Friday, November 18, 2016

ዋናው ትኩረት Abebe Gellaw


ወያኔ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሞና አማራ ክልሎች መጠነ ሰፊ አፈና፣ ሰቆቃ፣ ዝርፊያና ግድያ በመፈጸም ላይ ይገኛል። ይህንን ሃቅ ዘንግተን የምናደርገው አላስፈላጊ የቃላት ልውውጥ ውጤቱ ለወያኔ እፎይታን ለህዝባችን ደግሞ ቅስም ከመስበር ያለፈ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ሁላችንም ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል። ስለሆነም ሙሉ ትኩረታችን ወያኔ ላይ ይሁን።
ለነጻነት እንታገላለን ብለን የተንሳን ሁሉ አላስፈላጊ ጉዳዮችን ሁሉ ችላ ብለን ዋነኛው የጋራ ጠላችን ላይ እናተኩር። ሁላችንም ለወሳኙ ትግል እንነሳ። ወያኔ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያወጀውና በቀውስ የሚናወጠው በብዙ ንጹሃን ሰማእታት መስዋእትነት መሆንኑ ሳንዘነጋ ለፋሺስቶች ፋታ አንስጣቸው።
አላማ ላለለው ስድብ ጉዳት አያደርስም። የሚጎዳን በህዝባችን ላይ ዘውትር የሚርከፈከፈው ጥይት ነው። እንኳን ለሚሰድቡን ለሚመርቁን መልስ መስጠቱን ትተን ትግሉን በአንድነት እና በጽናት ከዳር ለማድረስ ሁላችንም በጽናት እንታገል። ብዙ የህዝብ ልጆች የተሰውለትን አላማ አንዘንጋ።
በዚሁ አጋጣሚ በተለያየ ጊዚያት ምክርና ማበረታቻ ለለገሳችሁን ወገኖቻቸን ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ። ጠንካራ ጎናችንን እያጎለበትን ድክመታችንን እያረምን ትግላችንን በጽናት እንቀጥላለን። ህዝባዊ አደራን ለመወጣት ቃላችንን አናጥፍም!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!Bilderesultat for abebe gelaw

No comments:

Post a Comment