ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔው አወቃቀር ክልል 3 ብሎ በሚጠራው አካባቢ ግጨው በተባለው ቦታ ከወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ጋር ባደረገው እረጅም ሰዓት የፈጀ ውጊያ 22 በመግደልና 29 ደግሞ በማቁሰል በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል የቆሰሉ ወታደሮችም ዲቪዥን ወደሚገኘው ሆስፒታል እንደተጓጓዙም የሪፖርተራችን መረጃ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ህዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚሁ በአማራ ክልል ዳንሻ አካባቢ ልዩ ስሙ ማይለሚን በተባለው ቦታ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ውጊያ 12 በመግደልና 14 በማቁሰል የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝ ሹማምንቶችን ቅስማቸውን የሰበረ አንፀባራቂ ድል እንዲሁም የወገንን አንጀት ያራሰ ድል መጎናፀፉን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል።
በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ድጋፍ እያገኘና ህዝብን ከጎኑ ማሰለፍ የቻለው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ባደረጋቸው ተከታታይ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች የሃገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረበትን ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡንና ይዞት የተነሳው አላማም በሃገራችን ላይ የተንሰራፋውን አምባገነናዊ ስርዓት ገርስሶ በመጣል ሃገርና ህዝብን መታደግ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብም ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገለት ይገኛል።
No comments:
Post a Comment