Thursday, February 26, 2015

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም :-አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ  በአለም ባንክ ድጋፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ፣ የባንኩን ፖሊሲ የሚጻረሩ ሆነው መገኘታቸውን የአለም ባንክ የውስጥ የምርመራ ክፍል ማሳወቁን ገልጿል። ይሁን እንጅ የባንኩ ማኔጅመንት በባንኩ የውስጥ የምርመራ ቡድን የቀረበውን ሪፖርት የሚቃረንና ባንኩን ከተጠያቂነት የሚያድን ሌላ ሪፖርት አቅርቧል። የአለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በምርመራ ክፍሉና በማኔጅመንቱ የቀረቡትን ሁለት የተለያዩ አስተያየቶችን ለማየት ከሶስት ቀናት በሁዋላ ይሰበሰባ
ል።

የምርመራ ክፍሉ፣  ከጋምቤላ አካባቢ የተፈናቀሉ ሰዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ተንተርሶ ምርመራ ያካሄደ ሲሆን፣ በምርመራውን የአለም ባንክ ራሱ ያወጣውን ፖሊሲ መጣሱን አረጋግጧል። በሂውማን ራይትስ ወች አለማቀፍ የገንዘብ ተቋማትን አስመልከቶ ምርምር የሚያደረጉት ጄሲካ ኢቫንስ እንደተናገሩት ፣ የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ለሰብአዊ መብት ጥሰቶችን  ተገቢውን ቢታ አልሰጠም። ተመራማሪዋ፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ላይ የሚያከናውነውን  ፕሮግራም መቀየር ፣ በዚሁ ፕሮግራም ለተጎዱት ችግረኞች መፍትሄ መስጠት ሲችል ያንን አላደረገም ብለዋል። 
በሰፈረ ፕሮግራም በርካታ ዜጎች ለችግር መዳረጋቸውንና መንግስት ያከናወነው ሰፈራ ፕሮግራም ከአለም ባንክ ፕሮጀክት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል። በባንኩ የምርመራ ቡድን የቀረቡትን ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦችን ተግባራዊ እንደማድረግ፣ የባንኩ ማኔጅመንት በተቃራኒው አሁን የሚታየውን ችግር የሚያጠናክር ሌላ የድርጊት መርሃ ግብር ነድፏል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ገልጿል።
የምርመራ ቡድኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብት ዙሪያ ላይ የሚሰሩ የሲቪል ሶሳይቲ ተቋማትን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ እንዲሻሻል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን አለመውሰዱ በመግለጫው ጠቅሷል ።
የአለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የማኔጅመንቱን መልስና አዲስ የወጣውን የድርጊት መርሃ ግብር በመመለስ፣ የምርመራ ቡድኑ ባነሳቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ  ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል።
ለትክክለኛ ልማት እንቅፋት የሆነው የሰብአዊ መብት ጉዳይ ትኩረት ያገኝ ዘንድ በባንኩና በኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ውይይት ሊካሄድ እንደሚገባውም የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ጠይቋል።
ለጋሽ አገራት በኢትዮጵያ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ግምት ውስጥ እንደማይከቱ የሚያመለክተው መግለጫው፣ በፕሮጀክቶች የድሆችን ተሳትፎ እንዲሁም ከሚለገሰው ገንዘብም ተጠቃሚ የሚሆኑበት ፕሮግራም መነደፍ እንዳለበት  ድርጅቱ አስታውቋል።የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የተፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በጽሞና እንዲያቸው ተጠየቀ

No comments:

Post a Comment