Sunday, March 1, 2015

የወያኔዋ ኢትዮጵያ ለአማራ ብሔር እና ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሌላኛዋ ኢራቅ ሶርያ … !!!

የወያኔዋ ኢትዮጵያ ለአማራ ብሔር እና ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሌላኛዋ ኢራቅ ሶርያ … !!!
የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም በአሳዛኝ ሁኔታ በሆሳህና ከተማ የምትገኘው የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአሳዛኝ ሁኔታ በእሳት ወድማለች ። በአሁኑ ሰዓት ያለችው የወያኔዋ ኢትዮጵያ ለአማራ ብሔር እና ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ፍፅማ የማትሆን ሁናለች ። ጥንታዊ ገዳማት እየፈረሱ ነው አብያተ ክርስቲያን በተደራጀ በታቀደ ሁኔታ ይቃጠላሉ ለምን ሲባል አክራሪዎች አሸባሪዎች እንባላለን መነኮሳት ይታሰራሉ ለምን ስንል እናንተ አማራዎች ናችሁ አይመለከታችሁም እንባላለን ሆን ተብሎ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች ይፈናቀላሉ ይህንን የሚያደርጉ ለፍርድ አይቀርቡም የዛሬ አመት ከአስር በላይ አብያተ ክርስቲያናት በደቡብ ክልል ተቃጥለዋል በዚች ሃገር ሕግ የለም ፍትሕ የለም ምን ማድረግ ይቻላል ? በቃ ይች ሃገር እንዲህ ሁናለች በየቀኑ የአብያተ ክርስቲያን ቃጠሎ መስማት ለእኛ እንደ ግራኝ መሐመድ እና እንደ ዮዲት ጉዲት አመን የተለመደ ሁኗል ። ጉዳዩ ቀጥታ የሚቀነባበረው በወያኔ መስርይ ፀረ ኦርቶዶክስ እና ፀረ አማራ ቅጥረኞች ነው በዚች ሃገር በርካታ የእስልምና የካቶሊክ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች አሉ ግን አንድም ቀን ጥቃት ደርሶባቸው መስጊዳቸው ተቃጥሎ አያውቅም ለምን መልሱ ግልፅ ነው በወያኔ አቋም መፍረስ መቃጠል ያለባት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና የአማራ ብሔር ነው ። ፖሊስ የመለዮ ልብስ ለብሶ ቤተ ክርስቲያንን ሲያቃጥል ያየንበት ዘመን ይህ የወያኔ የጥፋት ዘመን ብቻ ነው ። የዛሬ አመት በሚያሳዝን ሁኔታ የቡሻና በአታ ቅድስት ለማርያም ገዳም በጠራራ ፀሐይ በአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለች ዛሬ ደግሞ በአሳዛኝ ሁኔታ በሆሳህና ከተማ የምትገኘው የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በእሳት ውድማለች ። ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ አናውቅም !!!

No comments:

Post a Comment