Sunday, November 20, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ነጻነት ተፋላሚዎች በአዲ ጎሹ ከህወሃት ሠራዊት ጋር ውግያ መግጠማቸው ተገለጸ

ህዝባችንን በጠመንጃ ኃይል አፍኖ ለመግዛት ያለ የሌለ ኃይሉን ወደ ሰሜን በማጓጓዝ ላይ ካለው የህወሃት አገዛዝ ጋር ፊልሚያ የጀመረው የአርበኞች ግንቦት 7 ነጻነት ተፋላሚዎች በተለያዩ የጎንደር ግዛቶች ከፍተኛ ውጊያ እያካሄዱ መሆኑን ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች ያረጋግጣል።
በተለይ ካለፈው አንድ ሳምንት ጀምሮ በየዕለቱ እየተካሄደ ባለው በዚህ ፍልሚያ የጎንደር አካባቢ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ከነጻነት ተፋላሚው ኃይል ጎን በመሰለፍ ለነጻነቱ እየተዋደቀ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎአል። በሰሜን ጎንደር አዲጎሹ በተባለው ሥፍራ በትናንት ዕለት ዓርብ ህዳር 10 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት በተደረገው ውጊያ የአርበኞች ግንቦት 7 ተፋላሚዎች በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል እንደተቀዳጁ በዚህም የተነሳ በርካታ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ የመከላኪያ ሠራዊት አባላት መሳሪያቸውን ጥለው እንደኮበለሉ ተያያይዞ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ህወሃት በኦሮሚያ፤ በአማራና በደቡብ የተጀመረውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ለማኮላሸት ባወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገፍተው ብረት ያነሱና ጫካ የገቡ በርካታ የጎንደር ወጣቶች የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይልን እየተቀላቀሉ እንደሆነ ይነገራል። ከወጣቶቹ በተጨማሪ አገዛዙ ላይ ባላቸው ተቃውሞ መሳሪያ ያነሱና አካባቢው ውስጥ በተለያየ ደረጃ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎችም በመካከከላቸው ካገኙዋቸው የነጻነት ታጋዮች ጋር በመቀላቀል ጠላትን እየተፋለሙ እንደሆነ ታወቆአል።
የመንግሥትን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የአገር ሃብትና ንብረት ዘረፋ ላይ የተሰማራው የህወሃት አገዛዝ በእምነት ተቋሞች ውስጥ ሳይቀር በሚፈጽመው ወንጀል በርካታ የሃይማኖት አባቶች እየተገፉ ከነጻነት ትግሉ ጎን እየተሰለፉ እንደሆነ በዚህም የተነሳ 13 የዋልድባ ገዳም መናኩሳት አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅለው የነጻነት ትግሉን እየመሩት እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን የኢትዮጵያ  ሳታላይት ቴለቪዥን በትናንትናው ዕለት መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment