«አክራሪ እስልምና የኢትዮጵያ ክርስትና አስቸጋሪው ፈተና» ብለህ ያዘጋጀኸውን ጥናታዊ ጽሁፍ አዳመጥኩት። አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የሰጠህን ምላሽም እንዲሁ አነበብኩት። አንተም «ኤርሚያስ ሆይ!» ብለህ የጻፍከውን ምላሽ አንብቤ እንደጨረስኩ «ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመጨረሻ አስተያየት» የሚለውን የኤርሚያስን ጽሁፍም አነበብኩት። ሁሉንም ካነበብኩ በሗላ ግን ባንተ ብቻ ሳይሆን ባገሬ መንግስትም በጣም አዘንኩኝ።
በርግጥ ኤርሚያስ ለገሰ በሰጠህ መልሶች ብዙዎችን የማውቃቸውን እውነታዎች ባገኛቸውም ካንተን ጥናታዊ ፅሁፍና የመልስ ፅሁፎች ግን አንተና የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ ሙስሊም ያላችሁን ትልቅ ጥላቻ ለመገንዘብ ችያለሁ። ያነሳሃቸውን ነጥቦች ስመለከት ከመጀመሪያው ጀምሮ ያቀረብከው ታሪክ ስለቁራአን ፤ስለነጃሽ ፤ስለኢትዮጵያውስጥ እስልምና
፤ለአጼ ሃንስ እለፈት ምክኒያት ሆኑ፤ሞሶሎኒ እንዃን ሳይቀር ለሙስሊም ያደላ ዕንደነበር፤የክርስቲያን ሴቶች ራሱ በሙስሊሞች እንደሚደፈሩ፤የቤተክርስተያን ቅርሶች በሙስሊሞች እንደሚዘረፉ፤ ባጠቃላይ ከድሮ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ፈተና እንደነበሩ፤ወደፊትም ትልቅ ጠላት መሆናቸውን፤በአገሪቱ የሂጃብ መስፋፋት፤ የመስጊዶች ፤የቁርአን ትምህርት ቤቶች ፤ የኢስላማዊ ድርጅቶች ፤የሃጅ እና ዑምራ ተጓዦች፤ኢስላማዊ መፅሃፍትና ሌሎችም የሙስሊሙ እንቅስቃሴ አንተ ከምተፈልገው ቁጥር በላይ መብዛቱ እንዳሳሰበህ ከመግለፅና በሙስሊሙናክርስተያኑ መሃከል ጥላቻን ከመዝራት ባሻገር የገለፅካቸው ሁሉ ነገሮች ከጥናታዊ ፅሁፍነት ወደ ተራ የቡና ወሬነት ያደላሉ።
ጥናታዊ ፅሁፍህ ላይ ያቀረብካቸውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም? ብሎ ኤርሚያስ ለጠየቀህ ጥያቄም መልሱን «ኤርሚያስ ሆይ!» ብለህ በጀመርከው የመልስ ፅሁፍም ፕሮጀክተር ላይ ለሰወች እንዳሳየሃቸው ነገርከን እንጅ ለኛ ልታሳየን ስላልቻለክ ዳታወ ቪዲዮ ወይም አኒሜሽን ሊሆን ይችላል ብየ አልፍሃለሁ፡፡
ጥናታዊ ፅሁፍህን አስመልክቶ ኤርሚያስ ለገሰ ለጠየቀህያቀረብከውን መረጃዎችህን እንዴት እንዳሰባሰብካቸው፤ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ” ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ” ማንሳት እነዳልፈለክ፤ ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው ይሄን ጥያቄ ይዘህ ብቅ እንዳለክ የጠየቀህ ቢሆንም ጽሑፉ ነሐሴ 25 ቀን 1999 ዓም አሜሪካ እንደቀረበ የሚገልፅ ነበር ዳሩ ግን «አክራሪ እስልምና የኢትዮጵያ ክርስትና አስቸጋሪው ፈተና Published on Feb 20, 2015 Deacon Daniel Kibret https://www.youtube.com/watch?v=4u6ItFJeG4A »
50ኛው ደቂቃ 39ኛ ሰከንድ ላይ በ1987 ዓም ከተደረገው ሀገርአቀፍ ቆጠራ በሗላ የአምና በ2006ጥናትህን የኢቶጵያን ህዝብ በክልሎች ከፍለህ ስታበራራ ነበር፡፡ጥናቱ የቀረበው በ1999 ዓም፣ አንተ ጥያቄውን ያነሣኸው ደግሞ በ2007 ነው ብለህ ኤርማስን መቸ እነደቀረበ ሳያጣራ ብለህ ከመወንጀልህ በፊት ከላይ በተጠቀሰው ደቂቃና ሰከንድ እንደገለፅከው 2006ን አምና እያለክ ኤየገለፅክ «ስሜ ነው እንጂ እኔኮ ነቢይ አይደለሁም» እያለክ በማፌዝ ኤርሚያስን ለመዝለፍና ለመወንጀል ሞከረሃል ለመሆኑ የትኛውን 2006 ይሆን ፅሁፍህ ላይ «አምና2006» ብለህ የምትጠራው የፈረንጆችን እንዳልል «በ1987 ዓም ከተደረገው ሀገርአቀፍ ቆጠራ » ብለህ ከጠራህ በኋላ ስለሆነ 2006 ዓ.ምን ያበራራሀው ይሄንንም እዛው ፐሮጀክተሩ ላይ ይሆን ምናገኘው እንደዛ ከሆነ የፕሮጀክተሩ ማሳያ ብትር በተረ-ሙሴ መሆነ አለበት።
አንተና የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ ሙስሊም ያላችሁን ትልቅ ጥላቻ በድጋሚ ለመገንዘብ ችያለሁ አንተ (በ2000 ዓም ጥናቱን ካቀረብኩት በኋላ ነው ‹ሽመልስ ከማል ሠራው› ያልከው ጥናት ለመንግሥት የቀረበው፡፡ ያ ጥናት ለመንግሥት አካላት ሳይለዋወጥ መቅረቡን በወፍ በረር እናውቅ ነበር፡፡ ስለዚህም የተከተለ ከቀደመ ይወስዳል እንጂ የቀደመ ከተከተለ አይወስድምና ‹ቃላት ሳይቀየሩ የቀረበው› እኔ ያቀረብኩት ጽሑፍ እንጂ በእናንተ ስብሰባ ላይ የቀረበው ጽሑፍ ወደ እኔ መጥቶ ሊሆን አይችልም ) ስትለን
ኤርሚያስ ደሞ በጥናቱ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች እንደወረደ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማው በ2001 አም ከሽመልስ ከማል ነበር ፤ከግማሽ በላይ የአንተ ዶክመንት አባሪ እነደረገበት፤ ከአራት ሚሊዬን በላይ በሆኑ የኢህአዴግ አባላት ውይይት እንደረገበት እነደተቃወሙት ይገልፅልናል።
ኤርሚያስ ደሞ በጥናቱ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች እንደወረደ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማው በ2001 አም ከሽመልስ ከማል ነበር ፤ከግማሽ በላይ የአንተ ዶክመንት አባሪ እነደረገበት፤ ከአራት ሚሊዬን በላይ በሆኑ የኢህአዴግ አባላት ውይይት እንደረገበት እነደተቃወሙት ይገልፅልናል።
በስተመጨረሻ ወደ ዋናው ቁም ነገር ስመጣ ግን አነተም ቀደምክ ኢህአዴግ የሁለታችሁም ጥናታዊ ፅሁፍ ተብሎ የቀረበው ከጭፍን የሙስሊም ጥላቻ የመነጨና ኢስላምን የማጥፋት ድብቅ አጀንዳውን ከነማን ጋር አሲሮ የተነሳ ፤በአክራሪነት ስም ሆን ተብሎ ክርስቲያንና ሙስሊሙን ለማጋጨት የታቀደ መሆኑና የሙስሊሙና እርስቲያኑ አንድ መሆን እነደእግር እሳት የሚያቃጥላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች እነዳሉ ለማንም የተደበቀ አደለም ሆኖም እነዚህ ራሳቸውን እነደ ፀረ-አሸባሪ የሚያዩ አክራሪ ፀረ-ሰላሞች ሰላማዊ ዜጋን በማን አለብንነት የአሸባሪ ስም በመለጠፍ በየወህኒ ቤቱ በማጎርና በማሰቃየት ለታሪክ አስነዋሪ ለነገዋ ኢትዮጵያም የሚያሳፍረና የሚያወቃቅስ እየሰራችሁ የነፃነትን ትረጉም ሳታውቁ ራስን የነፃነት አረጎ ልደቴን አክብሩልኝ እያሉ መቀባጠር የረከሰ ፖለቲካ ነው።
የጥናት አቅራቢዎችም የጥላቻና እነቶፈንቶ ወሬ በመያዝ ከፀረ-ኢስላም የመንግስት ባለስልታናት ጋር ወግኖ የህዝበ ሙስሊሙን ደም መፍሰስ፣መሰቃየትና በእስር መማቀቅ ከማሴር ይልቅ ሃይማኖት በሚያዘው መልኩ በፍቅር፣በሰላም፣በመተዛዘን፣በመከባበር፣በመቻቻል ብትሰበኩ በፈጣሪ ዘንድ የተወደደና የተቀደሰ ደግ ሃሳብ ነው። ለሰው ደግ ሆናችሁ ስለደግነት ብታወሩና ብተሸልሙ ኢትዮጳ ውስጥ የምታዘጋጁት«የአመቱ ደግ ሰው» የተሰኘው አመታዊ ሽልማት በአለምአቀፍ ደረጃ አሳድጎ ሽልማቱ ቅድሚያ ለናነት በተገባችሁ ነበር።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39624#sthash.HkBjcqOh.dpuf
No comments:
Post a Comment