዙሃኑን እረግጠው የነጻነት ቀን የመጣ ቢመስላቸውም ነገ ብዙሃኑ አሸንፎ ነጻነቱን ሲያውጅ ለጥቂቶች እንደሚጨልምባቸው እወቁ። ከጥቂቶች ጋር በማቀንቀን የግፍ ጽዋን አታንሱ... ከብዙሃኑ ጋር የእውነትን መራራ ሕይወት ተጋሩት እንጂ። ምክንያቱም ግፈኞች የሚኖሩት ለጥቂት ግዜ ነውና... ሕዝብ ግን ለሁሌ ስለሆነ ከህዝ ጋር አትጣሉ እናንተ የወያኔ ተላላኪዋች። ዘርተን አብቅለን መገብናቸው የሚጠጡትንም አቀረብንላቸው መልሰው በጥጋባቸው እኛኑ እየረገጡን አላስቀምጥ አሉን። ጥጋባቸው ቁንጣን ሆነባቸው። ወያኔ ጋር የሚፈላ ደም እንጂ የሚያስተውል ልቦና እንደሌለ አወቅን። የወያኔ ስጋት ከልክ በላይ ደርሶ እንቅልፍ ካሳጣው ሰነባብቷል። በአሁኑ ግዜ ዞሮ ማየት በነጻነት መናገር እንደ ወንጀል ተቆጥሯል። እውነት ሲነገራቸው አይወዱም... ስለ ነጻነት እንዲነሳባቸው አይፈልጉም። እውነት ያስፈራቸዋል ነጻነትም ያንገሸግሻቸዋል። ከዚህ እውነት ለመሸሽ እናንተ የደርግ ርዝራዦች... እኛ ነን ሰው ያደረግናችሁ... እኛ ነን እድገት ያመጣንላችሁ... እኛ  ነን ነጻነትን ያመጣንላችሁ... ይሉናል በቀጣፊ አንደበታቸው አይናቸውን በጨው አጥበው። እኔ አልገባኝ ይሆን? ምንድነው ነጻነት? እድገትስ ምን ማለት ነው? ስታስነጥስ ይሄ የአሸባሪ አነጣጠስ ነው ብለው በፈሪ ዱላ እየቀጠቀጡ ወደ ወይኒ ማጋዝ ነው?... ወይስ ብዕር ስታነሳ ይሄ የአሸባሪ ብዕር ነው እያሉ ወይኒ ማውረድ ነው። ነጻነት ምንድ ነው? እድገትስ ምን ማለት ነው? የአይንህ ቀለም አላማረኝም ተብሎ አሸባሪ ነህ እያሉ በፈሪ ዱላ መቀጥቀጥ ነው። ወይስ ለጥቂት ተላላኪዎች እና  ለወያኔ ሰዎች የህዝብን ንብረት ዘርፈው በህዝብ ሃብት ህንጻ መቆለል ነው? ኽረ የቱ ነው እኔ አልገባኝም? አገሪቷን ከአለም አንደኛ  የብድር እዳ  ያለባት አገር ማድረግ ነውወይስ በየቦታው ስደተኛን እና ችግረኛን ማብዛት ነው? ወይስ ዜጎች በአገራቸው  መብት አልባ  አድርጎ ማኖር ነው? ወይስ ከላይ እስከ  ታች እንደ ሰንሰለት በተጠላለፈ ካድሬ መጠርነፍ ነው እድገት እና  ነጻነት? ምንድነው ነጻነት ? በነጻነት ካልኖሩ በነጻነት ካልሰሩ በነጻነት ካልተናገሩ በነጻነት ካልዘመሩ ነጻነቱ ምኑላይ ነው። ህዝቡ ነጻነ ያገኘች አገር ሆን ኖሮ ህዝቡ በነጻነት የመስራት እና  የመንቀሳቀስ መብቱ የተጠበቀ  ቢሆን... ሁሉም በሙያው ያለሙስና  እና ያለ አድሎ በእውቀቱ በችሎታው ቢሰራ... ህዝብ የወደደው መሪ በህዝብ የተመረጠ እና የተወደደ መሪ ቢኖራት አሁን ወያኔ አድጋለች ብሎ ከሚነግረን በሚታይ እድገት ሞቶ እጥፍ ከደስታ ጋርና ከሰላም ጋር ታድግ ነበረ... ውዷ አገራችን ላይ እንደመዥገር  ተጣብቀው የጥቂቶች እድገት እና ሰላም ታውጆባት የግፈኞች በደል ህዝባችን ላይ ተጭኖ ለመኖር ተገደድን። ሰላምን ያጣ እና  ነጻነቱን የተነፈገ ህዝብ በጀግንነቱ ነጻነቱን እንደሚመልስ የታወቀ ነው።ወያኔ ሆይ ህዝችን ጀግና መሆኗን አትዘንጋ።
አንዳርጋቸው ስሙ ትርጉም ያለው.. ስራውም ትርጉም ያለው... የኢትዮጵያ ብርቅዬና ጀግና ልጅ ነው። በሁሉ ነገር ሙሉ የሆነ በትምህርቱ፣ ትልቅ ቦታ የደረሰ ባለትዳር እና የ3ልጆች አባትም የሆነ ሰው ነው። አንዳርጋቸው ግን   ሁሉም በላይ ከትምህርቱም፣ ከቤተሰቡም በላይ ኢትዮጵያ ለሚለው ስምና አገር ትልቅ ቦታ ያለው ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ  ህዝብ ሙሉውን ግዜ በስራ  ላይ ያዋለ የኢትዮጵያ  ጀግና  እና ብርቅዬ ልጅ ነው። ይሄንን ጀግና ሁሌም እናስበዋለን። አንዳርጋቸው የጀመረውን የነጻነት ትግል ሁላችንም ወደ ትግሉ ተቀላቅለን ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር አጥፍተን በጀመርከው የትግል መንገድህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎንህ እንደሚሆን እና አደራውንም እንደምንወጣ ቃል በመግባት ነው።   
ፈሪ ሁሌም ሃይልን ያበዛል። የፈሪ በትሩ አንድ ነው እንዲሉ። ጀግና  ደግሞ  ዝም ይላል ይታገሳል ዝምታውን ሰብሮ  ትግስቱ  ያለቀ እለት... የወያኔን የፈሪን ጅስም ሰብሮ  ጀግናው ህዝብ ጅስሙን ያሳየሃል። ለዚህም ደግሞ   ተዘጋጅተናል። ግዜው የድል ነው።


- ደጀኔ                                                                                                                                                14.02.2015                                                                                                                                                                         Email- mergadejene50th@gmail.com

No comments:

Post a Comment