ህዝብ ገዢውን የኢህአደግ ጉጅሌ እንዲመርጥ የስርአቱ ታማኝ ካድሬዎች ሊያስገድዱ እንደሚገባቸው በዝግ ስብሰባ ላይ ጥብቅ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ከስብሰባው ተሳታፊዎች የደረሰን መረጃው አመለከተ፣
በአዲስ አበባ የስርአቱ ታማኝ ካድሬዎች የተባሉ የካቲት 21 2007 ዓ/ም ስብሰባው በስብሓት ነጋ እንደተካሄደ የገለፀው መረጃው የስብሰባው አጀንዳም መጪው ግንበት ላይ የሚካሄደው ምርጫ በተመለከተ ሲሆን የምርጫ ካርድ እንዲወስድ የታሰበው የህዝብ ቁጥር እንደተፈለገው አይደለም፤ ወስደዋል የሚባሉትም በስርአቱ ላይ እምነት ያላቸው ቁጥራቸው ያነሱ ናቸው የሚል ሃሳብ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው በማከል በህዝቡ እምቢተኝነት የሰጉ የህወሓት-ኢህአደግ ባለስልጣናት “ ከተቃዋሚዎች የወገነውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በሃይል እያስፈራራችሁ ኢህአደግን እንዲመርጥ ማስገደድ አለባችሁ” የሚል በስብሓት ነጋ የስርአቱ ታማኝ ካድሬዎች የአስገዳጅ ስራቸውን እንዲሰሩ መመሪያ እንዳወረደላቸው ምንጮቻችን ከከተማዋ የላኩልን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣
No comments:
Post a Comment