Tuesday, March 10, 2015

የባህር ዳር ከተማ …ነዋሪ ህዝብ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በሚያካሂዱ ድርጅቶች ላይ እምነት እንዳጣ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣

bahrdar poletical partyነዋሪ ህዝብ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በሚያካሂዱ ድርጅቶች ላይ እምነት እንዳጣ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣

በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ህዝብ በገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ተማርሮ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው ጭቆናውን ለመግታት ሲልም ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃውሞ ከሚያደርጉ ድርጅቶች ጎን ተሰልፎ ሲታገል የቆየ ቢሆንም ባሁኑ ግዜ ግን የፖለቲካ ድርጅቶች ሊያመጡት የሚችሉት ለውጥ የለም በማለትና ስርዓቱም የፖለቲካ ትግልን የሚያዳክም ስለሆነ። የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ሊወድቅበት የሚችለው የራሳችን ሌላ አማራጭ እንወስዳለን በማለት ሃሳብ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮም ገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች ተቃዋሚ አስመስሎ ሰላዮችን በመላክና ተቃዋሚዎችን በገንዘብ በማታለል እርስ በርሳቸው በማጣላትና በማበታተን ማዳከምን ልዩ ስራው አድርጎ የሚንቀሳቀስ ኢ-ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመሆኑ በጉያው ስር ሆነን ከስልጣኑ ሊወርድ ስለማይችል ራሱ በሚያምንበት የትጥቅ ትግል በማካሄድና በየአካባቢያችን ተደራጅተን ዓመፅ በማስነሳት ስርዓቱን እንገረስሰዋለን የሚል እቋም መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል፣

No comments:

Post a Comment