Tuesday, March 17, 2015

አገር ወዳዱና አጥባቂ ኦርቶክሳዊ የነበረው አበበ ቢቂላ አስገራሚ የታሪክ ማስታወሻ ቪድዮ

አገር ወዳዱና አጥባቂ ኦርቶክሳዊ የነበረው አበበ ቢቂላ አስገራሚ የታሪክ ማስታወሻ ቪድዮ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የኃይሌ ገብረሥላሴና የአበበ ቢቂላ የደምጽ መመሳሰል በጣም ይገርማል:: አዳምጠው ይፍረዱ! 
. ኢትዮጵያ ውስጥ ሩጫና ኦሎምፒክ እንዲስፋፋ ንጉሰነገስት ኃይለሥላሴ ከባድ ማበረታቻ ያደርጉ ነበር:: በዘመናቸው ትልቅ ሽልማት ያገኙት አትሌቶች ነበሩ:: 
. ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሻምበል አበበ ቢቂላ ሲያርፍ ሀገር አቀፍ የሀዘን አዋጅ አውጀው ነበር::ንጉሱ ጥብቅ ትዛዝ በማስተላለፋቸው የሻምበል አበበ ቢቂላን ቀብር ላይ 75,000 ሰው ተገኝቷል::
."አትሌት መሆን በቁምም ይሄን ያህል ካስሸለመ : በህልፈትም ይሄን ያህል ካስከበረ" በማለት በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቲክስን እንዲቀላቀሉ ሆነ::

. ሻምበል አበበ ቢቂላ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ በማግኘት የመጀመርያው ጥቁር አፍሪካዊ ነው::
. አበበ ቢቂላ ሮም ላይ ሲሮጥ እጅጉን ደሙን ያፈላው የአክሱምን ሃውልት ሮም ላይ ተተክሎ ማየቱ እንደነበር ተናግሯል:: ለጋዜጠኞችም የሰጠው መግለጫ እንዲህ ይላል
"I wanted the world to know that my country, Ethiopia, has always won with determination and heroism" ኣበበ ቢቂላ
በእንተ አበበ ቢቂላ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
"ያ ትውልድ" እየተባለ ስሙ የሚነሳው ግፈኛ ትውልድ: የታላቁን መሪ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ታሪክ ጥላሼት ለመቀባት ቢሞክርም : የንጉሱ ታሪክ ሲመረመር ለብዙ በጎ ነገሮች መሰረት የነበሩት አጼ ኃይለሥላሴ ነበሩ::
ሩጫ በሀገራችን እሺህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ መሰረት የጣሉትም እሳቸው ነበሩ:: ለመጀመርያ ግዜ የኦሎምፒክ ስፖርት ትልቅ በጀት እንዲመደብለትና አሰልጣኝ ተፈልጎ ጸኑ ስልጠና እንዲሰጥ አዘዙ:: የክቡር ዘበኛ አባል የነበረው አበበ ቢቂላም ልቡ ወደ ኦሎምፒክ በማድላቱ በስዊድናዊው አሰልጣኛ ለሩጫ ስፖርት ተመለመለ::
አበበ አሸንፎ ሲመጣም ንጉሱ ራሳቸው በክብር ይቀበሉት ነበር:: እጅግ ከበዛው የገንዘብ ሽልማት ባሻገር የማዕረግ እድገትም ተሸልሟል:: በመጀመርያው ድሉ የሃምሳ አለቃነት ማዕረግ ሲያገኝ በቀጣይ ድሎቹ ደግሞ የሻምበልነት ማዕረግ ተሸለመ::በግዜዋም እጅግ ዘመናዊ የተባለችን ቮልክስዋገን መኪና ከተበረከተለት ስጦታ አንዱ ነበር:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ይሄንኑ የተሸለመውን መኪና ሲነዳ አደጋ ገጥሞት አካለ ስንኩል ሆነ:: በመጨረሻም በ41 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::
"Men of success meet with tragedy. It was the will of God that I won the Olympics, and it was the will of God that I met with my accident. I accepted those victories as I accept this tragedy. I have to accept both circumstances as facts of life and live happily." ኣበበ ቢቂላ
ሻምበል አበበ ቢቂላ ሲያርፍ ንጉሱ በብሔራዊ ደረጃ ሀዘን አወጁ:: የኢዮጵያ ባንዲራም ዝቅ ብሎ ለሳምንት ተውለበለበ::ንጉስም ቀጭን ትዛዝ በማስተላለፋቸው በቀብሩ ላይ ሙሉ ንጉሳውያን ቤተሰቦችና 75,000 ( ሰባ አምስት ሺህ ሰው ) ተገኝቶ ነበር:: "ሩጫ ይሄን ያህል ያስከብራል እንዴ" በሚል ስሜት ሩጫ ባህል ሆነ::
ዋቤ
http://www.tributes.com/obituary/read/Abebe-Bikila-83920581
http://www.sports-reference.com/…/at…/bi/abebe-bikila-1.html
http://www.ethiomedia.com/all/6252.html
http://www.sports-reference.com/…/19…/ATH/mens-marathon.html

No comments:

Post a Comment