Monday, March 9, 2015

የ300 ሚሊየን ብር እርዳታ ለጤና ጣቢያ ግንባታ…የተባለውን ቅርጥፍ…

የ300 ሚሊየን ብር እርዳታ ለጤና ጣቢያ ግንባታ…የተባለውን ቅርጥፍ…..
መርካቶ ሲኒማ ራስ የዛሬን አያርገውና ገናናው አሜሪካን ግቢ ድሀዎችን በልማት ስም በማስነሳት/ጤና ጣቢያ ልንገነባ ነው ብለው ያፈናቀሉትን ህብረተሰብ ወደ ጎን አድርገው ዛሬ ኡራጎ የንግድ ማዕከል የሚል ሰርተውበት በሙስና በልጽገው ጠፍተዋል፡፡ ይህ ህንጻ ለማሰራት ተነሺዎችን ጤና ጣቢያ ሊሰራ ነው ለልማት ነው ብለው ካስነሱ በኋላ በብዙ ሚሊየን በሚቆጠር ብር መሬቱን ሽጠው አሁን የንግድ ማዕከል ሆኗል፡፡ በወቅቱ ግሎባል ፈንድ የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት 300 ሚሊየን ብር እርዳታ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ገንዘቡ የት እንደገባ አይታወቅም፡፡ የአሜሪካን ግቢ የኢህአዴግ ኮካዎች ላደረሱኝ መረጃና ፎቶ ከልብ አመሰግናልሑ፡፡ የስርዓቱን የሙስና ደረጃና አድሎአዊነት በየጊዜው እያጋለጥን ትግሉን ማቀጣጠል

አለብን፡፡


No comments:

Post a Comment