Thursday, March 12, 2015

የጎሳ ፌዴራሊዝም መርዝ በኢትዮጵያ (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሀሰት እና የሸፍጥ የተውኔት መድረክ የተንጸባረቀበትን ህገመንግስት አርቅቆ እ.ኤ.አ ታህሳስ 8/1994 በማጽደቅ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጫነ፡፡ በህገ መንግስቱ ሰነድ የመጀመሪያ መግቢያ መንደርደሪያ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ሰፍሮ ይገኛል፣ ”እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች…

March 11, 2015
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሀሰት እና የሸፍጥ የተውኔት መድረክ የተንጸባረቀበትን ህገመንግስት አርቅቆ እ.ኤ.አ ታህሳስ 8/1994 በማጽደቅ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጫነ፡፡ በህገ መንግስቱ ሰነድ የመጀመሪያ መግቢያ መንደርደሪያ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ሰፍሮ ይገኛል፣ ”እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች…
1ኛ) የብሄሮችን፣ ብሄረሰቦችን እና ህዝቦችን የእራስን ዕድል በእራስ ለመወሰን፣
2ኛ) ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የየእራሳቸውን አካባቢያዊ ግዛት እራሳቸው እንዲያስተዳድሩ እና የበለጸገውን እና የኩራታችን አሻራ የሆነውን የባህል ቅርሶቻቸውን በመያዝ በአንድነት እንዲኖሩ ለማስቻል፣
3ኛ) ለዘመናት ተንሰራፍተው የኖሩትን ፍትሀዊ ያልሆኑ ግንኙነቶችን ለማስተካከል፣ እና
4ኛ) አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ በመፍጠር ዕድገትን ለማፋጠን ይህ ህገመንግስት ተዘጋጅቷል” ይላል፡፡
አነጣጥሮ ለመመልከት ደግሞ የአሜሪካ ህገ መንግስት በመገቢያው አንቀጾች ላይ የሰፈረው መንደርደሪያ እንዲህ ይላል፣ “እኛ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ህዝቦች እንከን የሌላት ሀገርን ለመፍጠር፣ ፍትህን ለማስፈን፣ የሀገር ውስጥ ሰላም እና ጸጥታን ለማስፈን፣ የጋራ መከላከያችንን ለማጠናከር፣ የህዝቡን የኑሮ ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የእኛን እና የመጭውን ትውልድ ነጻነት ለመጠበቅ ሲባል ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ይህንን ህገ መንግስት አዘጋጅተናል፡፡“The Poison of Ethnic Federalism in Ethiopia’s Body Politic
የህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝቦች እንደ ከብት መንጋ በአካባቢ በመለያየት ወይም ደግሞ
በመበታተን እርስ በእርሳቸው የጎሪጥ በመተያየት የጥላቻ መንፈስ እንዲፈጠር እና ጎሳዊ፣ አካባቢያዊ እና መንደርተኛ አስተሳሰብ እንዲፈጠር በማድረግ የአንድነት ስሜት እንዳይኖራቸው እና አንዲት ጠንካራ ኢትዮጵያ እንዳትኖር በማድረግ በጎሳ ከፋፍሎ ለመግዛት የታለመ እና እንከንየለሽ አንድነትን ሳይሆን መለያየትን ለመፍጠር የተዘጋጀ የሸፍጥ ህገ መንግስት ነው፡፡ ህወሀት የኢትዮጵያን ህዝቦች በዘር፣ በቋንቋ፣ በባህል እና በአካባቢያዊነት ወይም በመንደርተኝነት በመከፋፈል ለዘመናት ተከባብሮ፣ ተዋዶ እና ተዋልዶ የኖረውን ህዝብ ማህበራዊ ትስስር፣ ፍቅር እና እርስ በእርስ መግባባት ሊመለስ በማይችል መልኩ ለዘመናት ለማጥፋት በማሰብ ይህንን እርባናየለሽ የሸፍጥ ህገ መንግስት አዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጭኖት ይገኛል፡፡

የህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን የሸፍጥ ከፋፋይ ህገ መንግስት የተዋቀረበት መሰረታዊ ዓላማው አንዲት ሉዓላዊ ሀገር ኢትዮጵያ እና አንድነቱ የተጠበቀ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለውን አስተሳሰብ በማጥፋት እና በመናድ ህዝቦችን በመንደርተኝነት በመከፋፈል ህዝቦች እርስ በእርሳቸው በጎሳ እና በድንበር እየተወዛገቡ እርስ በእርስ ሲነታረኩ እና ሲጭራረሱ እንዲኖሩ በማድረግ እርሱ አጋጣሚውን እየተጠቀመ የግዛት እድሜውን ለማራዘም የዘየደው እና እየተገበረው ያለው ዕኩይ ምግባር ነው፡፡ ከፋፍሎ እና አደህይቶ አቅምን አሳጥቶ መግዛት ከማቻቬሌ ዕኩይ ፍልስፍና የወሰዱት ዕኩይ ስሌት ነው፡፡ በወያኔ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚባል ነገር ቦታ የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ባህል የሚባል ምንም ዓይነት ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባል ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያውያን/ት የብሄራዊ ማንነት የሚባል ጥያቄ የለም፡፡ የሀገር አንድነት ተምሳሌት የሆነችው ሰንደቅ ዓላማ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ተራ ጨርቅ እንጅ የነጻነት ተምሳሌት ቀንዲል አይደለችም፡፡ ለወያኔ ኢትዮጵያ ህልም የላትም፣ የምትኖረው እና የምትተዳደረው በእርሱ ሰይጣናዊ የቅዠት ዓለም ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በወያኔ ድሁር አስተሳሰብ ኢትዮጵያ የምትባል ሉዓላዊ ሀገር አልነበረችም፣ አሁንም የለችም፣ ወደፊትም አትፈጠርም! የተደረገው ነገር ቢኖር በዘፈቀደ በተዘጋጅ ዘርን እና ጎሳን መሰረት ባደረገ መልክ ዓምድራዊ ግዛት በመሸንሸን በዓለም አቀፍ ህግ እንደሚባለው የመከራ ጊዜን ማራዘም እና በጎሳና በጎጥ መንደርተኛ ገዥዎች እጅ የወቀደቀች የየብሄሮች እና ብሄረሰቦች ስብስብ ናት፡፡ የማስመሰያ የብሄሮች እና ብሄረሰቦች ኮንፌዴሬሽን አለ ለመባል ብቻ የማደናገሪያ ስልታቸውን ፈጥረው አሳር ፍዳዋን በማሳየት ላይ የሚገኙባት ምናባዊት ኢትዮጵያ ብቻ ናት በአሁኑ ጊዜ ያለችው፡፡
የአሜሪካ ህገ መንግስት በቅኝ ግዛት ተይዘው የነበሩትን 13 የአሜሪካንን ግዛቶች አንድ በማድረግ ዩናይትድ (የተባበሩት ያሜሪካ ግዛቶች ) ስቴትስ አሜሪካንን እውን ለማድረግ እና አንድ ህዝብ አንድ ሀገር ለመፍጠረ ነው የተፃፈው፡፡ የአሜሪካ ህገ መንግስት የ13ቱን ግዛት ህዝቦች ወደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በማምጣት እንከንየለሽ ሀገር ለመፍጠር፣ ፍትህን ለማስፈን እና ሰላምን መረጋጋትን እና ለማረጋገጥ፣ የጋራ መከላከያ ለማቋቋም፣ ጠቅላላ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እና አሁን ላለው ህዝብ እና ለመጭው ትውልድ ነጻነትን ለማጎናጸፍ የተዘጋጀ አጠቃላይ የሆነ መሪ ሰነድ ነበር፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛትነት ለመላቀቅ ያካሄደችውን ጦርነት ተከትሎ በተበታተነ መልኩ ጉዞዋን ጀመረች፡፡ አሜሪካውያን በቀድሞዎቹ የእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎቻቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ ታሪካዊ ቅሬታ ነበራቸው፡፡ ታሪካዊ ቅሬታዎቻቸው አሜሪካውያን አንድ የሚያደርግ እና የሚያያይዝ ሙጫ ሆኖ አንድነታቸውን የበለጠ አስተሳስሮ በታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ህገ መንግስታቸውን እንዲያዘጋጁ እና በኮንፌዴሬሽን እንዲተዳደሩ አስቻላቸው፡፡ አዲሱ የሚቋቋመው መንግስት በቅኝ ገዥ አለቆቻቸው ላይ የነበራቸውን ቅሬታ የበለጠ አጠናክሮ ይቀጥልበታል በሚል እምነት ጥርስ የሌለው ሀገራዊ መንግስት በማቋቋም ተጠናቀቀ፡፡ እ.ኤ.አ በ1787 ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን በማቋቋም የነበረባቸውን ቅሬታ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ሰጡት፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ህገ መንግስት ታሪካዊ ኢፍትሀዊነትን ለማስወገድ በሚል እራሱን መሳሪያ አድርጎ አስቀመጠ፡፡ ህገ መንግስቱ ታሪካዊ ኢፍትሀዊንትን ለማስወገድ በሚል ማደናገሪያ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የእራሳቸውን ዕድል በእራሳቸው የመወሰን መብት እስከ መገንጠል የሚል የኒኩሌር ጦር መሳሪያ አስታጠቃቸው፡፡ ብሄሮች እና ብሄረሰቦች ህዝብን ለመጨረስ የሚያስችለውን የኒኩሌር ጦር መሳሪያ የያዘውን ሳጥን ለእያንዳንዳቸው ተሰጥቷቸው አራሳቸዉንም ጠቅላላ አገሪቱንም አፈንድተው ሁሉም ባንዴ አንዲጠፉ አዘጋጅተዋል ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ህገመንግስት አንድ ዓይነት የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሳይሆን አንድ ዓይነት ማህበረ ኢኮኖሚን ለመፍጠር እና ለማረጋገጥ ነው ዓላማ አድርጎ ተነሳው፡፡ ለዚያ አንድ ዓይነት ማህበረ ኢኮኖሚ መፈጠር ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተሩ ደግሞ በወያኔ ቁጥጥር ስር የተያዘው ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) እየተባለ የሚጠራው ኦዲተር የማያውቀው የሀገሪቱን ምጣኔ ሀበት ከ50 በመቶ በላይ የተቆጣጠረው የዘረፋ የንግድ ድርጅት ነው፡፡ እንደ ማረት የቀድሞው ሊቀመንበር መግለጫ ከሆነ የማረት ኩባንያዎች ለባንክ ብድር እና የውጭ ምንዛሬን ለማግኘት ወይም ደግሞ በመንግስት ጨረታ እና የኮንትራት ስራዎች እንዲሁም የጉምሩክ ቀረጥ አከፋፈል እና የአስመጭ እና ላኪ ፈቃድ ከማግኘት አንጸር የተለየ እድል ይሰጣቸዋል፡፡
የአሜሪካ ህገ መንግስት እንከንየለሽ አንድ ዓይነት የፖለቲካ ማህበረሰብ እንጅ አንድ ዓይነት ማህበረ ኢኮኖሚን ለመፍጠር ዓላማ አላደረገም፡፡ በአሜሪካ ህገ መንግስት የፖለቲካ አንድነት እንዲፈጠር የተደረገበት ዋናው ምክንያት ህዝቦች ነጻነታቸውን እንዲጎናጸፋ ለማስቻል ነው፡፡ እንከንየለሽ የፖለቲካ ውህደት የሚኖር ከሆነ የኢኮኖሚ ውህደት እና የማይገሰሰው በህይወት የመኖር፣ ነጻነት እና ሀብትን በማከማቸት የንብረት ባለቤት በመሆን በደስታ የመኖር መብት በእራሳቸው የሚከተሉ እና የሚመጡ ይሆናሉ፡፡
የወያኔ ህገ መንግስት ለኢትዮጵያ መበታተን እና መፈረካከስ የመጨረሻው ሰነድ ነው፡፡ ይህ ህገ መንግስት ሀገራዊ ጥፋትን ለማምጣት የጎሳ ጥላቻን የሚነዛ፣ በድብቅ በጨለማ ውስጥ የጭቆናን ዘር በጠርሙስ ውስጥ በማብቀል በሀገሪቱ ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነት እና የጎሳ ጥላቻ እንዲነሳ በማድረግ የዘራውን ለማጨድ ሌት ከቀን በመውተርተር ላይ ይገኛል፡፡ የወያኔ ህገ መንግስት በቅጥፈት በመታገዝ እንዲቀጣጠሉ የሚፈለጉ ታሪካዊ ኢፍትሀዊ ግንኙነቶች በሚል በብቸኝነት በተቆጣጠራቸው የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም እየዘራ ያለው አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ መጨረሻው ወደ ኋላ በመሄድ የዘር ጥላቻን በመቀፍቀፍ የጋራ ሀገራዊ እልቂት እና የአርማዴዎን የምጽአት ቀን እንዲመጣ አበርትቶ መስራት ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን ህገ መንግስት ላረቀቁት እና ላጸደቁት ዓላማው በወቅቱ ለነበረው ትውልድ ጥቅም ብቻ ሲባል የተዘጋጀ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ያ ህገ መንግስት በተከታታይ ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ ነበር፡፡ እንከን በእንከን ላይ ተቆልሎ የተዘጋጀ እንደ ወያኔ ያለ ህገ መንግስት ዓይነ ስውርን አገልጋይ ባሪያ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑ እውነት ነው፡፡ የዚህ ዓይነት እኩይ እና እርባናየለሽ ህገ መንግስት ዜጎችን በዘር፣ በቀለም እና በጾታ ላይ አድልኦ በማድረግ በህዝብ ምርጫ መሳተፍ እንዳይችሉ ያደርጋል፡፡ ሆኖም ግን ከተረቀቀ ከ228 ዓመታት በኋላ የአሜሪካ ህገ መንግስት ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፖለቲካ የመሰረት ድንጋይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በአራት የተለያዩ ወቅቶች የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ዊሊያም ግላድስተን የሚከተለውን ምልከታ አድርገው ነበር፣ “የእንግሊዝ ህገ መንግስት ለዘመናት በዘለቀው ታሪክ ተጸንሶ፣ ተወልዶ እና አድጎ አሁን ላለበት ደረጃ የበቃ በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰነድ እንደመሆኑ ሁሉ የአሜሪካ ህገ መንግስትም በተመሳሳይ መልኩ እኔ እንደማየው በጣም የተደነቀ ስራ እና በተወሰነ ጊዜ በሰው ልጅ ጭንቅላት ተረቅቆ ለሰው ልጅ ጥቅም የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡“ ብለው ነበር።
“ኢትዮጵያ የጨነገፈ (failed state) መንግስት ሰነድ”፣
በቅርቡ “ኢትዮጵያ የጨነገፈ መንግስት ሰነድ”፣ በሚል ርዕስ 54 ደቂቃ የሚወስድ ዘጋቢ የቪዲዮ ፊልም በየቱቢ ተለቅቆ ነበር፡፡ ዘጋቢ የቪዲዮ ፊልሙ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች በገልፅ ለመናገር ለመዎያየት የሚፈሩበት አሳሳቢ ጥያቄዎች ላይ ግልጥልጥ ያለ ዘገባ አቅረቧል ። ዘጋቢ ፊልሙ አሁን ያለው ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ከጨነገፉ (failed state) የአፍሪካ መንግስታት ዝርዝር ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የተሰጠው መልስ በጣም አስፈሪ እና እንዲህ የሚል ነው፡፡ ኢትዮጵያ በመበታተን ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እና ጥላቻ በመግባት በመጨረሻም እንደ ጎረቤቷ ሶማሊያ የሽብር ጥቃት ሰለባ ወደ መሆን የምጽአት ቀን ትሸጋገራለች፡፡
በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የቀረቡት እና የተገመገሙት ጉዳዮችና ማስረጃዎች ሁሉ አሳማኝ ሁሉን አቀፍና ለሙገት የማይመች ትንተናዎች ናቸው፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ ኢትዮጵያ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ጭቆና፣ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የአፍሪካ የጨነገፈች መንግስት የመሆን መጥፎ ዕድል እንደሚገጥማት ያመላክታል፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ በህወሀት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ እንዳሉ እና በአማራ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሞ ህዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት እና የጎሳ ማጽዳት ወንጀሎች በህወሀት የተፈጸሙ ለመሆናቸው አሳማኝ እና አስደንጋጭ የሆኑ ማስረጃዎች እንዳሉ ግልጽ አድርጓል፡፡ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የምዕራብ ለጋሽ ድርጅቶች ዶላር ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) እየተባለ በሚጠራው በኢትዮጵያ በገቢ እና በሀብት እንዲሁም በህወሀት ፖለቲከኞች ልጆች ስም በውጭ ሀገር ባንኮች ሂሳብ እየተከፈተ የሚቀመጥ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የሚመጣን የእርዳታ ገንዘብ የሚዘርፍ ትልቅ የሆነው ኮርፖሬሽን እንደሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡
ይህ ዘጋቢ ፊልም የህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን “ሸፍጠኛውን የጸረ ሽብር ህግ” በመጠቀም እንዴት አድርጎ ንጹሀን ዜጎችን በሸፍጥ እንደሚያስር፣ እንደሚያስፈራራ እና የተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን እና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ሰዎችን የጥቃት ሰለባ እንደሚያደርግ በግልጽ ያሳያል፡፡ ይህ ዘጋቢ ፊልም ወያኔ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በፖለቲካ በመፈረጅ እና የእምነቱን ቀኖናዊ ህግ በመጣስ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ መብት በመደፍጠጥ ላይ እንደሚገኝ፣ እንዲሁም ሌሎችን የቤተክርስቲያኒቷን ልምዶች እና ተሞክሮዎች ሁሉ እያፈረሰ እና የፖለቲካ እምነቱ ደጋፊዬ አይደሉም ብሎ የሚፈርጃቸውን እና በእምነታችን ላይ የፖለቲካ ጣልቃገብነት ይቁም የሚሉትን የቤተክርስቲያን አባቶች እያሰቃዬ እንደሚገኝ ያመላክታል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ይህ ዘጋቢ ፊልም ወያኔ በእስልምና እምነት ተከታዮች እና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መካከከል ጥላቻን ለመፍጠር እና እርስ በእርሳቸው ለማጋጨት ጥረት ማድረግ እና ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የሙስሊም ማህበረሰብ የእምነት ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ጣልቃ እየገባ የዜጎችን የእምነት ነጻነት እንዴት አድርጎ በመደፍጠጥ ላይ እንደሚገኝ ግልጽ አድርጓል፡፡
ይህ ዘጋቢ ፊልም ወያኔ የሀገሪቱን ምርጥ የሆነ ለም እና ድንግል መሬት እየመረጠ ከውጭ ሀገር ለሚመጡ ምንም ዓይነት የንግድ የሞራል ስብዕና ለሌላቸው ዘራፊዎች በርካሽ ዋጋ በመቸብቸብ እንዲሁም የዓለም ባንክ፣ የእንግሊዝ መንግስት እና ሌሎችም ለጋሽ ድርጅቶች ለመሰረታዊ አገልግሎቶች በሚል የሚሰጡትን የእርዳታ ገንዘብ በሙስና እና በዝርፊያ እየወሰደ የእራሱን የሂሳብ አካውንት በውጭ ባንኮች በመክፈት የዝርፊያ ገንዘቡን በእነዚህ የሂሳብ አካውንቶች እያጨቀ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ደኃ ዜጎችን በመንደር ምስረታ ስም ከቀደምቶቻቸው ጀምሮ ሲኖሩበት ከቆየው ቀያቸው እያፈናቀለ አሳር እና መከራ እያሳያቸው መሆኑን በግልጽ ጠቁሟል፡፡
ባለፈው ሳምንት የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉት ግድቦች፣ መንገዶች እና ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በሚል በብድር መልክ ይሰጠው የነበረው ገንዘብ ለተባለው ዓላማ በአግባቡ በስራ ላይ እንዳልዋለ እና የባንኩ ህጎች እንደተጣሱ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የእንግሊዝ መንግስት ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ በኢትዮጵያ ለሰፈራ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ይሰጥ የነበረውን 4.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ያቋረጠ መሆኑን ከሳምንት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ ዘጋቢ ፊልም ወያኔ የፍትህ ስርዓቱን በማኮላሸት የዝንጀሮ ፍርድ ቤት እንዲሆን በማድረግ ፍትህን በጨረታ ከፍተኛ ገንዘብ ላቀረቡለት እና ከእርሱ ጋር የፖለቲካ የትስስር ግንኙነት ላላቸው መሸጡን በግልጽ ያመላክታል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ዘጋቢ ፊልሙ በወያኔ የስቃይ ኑሮ ምክንያት በሀገራቸው ምድር ላይ ተስፋን በማጣት ብዛት ያላቸው የሀገሪቱ ወጣቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንደ ደራሽ ውኃ በመጉረፍ በርካሽ ከፍያ ጉልበታቸው እየተበዘበዘ እና ሰብአዊ መብታቸው እተደፈጠጠ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ የወታደር እና የደህንነት ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ በብቸኝነት 95 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎችን ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ግልጽ አድርጓል፡፡
ይህ ዘጋቢ ፊልም ዩኤስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ባላት ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ክስ ያቀረበባት ሲሆን ዩኤስ አሜሪካ የወያኔ ዋነኛ የገንዘብ ምንጩ ስለሆነች አሁን እየሆነ ያለውን ጉዳይ በአንክሮ በመመልከት ሁኔታውን ቀድሞ ወደነበረበት እንዲመለስ ጥረት የማታደርግ ከሆነ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ደም በእጇ ላይ እንደሚኖር ይፋ አድርጓል፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ እንዲህ በማለት ማጠቃለያ ሰጥቷል፡
ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ ላይ ትገናለች፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም የሚያበረታታ አይደለም፡፡ ሙሉ በሙሉ የጨነገፈች ሀገርን በመምራት ሶማሊያን፣ ሶሪያን እና ኢራቅን ልትቀላቀል ትችላለች፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ውጥረት እና ግጭት ከመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰ ስለሆነ በአሁኑ ጊዜ ቅንጣት የሆነች ነገር እንደ ሰበብ ሆና ወደ አጠቃላይ ቀውስነት ሊያመራ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በጎሳ፣ በኃይማኖት እና በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ የሚታዩ ግጭቶች እና ውጥረቶች ትዕግስትን ከመላበስ በላይ ዘልቀው ወጥተዋል፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ገና ከመጀመሪያው የኢትዮጵያን ህዝቦች ዋና ማሰሪያ የሆኑትን የኃይማኖት እና የመቻቻል ክሮችን በጥሶ ጥሏልና… ይህ ድርጊት በአሁኑ ጊዜ ተሸርሽሮ አልቆ ህልውናው አክትሟል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለችው ኢትዮጵያ በበቀል፣ በጥላቻ፣ ባበዶ ዲስኩር እና በርዕዮት ዓለም ፍልስፍና የተሞላች፣ ሆናለች… የወያኔ የጎሳ አገዛዝ በዘር ማጥፋት እና በእርስ በእርስ ጦርነት የተላለቁት የሩዋንዳ እና የዩጎዝላቪያ ቅሪት ነው…
በእርግጥ የወያኔ አመራሮች እንደዚህ በትዕቢት ተወጥረው በህዝብ ላይ እየጨፈሩ ያሉበት ጊዜ ተጠናቅቆ ለፈጸሙት የዘር ማጥፋት፣ የእልቂት እና የመከራ ህይወት ለፍትህ አካል በሚቀርቡበት ጊዜ ይህ ጠንካራ ዘጋቢ ፊልም ለፍትህ አካሉ በፍርድ ሸንጎ የመክፈቻ ክርክር ላይ በዋናነት በማስረጃነት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ በሰዓት እንደተሞላ ቦምብ?
ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ በአንድ ወቅት እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፣ “ሰላማዊ አብዮትን የማይቀበሉ ሁሉ መራራውን አብዮት እንዲያስተናግዱ ይገደዳሉ“፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የጆን ኬኔዲን የምልከታ እውነት እንደሚ ገነዘቡት አያጠራጥርም፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በሰዓት በተሞላ ቦምብ ላይ ተቀምጠው እንዳሉ ያለምንም ጥርጥር ይገነዘቡታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከዚህ ቀደም እንደጻፍኩት ሁሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሸዋ ላይ ህንጻ ገንብቷል፡፡ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛው ጥያቄ ግን ይህ ግንብ የሚደረመሰው ጥልቅ በሆነ አልገዛም ባለ ህዝባዊ ማዕበል ነው ወይስ ደግሞ እጅግ በጣም በተቆጡ እና ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ ህዝቦች ማዕበል ነው የሚለው ነው፡፡ በየትኛቸውም መንገዶች ይሆኑ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ባዶ ሆኖ ከነቅሌቱ በታሪክ የቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ አንደምጣል ብዙ ምልክቶች ይታያሉ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማያውቀው ከሆነ ሊያውቀው የሚገባ አንድ ዘላለማዊ የሆነ የታሪክ ህግ አለ፡፡ ያህንን ህግ የቀመሩት ማህተመ ጋንዲ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላል፣ “ለጊዜው ምንም ሊሞከሩ እና ሊደፈሩ የማይችሉ መስለው የሚታዩ አምባገነኖች እና ነፍሰ ገዳዮች አሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁሉም ተንኮታኩተው ይወድቃሉ – ተገንዘቡት ሁልጊዜም ተንኮታኩተው ይወድቃሉ፡፡“
አሁን በህይወታችን ያየናቸው እና ወዠቦ እንደመታው ዛፍ እየተገነደሱ የወደቁትና የተንኮታኮቱ እምነተቢስ አምባገነኖች የሚከተሉት ናቸው፡ ዚን አል አቢዲን ቤን አሊ፣ ሙአማራ ጋዳፊ፣ ሆስኒ ሙባረክ፣ ብሌይስ ኮምፓወሬ፣ ሳዳም ሁሴን፣ ፖለ ፖት፣ ሚልተን ኦቦቴ፣ ኢዲ አሚን፣ መንግስቱ ኃይለማርያም፣ መለስ ዜናዊ፣ ሞቡቱ ሴሴኮ፣ ሴኩ ቱሬ፣ ካሙዙ ባንዳ፣ ሲያድ ባሬ፣ አጎስቶ ፒኖቼ፣ ኒኮላ ቻውሴኮ፣ ስሎቦዳን ሚሎሴቪክ፣ ጂን ክላውዴ ዱቫሌር፣ ፈርዲናንድ ማርቆስ፣ ፉልጌኒሾ ባቲስታ፣ አናስታሲዮ ሶሞዛ፣ አንቶኒዮ ሳላዛር፣ አልፍሬዶ ስትሮስነር እና ሌሎች በርካታዎችንም መመልከት ተገቢ ነው፡፡ እናም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከዚህ ጠንካራ የታሪክ ህግ ሊያመልጥ ይችላልን?
የእኔ ትልቁ ስጋቴ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አፈር ድሜ ከበላ እና ግብዓተ መሬቱ ከተፈጸመ እና ወደ ታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ከተጣለ በኋላ የኢትዮጵያ (ወይም የብሄሮች እና ብሄረሰቦች ልበለው) ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው ነው፡፡
“የሻይ ቅጠሎችን ማንበብ፣”
ታዋቂው የአሜሪካ የስፖርት አለማማጅ የነበሩት ላውሬንስ ዮጊ ቤራ በአንደ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “መተንበይ በጣም ከባድ ነገር ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ስለወደፊቱ፡፡“ እንደዚህም ሁሉ ስለኢትዮጵያ ትንበያ መስጠት ከባድ ነገር ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ስለወደፊቱ ሁኔታ፡፡ በመኪና የኋላ መስታወት ወደ ሁዋላ ተመልክቶ የወደፊቱን መንገድ መተመን ነብይ ወይም ደግሞ ምጽአት አቅራቢ ሊያሰኝ አይችልም፡፡ ምናልባትም “የሻይ ቅጠል አንባቢ” ሊያሰኘው ይችል ይሆናል፡፡ ስለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍጻሜ ጨዋታ ከብዙዎቹ ዘገባዎች፣ ጥናቶች፣ የህዝብ መግለጫዎች፣ ትንታኔዎች፣ ትችቶች እና ሌሎች ምንጮች ላይ ቅጠሎችን አንብቢያለሁ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል እንደ መዥገር በኢትዮጵያ ህዝቦች ጫንቃ ላይ ተጣብቆ ከቆየ በኋላ አሁን በፍጻሜው ጨዋታ በመንገዳገድ ላይ እንደሚገኝ አምናለሁ፡፡ ለዚህ ድምዳሜዬ ማስረጃየን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
የመለስ ዜነዊ ህልፈት በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና የግብረ አበር ጥምረቶች፣ ደንበኞች እና ደጋፊዎች ላይ አውዳሚ የሆነ የስነ ልቦና ጫናን አስከትሏል፡፡ መለስ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እኩይ ድርጊት ቀያሽ ጭንቅላት እና ጠንካራ ጡንቻ ነበር፡፡ የእነርሱ አላሚ አሳቢ እና አስፈጻሚ ሁሉ ነገር ነበር፡፡ መለስ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መንግስት መርከብ ነጅ ካፕተን ነበር፡፡ ያ መርከብ በአሁኑ ጊዜ ሾፌር እና የአቅጣጫ ማመላከቻ ኮምፓስ አልባ ሲሆን እየተመራ ያለው ለመሪያቸው መቆየት በሚያስቡ የእርሱን መልአክትነት ሌት ከቀን በሚሰብኩ በተራ የመርከብ ሰራተኞች ቁጥጥር ስር መሆኑን ሳስብ በአንድ ወቅት በዋልት ዊትማን የተቋጠሩ እንዲህ የሚሉት የግጥም ስንኞች ትዝ አሉኝ፡፡
ኦ ጮሌው መርከበኛ፣ የእኛ መርከብ ነጅ፣
መምራትህን ሳይሆን መጓዝህን እንጅ፣
ማስተዋልን ሳይሆን መፍጠንህን እንጅ፣
ጥንቃቄን ሳይሆን ማላተምን እንጅ፤
ከቶ መች ተናግረህ ለዘመድ ወዳጅ፣
መፍትሄ የሚሆን ላገር የሚበጅ፡፡
አስፈሪው ጉዟችን አሁን ተጀምሯል፣
በባህር ማዕበል መናጡን ቀጥሏል፣
ከወዲያ ወደዚህ መምዘግዘጉን ይዟል፣
እያንዳንዱ አካሉ በኃይል ይላተማል፣
መሰበር መፈርከስ መጎዳትን ይዟል፣
እና ምን ይደረግ አቅማችንም ዳሽቋል፣
ሆኖም ግን በጽናት ጉዞ ቀጥለናል፣
የተመኘነውን ሽልማት ወስደናል፡፡
ሆኖም ግን ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መርከብ ባበህር ላይ ተንሳፍፎ በኃይለኛው የባህር ሞገድ እየተናጠ እና እየተንገዳገደ በህዝብ ቁጣ እና የበቀል ጥላቻ ተውጦ ያሸነፈውን ሽልማት ለምን ያህል ጊዜ ነው ይዞት ሊቆይ የሚችለው የሚለው ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በድርጅታዊ አሰራራቸው እና በድጋፍ ሰጭ መዋቅራቸው ላይ የመበስበስ እና ፈጣን የሆነ ውድቀት እያሳየ የመጣበት ሁኔታ የሚታይ በመሆኑ ሌላው ቀርቶ ትንሽ የውጭ ጫና ሊመጣ የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር እንኳ ሊቋቋም የማይችልበት እና ግራ በተጋባ መልኩ የሚደናበርበት ሁኔታን አስተውላለሁ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ቁንጮ የሆኑት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ለበርካታ ጊዚያት በስልጣን ላይ በመጣበቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ህዝብ በማያቋርጥ ሁኔታ በፍርሀት እየራዱ እና የሚይዙት እና የሚጨብጡትን እያጡ ከህዝብም ከፍተኛ የሆነ ጥላቻን እያተረፉ የመጡ በመሆናቸው እጅግ በጣም ተዳክመዋል:: በአሁኑ ጊዜ ሁሉም በሚባል መልኩ በእዕድሜ እያረጁ እና እየጃጁ ነው፣ እናም ሆዳም ሆዱን እንጅ ሞቱን አያይም እንደሚባለው ከኢትዮጵያ ህዝብ የዘረፉትን ግዙፍ ገንዘብ በውጭ ባንኮች በማስቀመጥ እንደገና ሲበሉ ለመኖር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጸሐይ ስትጠልቅባቸው ከሀገር በመኮብለል የዘረፉትን ገንዘብ እየበሉ ለመኖር ብቻ ነው ፍላጎታቸው ፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም አንድ በሆነችበት እና ማንም በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ያደረገ ወንጀለኛ እንደ ቀድሞው ከአንደ ሀገር ተነስቶ ወደሌላው አምባገነን ሀገር በመሄድ የዘረፍኩትን እየበላሁ እኖራለሁ የሚለው አስተሳሰብ ጊዜው ያለፈበት የሞኞች ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ ዓይነት ነገር ነው፡፡ አሁን አንድ ችግር ብቻ አለ፡፡ ይኸውም ከዚህ ቀደም በዝርዝር ለመግለጽ እንደሞከርኩት ሁሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል ተፈናጥጦበት ከቆየው ነብር ጀርባ ላይ በቀላሉ ለመውረድ ድፍረቱን አጥቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቅዠት እየተንጠራወዘ ይህንን በሚያደርግበት ጊዜ የደፈረሱ እና በቁጣ የቀሉ፣ እንደመጋዝ የሰሉ ጥርሶች፣ እንደ ብረት የጠነከሩ መዳፎች እና አንደምስማር የሾሉ ጥፍሮች የያዘ የተራበ እና የተበሳጨ ነብር እንደሚጠብቀው አሳምሮ ያውቃልና!
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መበስበሱን እና እየወደቀ መሆኑን ለመሸፋፈን ሲል በህዝብ ላይ የማታለል ድርጊቱን አሁንም ቀጥሎበታል፡፡ መረጋጋትን ለማምጣት፣ ኃይላቸውን እና የስልጣን የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ መድረኮችን ያዘጋጃሉ፡፡ ዓመታዊ በዓላቸውን በማክበር ስለምርጫ ተብየው ብዙ ይደሰኩራሉ፡፡ ታሪካቸውን ለማራመድ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የወደቀውን የሰብአዊ መብት ገጽታቸውን ለመጠጋገን ሲሉ የህዝብ መገኛኛ ድርጅቶችን እና የዜና ወኪሎችን ይቀጥራሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት እንኳ አወንታዊ የሆነ በጎ ገጽታ ለማግኘት በማሰብ ከአሜሪካ ድምጽ የእንግሊዝኛው ፕሮግራም ጋር ታሪካቸውን ለመግለጽ ጥረት አድርገዋል፡፡ በኋይት ሀውስ የፕሬዚዳንቱ ልዩ እረዳት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑት በኢትዮጵያ ፌዴራል ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታይተዋል፡፡ ለብዙ ጊዜ በድህነት ውስጥ ተዘፍቃ የቆየችው ኢትዮጵያ አሁን የኢኮኖሚ መነቃቃት እያሳየች እንደሆነ በኒዮርክ ታይምስ ትረካ አድርገዋል፡፡ በዓባይ ግድብ ዙሪያ ከሱዳን እና ከግብጽ ጋር ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የውኃ ኃይል ማመንጫ ማማ ስለሚያደርገው ስለ5 ቢሊዮን ዶላሩ ፕሮጀክት ሲኤንኤ ትረካ እንዲያቀርብ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል፡፡
በሸፍጥ ላይ በተመሰረተ መልኩ የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ባለፉት አስርት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ በ10.7 በመቶ ዕድገት እያስመዘገበ እንደመጣ እና ይህም ዕድገት በአፍሪካ በዓመት 5.2 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ከሚያስመዘግቡት ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች በእጥፍ ደረጃ እንደሚበልጥ እያናፈሱት ያለው ተራ ቅጥፈት እና የዕውቀት ደረጃችንን ለመፈተን የሚያደርጉት ጥረት እርባና የለሽ እና በድሁር አስተሳሰብ የታጀበ አይንችሁን ጭፍኑ ላሞኛችሁ ከማለት የዘለለ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም፡፡ ከዚህም በላይ ድብቁ የዓለም ባንክ እነርሱን ወክሎ የምጣኔ ሀብቱ አድጎ ተመንድጓል በማለት ጥሩንባውን እንዲነፋላቸው ለማድረግ ጥረት አድርገዋል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በቅጥፈት በተፈበረኩ አሀዞች ላይ የተመሰረተ እና ምንም ነገር የሌለበት በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቁጥር መቀቀያ ማድቤት እየተፈበረከ የሚወጣ ነጭ ውሸት፣ የቀጥፈት ስብስብ ድሪቶ እና የጠራራ ጸሐይ ቅዠት መሆኑን በማያጠራጥር መንገድና ባማያከራክር ማስረጃ አሳይቻለሁ፡፡ የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Endowment Fund for the Rehabilitation for Tigray (EFFORT) እየተባለ በሚጠራ በአንድ ኮርፖሬሽን ስር በብቸኝነት ተጠቃሎ ተይዞ ባለበት ሁኔታ አንድ በቂ መረጃ ያለው ሰው እንዴት አድርጎ ሀገሪቱ በምጣኔ ሀብት ዕድገት እንደ ሮኬት ወደ ላይ ተመንጥቃለች እያሉ ተራ ቅጥፈትን ማሰራጨታቸው እና እንዴት አድርገው እራሳቸውን ለማሳመን መቻላቸውን ለመገንዘብ ያዳግታል ፡፡
እሺ መልካም ነው ፣ ይኸ ሁሉ ነገር የሚደረገው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እየደረሰበት ያለውን መበስበስ እና ውድቀት ለመደበቅ፣ ለመሰወር እና ለማጥፋት የታቀደ የፖለቲካ ቁማር ጨዋታ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እራሳቸውን እንደ ዱሮው ገራገር እና ቅን አሳቢ አስመስለው እንደ አዲስ ለማቅረብ እያደረጉት ያለው ጥረት ለምን እንደሆነ ለመገንዘብ እችላለሁ፡፡ ሆኖም ግን የተደበቀውን የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት እና ድፍጠጣ የሸፍጥ የህዝብ ግንኙነት ስራ እና ዕኩይ የቅጥፈት ዘመቻ በመስራት እራሳቸውን ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማንንም ለማሞኘት ይችላሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ የባልቲሞሩ ብልህ ሰው ሄንሪ ኤል. ሜንከን በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “እስከ አሁን ድረስ ማንም ቢሆን የአሜሪካንን ህዝብ ብልህነት እና ግንዛቤ የሉም ብሎ ተወራርዶ ያሸነፈ የለም፡፡“ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮችም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተመሳሳይ አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል።
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስሙን ለማደስ በርካታ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በመስራት ላይ ቢገኝም ጭፍራው የጠፋ ድርጅት ነው፡፡ ይህንን እውነታ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጃጁ አመራሮች የበለጠ የሚገነዘበው የለም፡፡ ከመለስ ህልፈት ጀምሮ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ በአደናጋሪ እና ግራ አጋቢ ንግግሩ የሚታወቅ አንድ የአካባቢ ንጽህና መሀንዲስ በአሻንጉሊት ጠቅላይ ሚኒስትርነት በማስቀመጥ የጋራ አመራር እንደሚሰጡ እና ውስጣዊ ጥንካሬን የተላበሱ ለማስመሰል ድርጅታቸው የህዝብ ግንኙነት ስራውን ለመስራት ሌት ከቀን ይታትራል፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ እንደ በረዶ ተራራ የተቆለለውን የሙስና ቆሻሻ ለማጽዳት ምንም ዓይነት ያደረገው ጥረት የለም፡፡ ቢሞክርም አቅሙምም ስብዕናውም አይፈቅድለትም፡፡ ምክንያቱም እውነተኛዋ ስልጣን ከእርሱ ወንበር ስር የለችምና፡፡ በእርግጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኃይለማርያምን በአሻንጉሊትነት በማስቀመጥ የእራሱን ቤት እስኪያጸዳ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ የሆነውን አዲሱን የእራሱን ሰው በወንበሩ ላይ እስከሚያስቀምጥ ድረስ ኃይለማርያምን የመሰለ ታማኝ ሎሌ አገልጋይ ለይስሙላ ማስቀመጥ የተሻለ ዘዴ መሆኑን አሳምሮ ያውቃል፡፡ የተፈለገው ለይስሙላም ቢሆን ከሌሎች ብሄረሰቦች ያውም ከአናሳ ብሄረሰብም እስከ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ድረስ ስልጣን እንዲጋራ የሚያደርግ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንዲባል ስለተፈለገ ነው፡፡ ወያኔን በእኩይ ምግባሩ እና በተካነው የሸፍጥ ስራው የማያውቀው ይኖራል ተብሎ ይታመናልን? ተረቱ ለማውቁሽ ታጠኝ ነው!
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የስልጣናቸውን የመጨረሻውን ጨዋታ እየተጫወቱ እንደሆነ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ አሁን እያደረጉት ያለው ጨዋታ በማንኛውም ጊዜ ሊቆም እንደሚችል ይገነዘባሉ፡፡ የመጨረሻው ጨዋታቸው በአንድ ህዝባዊ አመጽ ወይም ደግሞ በእራሳቸው ውስጥ ዘገመተኛ እና ቀሰስተኛ በሆነ ወስጣዊ አመጽ ይሁን አይሁን አጣርቶ ለማወቅ እንቅልፋቸውን በማጣት ሌት ቀን በመውተርተር ላይ ይገኛሉ፡፡
የፍጻሜው ጨዋታ የተነገሩለት ጉልህ የትረካ ማስረጃዎች በመታየት ላይ ናቸው፣
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፖለቲካ ጭቆናውን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ የመገናኛ ብዙሀንን ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ አድርጎ ዘግቷል፡፡ የነጻው ፕሬስ ጋዜጦች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል፣ እናም በርካታ ጋዜጠኞች ታስረዋል ወደ ግዞትም ተወስደዋል፣ የቀሩትም ሀገር ለቀው ተሰደዋል፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮች ማስፈራሪያ ይደረግባቸዋል፣ ይታሰራሉ፣ ስቃይ እና መከራም እንዲያዩ ይደረጋሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚገልጹ ሰላማዊ አመጸኞች እና ወጣት ጦማሪያን ወደ እስር ቤት ተወርውረው በማህበራዊ ድረ ገጾች ሀሳባቸውን በመግለጻቸው የሀገር ክህደት የሚል ክስ ተመስርቶባቸው በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ ህጋዊ ዕውቅና እና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እና ድጋፍ አለኝ የሚል አገዛዝ ተቃዋሚዎቹን እና በእርሱ ላይ ትችት በሚያቀርቡ ዜጎች ላይ ይህን የመሰለ እርምጃ መውሰድ በመንግስት ህጋዊነት ጥያቄው ላይ እምነት አለው ብሎ ለማመን ይቻላልን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የእነርሱ ግብረ አበሮች፣ ደንበኞች እና ደጋፊዎች የህዝብን ገንዘብ እየዘረፉ ከሀገር ውጭ በማውጣት በውጭ ባንኮች በከፈቷቸው የሂሳብ አካውንቶች በማጨቅ፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች ሀገሮችም የንግድ ድርጅቶችን እና ንብረቶችን በመግዛት ላይ ይገኛሉ፡፡ ጥቂቶች እንዲያውም ከዚህ አልፈው በእራሳቸው ላይ ሊመጣ ስለሚችለው የመጀመሪያው ችግር እንዴት ማምለጥ እንደሚችሉ እና እራሳቸውን ከችግር ማውጣት እንደሚችሉ ዕቅድ በማውጣት በግልጽ በመነጋገር ላይ ናቸው፡፡ ለእራሳቸው ለቀሪ ህይወታቸው፣ ለልጆቻቸው እና ለልጅ ልጆቻቸው ማቆያ የሚሆን በቂ ገንዘብ በውጭ ባንኮች በማጨቅ ላይ ናቸው፡፡ ይኸ ነገር እንዴት ሊሆን ቻለ? ዓለም አቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም/Global Financial Integrity እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ እየታጋጡ ነው፡፡ ከፍጹም ማጣት እና ከድህነት አራንቋ ውስጥ ለመውጣት የተፈለገውን ያህል ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም እንኳ በአሁኑ ጊዜ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ባህር ውስጥ በመግባት ወደ ላይ ወደ ምንጩ በመዋኘት ላይ ይገኛሉ፡፡“ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ እያራመደው ስላለው የወደፊቱ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ እምነት የለውም፡፡ አራት ነጥብ! በህጋዊነቱ ላይ እምነት እና በሰፊው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ ተቀባይነት እና አለኝ ከሚል አገዛዝ በብዙ ቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ከሀገር እየተዘረፈ እየወጣ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በቻይና መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ የእራሱን የግል ጥቀም ማሳደድ ይኖርበታልን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጣዊ አደረጃጀት ደካማ ከመሆኑም በላይ አመራሩ በፓርቲው ላይ ያለው ቁጥጥር፣ የወታደራዊ እና የደህንነት ተቋማት እጅግ በጣም ባልተረጋጋ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ቢሮክራሲያዊ ተቋም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት፣ ግብረ አበር ሎሌዎች እና ደጋፊዎች ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ቢሮክራሲያዊ ድርጅቶችን የሚያንቀሳቅሱ ታማኝ ሎሌዎችን ለማግኘት ያለ የሌለ ጥረታቸውን በማድረግ የሞት ሽረት ትግላቸውን ያካሂዳሉ፣ ሆኖም ግን ቢሮክራሲውን የሚያንቀሳቅሱት ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻችን ለእንጀራቸው ሲሉ ለመኖር የሚያደርጉት ጥረት እንጅ የወያኔ ሎሌ እና አሽከር ለመሆን አይደለም፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞች ቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በረብጣ እየታሰረ ከባንክ የሚወጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ በርካታ ገንዘብ በመያዝ የተሟላ የእስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ውድ ተሸከርካሪዎች/Sport Utility Vehicles (SUVs) እና በሌሎች ውድ ተሸከርካሪዎች በመጠቀም በአዲስ አበባ ከተማ ከቦታ ቦታ ሲንገዋለሉ የሚውሉ ቢሆንም ሀብቱን እና መብቱን የተነፈገው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥርሱን የነከሰ እና ጥፍሮቹን ያንጨበረረ ነብር ሆኖ በላያቸው ላይ እመር ብሎ ሊከመርባቸው እንደተዘጋጀ ሊያውቁት ይገባል፡፡
አዎ ሀመሮቻችሁን እና ሌሎችንም ውድ ተሸከርካሪዎች ንዱ! እኛ የአነዳዳችሁን ሁኔታ በአንክሮ እንመለከታለን፡፡ ትንሽ ህሊና እንኳ ቢኖራችሁ እስቲ ሌሎችን በረሀብ እና በችጋር የሚለበለቡትን የሀገሪቱ ባለቤት የሆኑትን ዜጎች ሆኖም ግን እንዲሆኑ የማይፈለጉትን ወገኖቻችንን ህይወት ለጥቂት ደቂቃዎች ዘወር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ ቁንጮው እና መካከለኛው የወታደር አመራር የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባሎች ወይም ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ባለዝቅተኛ እና ባለሌላ ማዕረግ የሆኑ ወታደሮች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባል ሳይሆኑ ህይወታቸውን ለመምራት ሲሉ በውትድርናው ዓለም ተቀጥረው በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ እውነታው ተገልጦ ሲታይ ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በብዙሀኑ ህዝብ ዘንድ ድጋፍ እንዳለው አድርጎ በብቸኝነት በተቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሀን ሌት ከቀን ፕሮፓጋንዳውን በመንዛት እራሱን ለማሳመን ቢሞክርም ይኸ እየተባለ ያለው ድጋፍ ከልብ የጠለቀ ሳይሆን ብን ብሎ የሚጠፋ ግልብ ነው፡፡ በህጋዊነቱ ላይ እምነት እና በሰፊው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት እና ድጋፍ አለኝ የሚል አገዛዝ መንግስታዊውን ቢሮክራሲ፣ የወታደራዊ እና የደህንነት ኃይሉን እንዲሁም የምጣኔ ሀብቱን ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት መቆጣጠር ሊኖርበት ይችላልን?
በአንድ ወቅት በአብዛኛው በሚባል መልኩ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ተወስኖ የነበረው ሙስና እና ዘረፋ በአሁኑ ወቅት ቅርጹን እና ይዘቱን ከፍ ወዳለ እና መጠነ ሰፊ ወደሆነ ደረጃ ቀይሮ ወያኔ በመሰረተው የሙስና ተቋም ላይ መሰረቱን ተክሎ በአሁኑ ጊዜ በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ አካባቢ እና ተቋም (የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብለው ይሻላል) ውስጥ እንደ አደገኛው ተስፋፊ ካንሰር በሀገሪቱ የሰራ አካላት ላይ ተሰራጭቶ በማህበረሰቡ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካው፣ በኃይማኖት፣ በቢሮክራሲው እና በወታደራዊ ተቋማት ሁሉ ተዛምቶ ሀገሪቱን እግር ከወርች ጠፍሮ ይዞ ይገኛል፡፡ ለህዝብ ምንም ዓይነት ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሌለበት እና የህግ የበላይነትን ከቁብ የማይቆጥር በቤተሰባዊነት እና በዘመድ አዝማድ ትስስር የሰፈነበት መጠነ ሰፊ የሆነ የሙስና ግዛት ለመመስረት እንዲቻል በሚል ዕኩይ ስሌት የአንድ ፓርቲ የአገዛዝ ስርዓትን መስርተው ሀገሪትን በማተራመስ ላይ ይገኛሉ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሙስና የበከተውን ግዛቱን ለብዙ ጊዜ ይዞ ማቆየት እንደማይችል ያውቃል፡፡ የቅርብ ታሪክ እንደሚያሳየው የማህበራዊ ቀውስ እና ፖለቲካዊ አመጾች የሚቀሰቀሱት አስደንጋጭ በሆነ ሙስናና ዘረፋ እንዲሆም ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ ከመቀም የሚመነጩ ናቸው፡፡ በዘመናዊቷ አፍሪካ ጥቂት አገዛዞች ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በላይ የስልጣን ሙስናን ያካሂዳሉ፡፡ ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል በሚባል መልኩ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፍጹም የሆነ የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣንን ይዞ በስልጣኑ ከህግ አግባብ ውጭ ፍጹም የሆነ ሙስና ሲተገብር ቆይቷል፡፡ በህጋዊነቱ ላይ እምነት እና በሰፊው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት እና ድጋፍ አለኝ የሚል አገዛዝ እንደዚህ ባለ እርቃንን በሚያስቀር አሳፋሪ ሙስና ተዘፍቆ መገኘት ይኖርበታልን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015ን የምርጫ ዕለት አድርጎ ሰይሟታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 መለስ የ99.6 በመቶ የዘረፋ ምርጫ የአሸናፊነት ድል እድራጊነትን የዕቅድ ስሌት ለማሳካት ሲል በግድ ህዝብ ያላመነበትን እንዲመርጥ አስገድዷል፣ ለሸፍጥ ምርጫው ሲል ጉቦ ሰጥቷል፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ሁከት እንደፈጠር አድርጓል፣ አስፈራርቷል፡፡ ለሰብአዊ መብት ድጋፍ በሚል ከውጭ አበዳሪ እና እርዳታ ሰጥ ድርጅቶች የተገኘውን እርዳታ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በማጭበርበር ድምጽ ለማግኘት በሚል እኩይ ምግባር ገንዘቡን ከተመደበለት ዓላማ ውጭ አውሏል፡፡ የወጣቱን የምርጫ ታማኝነት ለማግኘት በማሰብ ለጊዜው ስራ ፈትነትን ብቻ ለማስታገስ የሚያስችሉ እንደ የድንጋይ ጠረባ እና ድርደራ/ኮብል ስቶን ስራዎችን ሰጥቷል፡፡ ለእራሱ ገዥ ፓርቲ ድጋፍ ለማሰባሰብ በማሰብ የመንግስትን ሀብት ከህግ አግባብ ውጭ ለምርጫ እንቅስቃሴ እንዲውል አድርጓል፡፡ የተቃዋሚ ኃይሎችን ለመሰለል እና መረጃዎችን በማግኘት እንቅስቃሲያቸውን ሁሉ ለማምከን በማሰብ የምርመራ ፕሮግራሞችን እና የስለላ መረቦችን አደራጅቶ በስራ ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡
መለስ እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫውን ስርዓት ባለው መልክ በህዝብ ድምጽ በሚገኝ ምርጫ ሳይሆን በኃይል፣ በዘረፋ እና በማጭበርበር አሸነፍን በማለት በቆዩበት የስልጣን ወንበር ላይ እንደገና ደግመው ደጋግመው ፊጥ አሉ፡፡ እ.አ.ኤ አሁን በዚህ ዓመት የፊታችን ግንቦት 24/2015 ይደረጋል ተብሎ ለተያዘው የወያኔ የይስሙላ ምርጫ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምንም ይሁን ምን በ99.6 በመቶ ያሸንፋል በሚለው ሀሳብ ላይ ጥያቄ የሚያቀርብ ይኖራልን? እንግዲህ ቢያንስ 99.6 በመቶ የድምጽ ውጤት በማምጣት አሸንፋለሁ የሚል አገዛዝ ከእራሱ ላይ መተማመንን አሽቀንጥሮ በመጣል ሰላማዊ ዜጎችን ማስፈራራት እና ተቃዋሚዎቸ ናቸው የሚላቸውን ሰላማዊ ዜጎች ማሰር፣ ነጻውን ፕሬስ መምታት እና መዝጋት፣ እንዲሁም ህጻናትን እና በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል አካባቢ የሚገኙትን ወጣት ጦማሪያን ሀሳባቸውን በነጻነት በማህበራዊ ድረ ገጾች በመግለጻቸው ብቻ ወንጀል ተደርጎ አሸባሪ የሚል የክስ ታፔላ በመለጠፍ አሳር ፍዳቸውን ማሳማየት ይኖርበታልን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሰዓት በተሞላ ቦምብ ላይ ተቀምጦ የቁማር ጨዋታ በመጫወት ላይ እንዳለ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡ በትዕቢት በመወጥር እና በትምክህት የሰከሩት የወያኔ አመራሮች ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት የለኮሱት የጥላቻ እሳት ነበልባል አንድ ቀን አቅጣጫውን ወደ እንርሱ አዙሮ ሊለበልባቸው እና ሊያጋያቸው እንደሚችል ሊያሳየአቸው የሚችሉት ሂሊናቸው እና ዓይኖቻቸው ታውረዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት የተጠራቀመው፣ ጥላቻ፣ ፍርሀት እና ጥልቅ የበቀል ጥላቻ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ እነርሱ ሊዞር ይችላል፡፡ ወያኔዎች አንዱን ጎሳ በሌላኛው ጎሳ ላይ በጥላቻ በማነሳሳት፣ አንዱን ኃይማኖት በሌላው ላይ በማነሳሳት ለዘላለም በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀን እንኖራለን የሚል የበከተ ሀሳብ ይዘው ከሆነ እጅግ በጣም ታላቅ የሆነውን ስህተት ሰርተዋል፡፡ ሁሉንም የጎሳ ቡድኖች ለጥቂት ጊዚያት ሊያሞኟቸው ይችላሉ፣ ጥቂት የጎሳ ቡድኖችን ደግሞ ለሁልጊዜ ሊያሞኟቸው ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም የጎሳ ቡድኖች በፍጹም ሁልጊዜ ሲያታልሏቸው ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ሁሉንም ክርስቲያኖች… ሙስሊሞች ለጥቂት ጊዚያት ሊያታልሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን በፍጹም ሁሉንም ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ሁልጊዜ ሲያታልሉ ሊኖሩ አይችሉም፡፡
ሴልማ፣ አላባማ እና ኢትዮጵያ፣
እ.ኤ.አ መጋቢት 7/2015 ፕሬዚዳንት ኦባማ በሰልማ፣ አላባማ በዕለተ ቅዳሜ በርካታ ዜጎች ባለቁበት 50ኛ ዓመታ መታሰቢያ በዓል ላይ በመገኘት ወደ 100 ገደማ ከሚሆኑት የሰልማ፣ አላባማ የምክር ቤት/ኮንግረስ አባላት ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡ ከ50 ዓመታት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ በምርጫ ለመሳተፍ ፍጎት የነበራቸው አፍሪካ-አሜሪካውያን/ት በመንግስት ፖሊስ እና በእጀ በተመረጡ ህገወጥ ህግ አስከባሪዎች በዱላ ተደበደቡ፣ በእርግጫ ተመቱ፣ የእንባ አስለቃሽ ጋስ ተረጨባቸው፣ እንደዚሁም በእጅ እየተገፈተሩ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በድልድዩ ላይ ቆመው ለህዝቦቹ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣ “ያንን የፖሊስ የኃይል እርምጃ የተቀላቀለበትን ክስተት በኢድሞንድ ፔተስ ድልድይ በጽናት ቆመው ፊት ለፊት ለተጋፈጡት ወንዶች እና ሴቶች ጀግኖች ለዘመናት እንደ ገደል ማሚቶ ሲጮህላቸው እና ሲወደሱ ይኖራሉ፡፡ ይህም የሚሆነው በአሸናፊነት ያመጡት ለውጥ አስቀድሞ የተተነበየ እና የተወሰነ በመሆኑ ምክንያት አልነበረም፣ ወይም ደግሞ ሁሉንም ነገር በአሸናፊነት የደመደሙት በመሆናቸው ምክንያት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ኃይል ባልተቀላቀለበት በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በማረጋገጣቸው እና ፍቅር እና ተስፋ ምንጊዜም ቢሆን ጥላቻን እንደሚያሸንፉ በማሳየታቸው ነው፡፡“
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ በመጨረሻው የቁማር ጨዋታው ላይ ስለመሆን ጥያቄ የሚያቀርቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት የመጨረሻው የጨዋታ ፍጻሜ ለመጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ይቀረዋል በማለት ይጠይቃሉ፡፡
ከ50 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ መጋቢት 7/2015 ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ተመሳሳይ የሆኑ ጥያቄዎችን በማንሳት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ የሚል ተገቢ ምላሽ ሰጥተው ነበር፡
በዛሬው ዕለት “ምን ይህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል?” ብላችሁ እንደምትጠይቁ አውቃለሁ፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ እንዲህ የሚል ጥያቄ ያቀርባል፣ “ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የሰዎችን ዓይን በማወር እንዳያዩ የሚያደርገው፣ ገንዛቤ እንዳይኖራቸው አጨልሞ እንዲያዙ የሚያደርጋቸውን እኩይ ሀሳብ በማስወገድ ብሩህ ዓይን እና ጥበብን የተላበሰችው ፍትህ ወደ ቅዱስ ዙፋኗ የምትመጣው መቸ ነው?“ ሌላው ሰው ደግሞ እንደዚሁ እንዲህ የሚል ጥያቄ ያቀርባል፣ “የቆሰለችዋ ፍትህ ከሰልማ እና ከበርሚንግሀም መንገዶች ላይ እንዲሁም በጠቅላላው ከደቡብ ማህበረሰብ ዘንድ ወድቃ የምትገኘው ፍትህ ከዚህ የውርደት ቦታ ላይ ተነስታ በሁለም ህዝቦች ዘንድ ዋና ተፈላጊ ሆና የምትቀርበው መቼ ነው?“ እንደዚሁም ሌላው እንዲህ የሚል ጥያቄ ያቀርባል፣ “አንጸባራቂ የሆነው ተስፋችን በዚህ በጨለማ እና ብቸኛ በሆነው ምሽት ተተብትቦ ተይዞ ከአሰልች የፍርሀት ህይወት እና ከሞት ሰንሰለት ነጻ የምንሆነው መቸ ነው?“ መቸ ነው ፍትህ ነጻ ወጥታ እውነትን ተላብሳ ወደ እውነተኛ መንበሯ ላይ መሰየም የምትችለው?
እኔም ዛሬውኑ ከሰዓት በኋላ እላችኋለሁ፣ ሆኖም ግን ክስተቱ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሰዓቱም የቱንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ሩቅ አይሆንም ምክንያቱም እውነት በመሬት ውስጥ ተቀብራ አትቀርም፣ እናም በአንድ ወቀት በደማቅ እና ጸዳልን በተላበሰ ሁኔታ ብርሀኗን ከጫፍ እስከ ጫፍ ፈንጥቃ ብቅ ማለቷ አይቀርም፡፡ እኮ እስከ መቸ? ሩቅ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ምንም ዓይነት ቅጥፈት ለዘላለም መኖር አይችልም፡፡ ምን ዓይነት ተስፋ አስቆራጭ ነገር ነው የሚናገሩት! እኮ እስከ መች ነው እኮ የምለው? ብዙም ሩቅ አይሆንም ምክንያቱም ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና፡፡
እርግጠኛ ነኝ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከሰልማ ልምድ ትምህርትን ይቀስማል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኃይል ባልተቀላቀለበት ሰላማዊ ትግል ለውጥን ማምጣት ይቻላል፡፡ ፍቅር እና ተስፋ ጥላቻን ድል ያደርጋሉ፡፡ በሌላ አባባልም በጣም ማስፈራራት፣ በጣም ተስፋየለሽ አድርጎ ጨለምተኛ ማድረግ፣ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንዲወሸቁ አድርጎ በድን ማድረግ ለመጨረሻው ውድቀት ምልክት ካልሆነ በስተቀር ሌላ የሚያተርፈው ነገር እና የሚፈይደው ጉዳይ ስለሌለ እኔ ይኸ ጉዳይ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው እላለሁ፡፡
የሰላም ለውጥ ከሌለ ያለው ምርጫ ያለምንም ጥርጥር “እያንዳንዳችሁ የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ!“ ነው።
ይቀጥላል…
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment