#የሚሊዮኖችድምጽለሕሊናእስረኞች ኢህአዴግም የቀድሞ ሥርዓቶች ቀጣይ ነው።
ሀብታሙ አያሌው
የኢህአዴግ አባል ነበር። ገንዘቡም መኪናውም በዕጁ ነበር። ነገር ግን የሚያየው ነገር ከሕሊናው ጋር የሚሄድ ስላልሆነ አምባ-ገነኖችን ትቶ ዕውነተኛ ፍትህን፣ ነጻነትንና ዕኩልነትን በሀገሪቱ ውስጥ ለማምጣት ሰላማዊ የፓለቲካ ትግሉን ተቀላቀለ። በተለያዩ ክርክሮች ላይም ነገሮችን በተጨባጭ ማስረጃ በማቅረብ በጥሩ አንደበቱ የኢህአዴግን ገመና በየመድረኩ ያጋልጥ ጀመር። አምባ-ገነኑ ደርግ እንደ ወደቀው ሁሉ ከስህተቱ ካልተማረና ካልተመለሰ ኢህአዴግም እንደሚወድቅ በሰላማዊ ሰልፎችና በተለያዩ መድረኮች ጋር በግልጽና በአደባባይ ይነግራቸው ጀመር።
የልጁ ደፋርነትና በተጠና ሁኔታ ከሌሎች ጋር ሆኖ ትግሉን መምራት ለኢህአዴግ ራስ ምታት ሆነብት። ስለዚህ በሐሰት ክስ "ሽብርተኛ" ብለው ቃሊቲ ወረወሩት። እሱም ጥቅምና ስልጣን ቢፈልግ ኖሮ "ታላቁ መሪ" እያለ ተሾሞ እዚህና እዚያ መሬት ወስዶ በመቸብቸብ ሚሊየነር ይሆን ነበር። ሕጻን ልጁንም እንደ ሌሎቹ ባለሥልጣናት አሞላቆ ያሳድጋት ነበር። ነገር ግን እሱ በወንጀልና በሰዎች ደም ከሚገኝ ገንዘብና ሥልጣን ይልቅ ነጻነቱን መረጠ። ሕጻን ልጁን እቤት ትቶ ላመነበትም ነገር ታስሮ ቶርች እየተደረገ ዋጋ ከፈለ። አሁንም በመክፈል ላይ ነው። እሱ ይሄንን ሁሉ እያደረገ ያለው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ነው።
No comments:
Post a Comment