Monday, February 16, 2015

‪#‎Ethiopia‬: በየመን የሚኖሩ የቀድሞ ኦነግ አባላት በኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር እየተመለመሉ ነው::በኬንያ ድርድሩ ቀጥሏል:: ‪#‎Oromo‬ ‪#‎ODF‬ ‪#‎OMN‬
Minilik Salsawi በኬንያ የተደረገው የምልመላ እና ስብሰባ ጥሪ ሳይሳካ በተቃውሞ ታጅቦ መሰረዙ ታውቋል::በየመን በስደት የሚኖሩ የቀድሞ የኦነግ አባላት በወያኔ አጋዥነት በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አስተባባሪነት በሌንጮ ባቲ መሪነት ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ እየተመለመሉ መሆኑን በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገለጹ::ከወያኔ ጋር በኬንያ ድርድር እያካሄደ ያለውና በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር በየመን በመሰረተው ቅርንጫፍ አማካኝነት በወያኔ የደህንነት ሃይሎች እየታገዘ በየመን ለሚመለምላቸው የቀድሞ የኦነግ አባላት ከወያኔ አስፈላጊዉን በጀት እንደተመደበላቸው ለማወቅ ተችሏል::

የወያኔ እና የኦዴግ ዋና ግብ የአንድነት ሃይሎችን አዳክሞ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስፋፋት እንዲሁም በውጪ ላሉ የጎሳ ድርጅቶች አስፈላጊዉን አሟልቶ ወደ ሃገር ቤት መመለስ ሲሆን የቀድሞ የኦነግ አባላትን አሰባስቦ ወደ ሃገር ቤት ማምጣት ሌላኛው አላማቸው ነው በዚህም መሰረት በአቶ ሌንጮ ባቲ የሚመራ ቡድን በየመን እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ሲታወቅ ወደሰላማዊ ትግል መመለስ እንጂ ወያኔን ከስልጣን የማውረድ ግብ እንዳሌለው ለተመልማዮች ባዘጋጀው ኦረንቴሽን ላይ ገልጿል::
እንዲሁም ላለፉት 40 አመታት የታገልነው የመገንጠል ጥያቄ ምንም ውጤት ስላላመጣ በጋራ ከሕወሓት ጋር በመሆን ኦሮሚያን ማስተዳደር እና በግዴታ የሚጫንን ኢትዮጵያዊነት መቃወም የሚሉ ንግግሮች ለተመልማይ ስደተኞች አስደምጠዋል::ከሕወሓት ጋር አስፈላጊዉን ድርድር እንዳደረጉና ተመልሰው ወደ ሃገር ቤት ለሚገቡ ስደተኞች አስፈላጊ የደህንነት ከለላ እና ስራም እንደሚሰጣቸው እየተሰበከ መሆኑን ከአከባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ሲጠቁሙ በኬንያ እየተደረገ ያለውን ድርድር/ንግግር ተከትሎ ለስደተኞች ሊደረግ የታሰበው ሰበካ በሁለቱም ወገን ሳይሳካ ቀርቷል::በኬንያ የቀጠለው ድርድር ከኦሮሞ ተወላጆች ተቃውሞ እየቀረበበት ሲሆን ቀጣዩ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ጉዞ አለየለትም የሚሉ ወገኖች ቢከሰቱም ወደ ሃገር ቤት ለመግባት አስፈላጊዉን ሁሉ ከመስማማቱም በላይ ወደ ሃገር ቤት ለሚመለሱም ወገኖች አስፈላጊዉን ክፍያ ለማድረግ ከወያኔ ገንዘብ እንደተቀበለ ለግንባሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል::

No comments:

Post a Comment