አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም
ለጋዜጠኞች ጥበቃ የሚሰጠዉ አለም አቀፍ ድርጅት ሕዉሐት እያደረግ ያለዉን ጋዜጠኞችን የማፈንና የማሰር የማሳደድ እንዲሁም የመግደል ድርጊቱን እንዲያቆምና ያሰራቸዉን ጋዜጠኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ ይኸዉ አለም አቀፍ ድርጅት ጠየቀ።
በዚህ ባሳለፍነዉ ሳምንት ዉስጥ አንድ የጋዜጣ አዘጋጅና ሁለት የዞን ዘጠኝ ተሸላሚ ብሎገሮችን በተደጋጋሚ በሽብርተኛና ሽብርን በማነሳሳት በሚል ክስ በተደጋጋሚ በመክሰስ እስር ቤት እንዳስገባቸዉ ይታወሳል። አራተኛዉ ጋዜጠኛ ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ የት እንዳለ ባለመታወቁ ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ግን ከመንግስት እስር ቤቶች በአንዱ ዉስጥ ሊኖር እንደሚችል ስጋታቸዉን ይገልፃሉ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስከትሎ ሕዝቡ በክፍተኛ ሁኔታ ተቃውሞዉን መግለፁን አስታኮ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ መጀመሩም ይታወቃል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተክትሎ በሕዉሐት ደህንነት ታፍነዉ ወደ ማጎሪያ ቤት የተወሰዱት 11000 እንደሆኑ አቶ ታደሰ ወርዶፋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቦርድ ሃላፊዉ በኖቬምበር 12 20016 በቴሌቪዥን በሰጡት ቃል መግለፃቸዉ ይታወቃል። ይኹን እንጂ ይኼ ቁጥር በአራት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ብዙዎች ይስማማሉ።
የሲፒጂ አፍሪካን ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አንጄላ ኩይንታል ከኒዮርክ እንደገለፁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንም አይነት መረጋጋትን እንዳላመጣም አያይዘዉ ገልፀዋል። የ2015 የአለም አቀፉን የነፃ ፕሬስ ሽልማት የተቀበለዉ የብሎግ ዘጠኝን ከመሰረቱት አንዱ የሆነዉ በፍቃዱ የሕዉሐት ደህንነት ሰዎች መልሰዉ እንዳሰሩትም ሲታወቅ የታሰረበትን ምክንያት ጓደኛዉ እንደገለፀዉ ለቮይስ ኦፍ አሜሪካ መንግስት ሰልፍ በወጣዉ ሕዝብ ላይ የወሰደዉን እርምጃ አስመልክቶ በሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ሊሆን እንደሚችልም ገልጿል። እስከአሁንም ድረስ ምንም አይነት ክስ ያልተመሰረተበት ሲሆን የታሰረበትንም ምክንያት አልተገለፀም።
ሲፒጄ ለኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ ነገሬ ሌንጮ የስልክም የቴክስትም ጥያቄ አቅርቦ ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን በዘገባዉ ገልጿል። የዞን ዘጠኝ ብሎገር የሆነዉ ናትናኤል ፈለቀ ባለፈዉ ኦክቶምበር 4 ምግብ ቤት ዉስጥ በሰጠዉ አስተያየት በደህንነቶች ታፍኖ የተወሰደ መሆኑም ይታወሳል። የኢትዮ ምህዳር አዘጋጅ የንበረዉ ጌታቸዉ ወርቁም አዲስ አበባ ዉስጥ በቤተ ክህነት ዉስጥ ስላለዉ የገንዘብ ብክነት በፃፈዉ ፅሑፍ ምክንያት ኖቬምበር 15 2016 አንድ አመት እንደተፈረደበትም አያይዞ ዘግቧል። አብዲ ገዳ የተባለዉ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ እንዲሁ ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ የተሰወረ ሲሆን ቤተስቦቹና ጓደኞቹ በስደት ላለዉ ድምፅ አልባ ለሆኑት ድምጽ እንሁናቸዉ ለሚባለዉ ጋዜጣ መናገራቸዉን ጋዜጣዉ ጨምሮ ዘግቧል።
በፍቃዱ ኃይሉ፤ ናትናኤል ፈለቀ፤ አቤል ዋቤላ፤ እና አጥናፍ ብርሃኔ በኦክቶምበር 2015 በአሸባሪነት ክስ ተከሰዉ ፍርድ ቤት መቅረባቸዉ ይታወሳል። –
No comments:
Post a Comment