Wednesday, February 18, 2015

"ልክ እናስገባቸዋለን"፡
ኦሮሞን አሁን ነው እንዴ ልክ ማስገባት የጀመሩት? ወያኔ እኮ የጅል-ብልጦች ስብስብ ነው። ኦነግ ከልቡ አምኖ ብዙ መስዋትነት አብሯቸው ከከፈለ በኋላ፥ ፊንፊኔን ከተቆጣጠሩ በኋላ በከይሲ ስራቸው፥ በአሻጥር የኦነግ አመራሮችን ግንባር ግንባራቸውን ብለው ነው ወደ ዜሮ ያወረዷቸው። ታዲያ ይሄ የሚጠፋው ኦሮሞ አለ? ያለ ይኖራል ብየ አላስብም።
በያንዳንዷ ሰላማዎ ተቃውሞስ ውድ የኦሮሞ ልጆችን፥ ኦነግን እንደዛ ማፍረሳቸው ሳያንሳቸው፥ ስሙን እየተጠቀሙ ስንቱን በስር አበሰበሱት ስንቱንስ በቶርቸር ገደሉት? ይህስ ይረሳል?
በቅርቡ እንኳን በፊንፊኔ ዙሪያ ማስተር ፕላን ዙሪያ ነጭ ወረቀት ይዘው የወጡን ተማሪዎች ግንባር ግንባራቸውን ብለው ገድልው በብዙ ሺ የሚሆነው ማሰራቸውስ እንዴት ይረሳል?

የ አባይ ጸሃየ" ልክ እናስገባቸዋል"ስ እንዴት ይገርማል ? እየተስተዋልው!
በቅርቡ ከአባዱላ ጋር ሻይ ለጠጣችሁ፥ በግልጽ የኦሮሞን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለባችሁ። ነገ እራሱ አባዱላ" ልክ አስገባችኋለሁ" ይላል ፥ ያደርገዋልም በጣም ጨካኝ ሰው ነው። በኦሮሚያ የተደረጉ ማንኛውም መግደልና ማሰር ከሱ እውቅና ውጭ አልተደረገም። ስለዚህ ልክ ማስገባት ለሱ ቀላሉ ነገር ነው።
ትምህርት ያልቀመሰው አባይ ጸሃየ፥ የበፊት መሰንጠቅ መዓበልን በዘዴ የሸወደ፥ አሁን ደግሞ ባዶነቱን በንጹሃን ኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ አሳይቷል።
አንድ የኦሮሞ ጀግና ወያኔን ልክ የሚያስገባ ይጠፋል? በፍጹም የጊዜ፡ጉዳይ ነው!
ልክ ይገባሉ!

No comments:

Post a Comment