Thursday, February 26, 2015

አሁን ገና ጫላ ጩቤ ጨበጠ !
ኦህዴድ ውስጥ ያላችሁ
*ብሄር እና ሃይማኖት , ፖለቲካ እና ሃይማኖት , ባህል እና ሃይማኖት የተምታታባችሁ ወይም ሆን ብላችሁ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ ያላችሁን ጥላቻ በብሄር እና ክልል ስም በመሸፈን ... በትምክህት ተወጥራችሁ ይቺን የፈረደባት ቤ/ክርስትያን በቃላትም , በድርጊትም የምታጠቁ የተለያዩ እምነት ተከታይ የሆናችሁ ፅንፈኞች , አታብዙት !
ትላንት ደራ ይሁን ኦዴት የተሰበሰቡት የማይታወቅ የጅሎች መንጋ .. ከ 700 አመት በላይ የሆነውውን ታሪካዊ የሃይማኖት ቦታ .. መንካት ቀላል ከመሰላችሁ ሞክሩት ::

ሲጀመር የምስራቅ ሸዋ ተወላጅ የሆኑ ኦርቶዶክስ ኦሮሞዎች , እንዲሁም መላው ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያዊ ዝም አይላችሁም :: ይቺንም ድፍረታችሁን የሞከራችሁት , ከሌላ የኦሮምያ አካባቢ መጥታችሁ ምስራቅ ሸዋን የምታስደዳድሩ ኦርቶዶክስ ያልሆናችሁ ሰዎች ናችሁ ::
በኦሮሞ ስም አትነግዱ ! ሌቦች ..አናቃችሁም እንዴ ? ለአበባ ንግድ , ኢንደስትሪ ዞን , ኢንቨስትመንት እያላችሁ ስንቱን የገበሬ መሬት ነጥቃችሁ በሙስና እንደቸበቸባችሁ .. የምትቆረቆሩ ከሆነ ሌብነታችሁን አቁሙ ! በዘመድ አዝማድ ስም 3 እና 4 ቦታ ከ የትም እየመጣችሁ, እየተጠራራችሁ ምስራቅ ሸዋ ላይ በፉክክር እንደተቀራመታችሁ እናውቃለን .. ለህዝብ የቆማችሁ በማስመሰል ኦርቶዶክስ ላይ የጀመራችሁትን ዘመቻ ብታቆሙ ይሻላችሁዋል ! በሃይማኖት ሰፋጣ ከመጣ ማንም ዝም አይላችሁም .. !
ሃገር እና አካባቢው የተለያየ ሃይል ሲፈራረቅበት 700 አመት ሙሉ ፀንቶ የቆመ ገዳም ነው ::
እንከባበር !
ለማንኛውም , መጋቢት 5 መጥታችሁ ክብረ በአሉን እዩት እና ይቺ ያበጠች ልባችሁ ምንም እንደማታመጣ ትረዳላችሁ ::

No comments:

Post a Comment