Friday, February 6, 2015

ጣይቱ
ሙሉ ንግስት የሴት አርበኛ
አትንኩኝ ባይ ፍርድ አወቅ ዳኛ
ለነፃነት ፋና የሆነች
ጀግና እመቤት ማነች 
አረግ አረግ እንዴት ቢደረግ
የምረሳት የራሴን ማረግ
ጸሃይ ሆና ሀገር የሞቃት
ፊት አውራሪ አለም ያወቃት

ጣይቱ እቴጌይቱ
ጣይቱ እመቤቲቱ
አደዋ ላይ ዘምታ ያዘመተች
ደግ እመቤት ፍቅር አዋቂ ነች
ያገር እናት ያች ልበ ብርቱ
በልቤ ውስጥ በርታለች ጣይቱ
ያች ያገር እናት እመት መላይቱ
ዛሬም በልቤ ውስጥ በርታለች ጣይቱ
የጀግናዋ ልጅ ነኝ የጣይቱ ፍሬ
የቁርጥ ቀን ብርሃን እኔም አለኝ ዛሬ
መች ፈሪ ነኝ እና ወደኋላ እላለሁ
ካሰብኩት እደርሳለሁ ታላቅ እሆናለሁ
ዘራፍ ዘራፍ ምያለሁ በጀግናዋ እናቴ
ዉርድ ከራሴ ለዛ ጠላቴ
ወድቆ ሳላየው አንላቀቅም
የምን ፍራቻ ታሪክ ሳልደግም
ጣይቱ ማለት እኔ ነኝ ዛሬ
አለሁልሽ ባይ ለእናት ሃገሬ
ባለመፍትሄ የስኬት አንጋሽ
ያን ጀግንነቷን እኔ ነኝ ወራሽ
.....
እምየም አክብሯት እሷም አክብራው
በንግስቷ ብልሃት ሃገር የመራው
የእድገት መሰረቱ የማለዳ ጮራ
ምኒልክ ወንድ ነው በሴት የሚጠራ
እምየ ምኒልክ ጊዜን ቀድሞ ነቅቶ
ለቴጌ ጣይቱ ትልቅ ቦታ ሰጥቶ
ልክ እንደማጀቷ ጦሩን አዘጋጅታ
ሃገሩን መራችው በወኔ ተሞልታ
የጣይቱ ደም ነን ጀግንነት ወርሰናል
ካለምነው ሳንደርስ ማን ይመልሰናል
ስሟ እንኳ ስንቅ ነው ልብን ያበረታል
ዝናዋን የሰማ መች ያፈገፍጋል
ሙሉ ንግስት የሴት አርበኛ
አትንኩኝ ባይ ፍርድ አወቅ ዳኛ
ለነፃነት ፋና የሆነች
ጀግና እመቤት ማነች 
አረግ አረግ እንዴት ቢደረግ
የምረሳት የራሴን ማረግ
ጸሃይ ሆና ሀገር የሞቃት
ፊት አውራሪ አለም ያወቃት
ጣይቱ እቴጌይቱ
ጣይቱ እመቤቲቱ
አደዋ ላይ ዘምታ ያዘመተች
ደግ እመቤት ፍቅር አዋቂ ነች
ያገር እናት ያች ልበ ብርቱ
በልቤ ውስጥ በርታለች ጣይቱ
ያች ያገር እናት እመት መላይቱ
ዛሬም በልቤ ውስጥ በርታለች ጣይቱ
የጀግናዋ ልጅ ነኝ የጣይቱ ፍሬ
የቁርጥ ቀን ብርሃን እኔም አለኝ ዛሬ
መች ፈሪ ነኝ እና ወደኋላ እላለሁ
ካሰብኩት እደርሳለሁ ታላቅ እሆናለሁ
ዘራፍ ዘራፍ ምያለሁ በጀግናዋ እናቴ
ዉርድ ከራሴ ለዛ ጠላቴ
ወድቆ ሳላየው አንላቀቅም
የምን ፍራቻ ታሪክ ሳልደግም
ጣይቱ ማለት እኔ ነኝ ዛሬ
አለሁልሽ ባይ ለእናት ሃገሬ
Mimi Mimi's photo.
Mimi Mimi's photo.

No comments:

Post a Comment