ዞን ዘጠኝ በሚል ስያሜ ከሚታወቁት የድረ-ገጽ ጸሐፍት መካከል በፍቃዱ ኃይሉ በድጋሚ መታሰር እንዳሳሰበዉ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት «RSF» ዛሬ አስታወቀ። በፈቃዱ ኃይሉ ከሕዳር ሁለት ጀምሮ እስር ላይ እንደሚገኝ የገለፀዉ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ከመስከረም 29 ጀምሮ የመረጃ ነጻነት ከድሮዉi ይበልጥ መደፍለቁን ገልጾአል።
በፈቃዱ በጎርጎርጎረሳዉያኑ 2014 ዓ,ም ከሌሎች አምስት የዞን ዘጠኝ አባላት ጋር በፀረ-ሽብር ሕግ ተከሶ ለ 18 ወራት እስር ላይ እንደነበር መግለጫዉ ያትታል። ዞን ዘጠኝ የድረ-ገጽ ጻሕፍት ባለፈዉ ዓመት ከድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በጡመራ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽዖ የዓመቱን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተቀብለዉ እንደነበር ይታወሳል። ድርጅቱ የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ያሳስባል።
No comments:
Post a Comment