Friday, March 20, 2015

በአውሮፓ ስዊዘርላድ ጄኔቭ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Geneva‬ ‪#‎Switzerland‬ ‪#‎HumanRights‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EU‬ Minilik Salsawi - የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እስር ግድያ እና ዘረፋ በመቃወም ለአለም አቀፉ ሕብረተሰብ እና መንግስታት ለማሰማት በዛረው እለት በአውሮፓ ስዊዝ መዲና ጄኔቭ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል:: በሕወሃት ኢሕአዴግ ዘረኛ አገዛዝ በግፍ ወሕኒ ለተወረወሩ ወገኖቻችን በስዊዝ የመንግስታቱ ጽ/ቤት ደጃፍ ድምጻቸውን ለማሰማት የወጡ ኢትዮጵያውያን በርካታ ሲሆኑ በኢትዮጵያ ባንድራ ታጅበው የተለያዩ መፈክሮችን እና የታሳሪ እና ተጎጂ ወገኖቻችንን ምስል በመያዝ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው::


No comments:

Post a Comment