Wednesday, February 11, 2015

ፖለቲካ እንደገና የሞቀው የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ እሰጥ አገባ

እንደገና የሞቀው የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ እሰጥ አገባ - ዘገባ
ከአምባሣደር ግርማ አስመሮም ጋር ለተደረገው ቃለምልልስ ከታች ያለውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ፡፡
አምባሣደር ግርማ አስመሮም በኢትዮጵያና በኤርትራ ጉዳይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ከቪኦኤ የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በትረ ሥልጣን ጋር ያደረጉትን ውይይት ከታች ከተቀመጠው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አምባሣደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ውይይት
የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያ ጦሯን “ከተወሰነልኝ ክልል ታስወጣ” እያለ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሳምንቱ ማብቂያ ጅቡቲን በጎበኙበት ወቅት የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማይል ኦማር ጊሌም በኤርትራ ላይ ተመሣሣይ ክሥ አሰምተዋል፡፡
በአፍሪካ ኅብረት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪ፤ አምባሣደር አርአያ ደስታ ሰሞኑን ለኅብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ ደብዳቤ ፅፈው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ በሕግም ሆነ በቴክኒክ ውሣኔ ካገኘና ከተጠናቀቀ ሰባት ዓመታት ማለፋቸውን፤ የኢትዮጵያ ጦር ከኤርትራ ግዛት እንዲወጣና መሬቱ እንዲመለስላቸው ግፊት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮምም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተመሣሣይ ጥያቄ አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽኑን ውሣኔ መቀበሏን በወቅቱ ማሳወቋን ጠቁመው የመካለሉን ጉዳይ ለመጨረስ ኤርትራ ለውይይት መቀመጥ እንዳለባት ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያና ኤርትራ

No comments:

Post a Comment