አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
በጋንቤላ የመከላከያና የክልል ልዩ ሀይል በጋራ የተሳተፉበትና የጦር መሳርያ ለማስፈታት በሚል የቤት ለቤት አሰሳ እየተደረገ ሲሆን በዚህ ድንገት በተጀመረ አሰሳ የጦር መሳርያዎች የተያዙ ሲሆን አናስረክብም ያሉ በርካታዎች ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
ከኢታንግ የተጀመረው የቤት ለቤት አሰሳ በአኮቦና በጋንቤላ ከተማ የተደረገ ሲሆን በመቀጠልም በሌሎች ወረዳዎች እንደሚቀጥል ሲታወቅ በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የድንበር ላይ የምትገኘው የማተር ከተማ ቀጣይ ተፈታሽ ከተማ መሆንዋ ተሰምቷል። ይህ ፍተሻ ከትናንት በስቲያ ሲጀመር የክልሉ ፖሊስ ሀይል ትጥቅ እንዲፈታ መደረጉ ታውቋል፡፡
ከወደ ጋምቤላ እንደሚሰማው ከሆነ ይህ የቤት ለቤት ፍተሻ ህገ-ወጥ የጦር መሳርያ የታጠቁትን ለማስፈታት በሚልና ባለፈው አመት ተቀስቅሶ የነበረው የእርስ በርስ ግጭት አይነት ዳግም እንዳይቀሰቀስ ለመከላከል መባሉና መሳርያ የተገኘባቸውን መሳርያቸውን ከመውረስ ባሻገር ከየት እንዳመጡት ምርመራ ይደረግባቸው እንደነበር ያስረዳል፡፡
ከትናንት ወዲያ በጋንቤላ ከተማ ከሌሊቱ 11 ሰአት የክልሉ ነዋሪዎች ሳያውቁት ድንገት የተጀመረው ይህ የቤት ለቤት አሰሳ ከተሰጠው ምክንያት ይልቅ ክልሉ በተደጋጋሚ ፀረ ወያኔ አመፅ የታየበት በመሆኑና ዳግም ሊከሰት እንደሚችል በመስጋት በቅድሚያ የተወሰደ እርምጃ መሆኑንና ይልቁንም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአማፂው የደቡብ ሱዳን ም/ፕሬዘዳንት ጋር የተፈጠረው ልዩነትና የሰውየው ሸማቂ ሀይሎች በጋንቤላ አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች ላይ መንቀሳቀሰቀ ለወያኔ ተቃዋሚ ሀይሎች ሊፈጥር የሚችለውን ምቹ ሁኔታ የፈጠረው ስጋት ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩ በርካቶች ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment