ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ ራሳቸውን ያደራጁ የነጻነት ሃይሎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ለሳምንት የዘለቀው ፍጥጫ ዛሬም ቀጥሎአል። የቡድኑ አስተባባሪ ለኢሳት እንደገለጸው፣ ቀደም ብሎ ተደርጎ በነበረው የተኩስ ልውጥ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ምንም እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች አካባቢውን ከበው በመጠባበቅ ላይ ቢሆንም፣ ጫካ የገቡት ሃይሎች አሁንም በጥሩ የጥንካሬ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። አገዛዙ በሃይማኖት አባቶች በኩል እጃችንን እንድንሰጥ ጥረት ቢያደርግም፣ እኛ ግን የሚደርስብንን ስለምናውቅ እጅ ለመስጠት ፍለጎቱ የለንም ብለዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው አስተባባሪው ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል በርካታ ቁስለኛ የስርዓቱ ወታደሮች በጎንደር ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በአገዛዙ ወታደሮችና በእያካባቢው እየተደራጁ በሚታገሉ የነጻነት ሃይሎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ለውውጥ እንደሚካሄድ የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
No comments:
Post a Comment