የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች መካከል መነሻውን ጥቅም ያደረገ ልዩነትና አለመግባባት መፈጠሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣በመረጃው መሰረት ቀደም ሲል በርከት ያሉ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሰራዊት አዛዦች ለምን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ደግሞ ታዛቢ እንሆናለን የሚሉ ቅሬታዎች የነበሩ ሲሆን ይህንን ያረጋጋል ተብሎ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከሻለቃ በላይ ሃላፊነት ያላቸው የመከላከያ ስታፍ አባላት በሜጀር ጀኔራል መሃሪ ዘውደ የተመራ ስብሰባ እንዳካሄዱ ታውቋል፣
መረጃው ጨምሮም በመከላከያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለው አድሎና ሙስና እንዲቆም ሰራዊቱ ተቃውሞ እያካሄደ የቆየ ቢሆንም የመጣ ለውጥ የለም ሲሉ የገለፁት ተሰብሳቢዎች በሁኔታው የሰጋው ሜጀር ጀኔራል መሃሪ ዘውደም የአዛዦችን ስሜት ለማረጋጋት ሲል “የኑሮ ችግር ያለባችሁ ማመልከቻ አስገቡና ይፈታላችኋል” በማለት የማይፈፀም ቃል የገባ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
በዚህ ከፋፋይና የማይፈፀም የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቃል ያልተስማሙት ከፍተኛ መኮነኖች በበኩላቸው ከሻምበል በታች ያሉት የሰራዊት አባላት ምን የተፈታላቸው አለ የሚል ሃሳብ በማቅረባቸው በሜጀር ጀኔራል መሃሪ የተሰጣቸው መልስም። ችግር አለብን እያላችሁ ሰራዊት ስታነሳሱ ቆይታችኋል አሁንም ችግራችሁን እንፈታላችኋለን ካልናችሁ ከዚህ በላይ ምን ፈልጋችሁ ነው ማንን ለማነሳሳት ነው እንደዚህ ዓይነት ሃሳብ የምታቀርቡት በማለት ያለስምምነት እንደተበተነ ለማወቅ ተችሏል፣፣
No comments:
Post a Comment