Friday, March 13, 2015

የመከላከያ ሰራዊት አባላት …

millitary about election
ተገድደን ገዥውን መንግስት አንመርጥም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ አመለከተ፣በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያለ ፍላጎታችንና የማናምንባቸውን ከፍተኛ ጀኔራሎች ስለምትፈልጓቸው ብቻ እንድንመርጣቸው አታስገድዱን፤ ምረጧቸው የምትሉን ዜጎችንም ማንነታቸውን አናውቃቸውም። ስለዚህ ያሁኑ ምርጫ አያስፈልገንም አታስገድዱን በማለት ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረድቷል፣

ይህ አሁን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚታየው ተቃውሞ ትክክለኛና ወቅታዊ እንዲሁም ፍትሃዊ እርምጃ መሆኑን የገለፀው መረጃው ባለፈው 2002 ዓ/ም በተካሄደው ምርጫም ለምን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ያልመረጣችሁ ተብሎ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምክንያቶች እየተፈጠሩ ተባርረዋል ታስረዋል በማለት ምሬታቸውን እያሰሙ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣

No comments:

Post a Comment