Tuesday, November 1, 2016

ወያኔ የካቢኔ ሹም ሽር አደረገ

መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከአንድ ዓመት በላይ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ሲካሄድ የነበረው ህዝባዊ ተቋውሞ ወያኔን ታዋቂው ምሁርና ጸሃፊ ፕሮፌሰር አል ማሪያም ከአንድ ሳምንት በፊት ባወጡት ጽሁፋቸው የተነበዩትን የማታለያ እና የማደናገሪያ ለውጥ አንዲአደርግ አስገደደው።የሰጡትን ተቀብሎ ከአለምንም ጥያቄ  የሚአፀድቀው ጥርስ አልባው የሕዝብ ምክርቤት ተወካዮችም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የአቀረቧቸውን አዲሱን ካቢኔአቸውን በሙሉ ድምፅ አጽድቀውላቸዋል።

ወያኔ የተነሣውን ተቋውሞ ለማብረድ፤ የገንዘብ እርዳታ የሚአፈሱለትን የውጭ አገር እርዳታ ሰጭዎችን እና የኢትዮጵያን ሕዝብን እንደተቀየረ ለማሳመን ከስርአቱ ውጭ ሳይወጣ ሌሎቹን ታማኞቹን በመተካት ያደረገው የጉልቻ ለውጥ ነው በማለት ለሌላ ዙር ወያኔ ሙሉ በሙሉ የፖለቲካ ሲስተሙን እና መዋቅሩን ተቆጣጥሮ እንደያዘው የሚቀጥልበትን መንገድ ነው አሁንም ያደረገው በማለት የካብኔ ሹም ሽሩን ብዙ የተቃዋሚ ፓሮቲዎችና አክቲቪስቶች ተቃውመውታል።ለማንኛውም አዲስ ተሿሚዎቹና ነባሮቹ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስም ዝርዝር እድሚከተለው ነው።
አዲሶቹ ተሿሚዎች
  1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  2. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
  3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
  4. ዶክተር በቀለ ጉላዶ፦ የንግድ ሚኒስትር
  5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፦ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር
  6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር
  7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
  8. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚኒስትር
  9. ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
  10. ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፦  የኮንስትራክሽን ሚኒስትር
  11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
  12. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅናየ ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
  13. ዶክተር ገመዶ ዳሌ፦ የአካባቢ ደን ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
  14. ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም፦ የትምህርት ሚኒስትር
  15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
  16. ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
  17. ዶክተር ሒሩት ወልደማርያም፦  የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
  18. ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ፦  የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
  19. አቶ ርስቱ ይርዳው፦ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር
  20. አቶ ከበደ ጫኔ፦ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኃላፊ ሚኒስትር
  21. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፦ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር


የቀድሞቹ እንዳሉ እንዲቆዩ የተወሰነው
  1. አቶ ደመቀ መኮንን፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
  2. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፦ የመከላከያ ሚኒስትር
  3. አቶ ካሳ ተክለብርሃን፦ የፌዴራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር
  4. ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል፦ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
  5. አቶ አህመድ አብተው፦የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
  6. አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፦የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
  7. ዶክተር ይናገር ደሴ፦ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
  8. አቶ ጌታቸው አምባዬ፦ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
  9. አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ምንጭ አባይ ሚዲያ  ሱራፌል አስራት የእንግሊዝኞው ክፍል

No comments:

Post a Comment