አርበኞች ግንቦት 7… እየመጡ ነው! አርበኞች ግንቦት 7… አዲስ አበባ ድረስ ሊመጡልህ አይደለም ወይ…
====================================================

ሰሞኑን ወያኔ እየደለቀው የሚገኘው “የጦርነት ክተት አዋጅ” አታሞ ለጆሯችን አዲስ አይደለም፡፡ የተለመደ ከተራና ትርጉምየለሽ የፖለቲካዊና ወታደራዊ ፕሮፖጋንዳ ያላለፈ ፍርሃት ከወለደው ጭንቀት የመነጨ ቅዠት /Nightmare/ የእንቅልፍ ዓለም እንቅስቃሴ /Somnambulism/ ነው፡፡ ህ.ወ.ሓ.ት ጠብመንጃና ጥይት እንጂ የመዋጋት ስነ-ልቦና ፈፅሞ በውስጡ የሌለውን መከላከያ ሰራዊቱን ቢያንስ፣ ቢያንስ በየስድት ወሩ ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች የስጠጋል፣ መልሶ ያሸሻል ያስጠጋል መልሶ ያሸሻል፡፡ በኦጋዴን በኩልም ከኦብነግና አልሸባብ ጋር በተያያዘ እንዲሁ ነው፡፡ አራቱን የሂሳብ ስሌቶች እንኳን ጠንቅቀው የማያውቁት የወታደራዊ ሳይንስ ሽፍታ “ጨዋ” የህ.ወ.ሓ.ት ጀነራሎች ተግባራቸው ሁሉ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ከሆነ ከራርሟል፡፡ ሟች በሌለበት ገዳይ መሆናቸው እና የሚገባላቸው አያገኙም እንጂ ወጣቶችን በሀገር መከላከያ ስም ለስልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ ለመመልመል ማስታወቂያ ማውጣታቸውም ቢሆን ከዚህ በፊት እየተደጋገመ ያሰለቸን ጉዳይ ነው፡፡
ወያኔዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ዛሬም ወደፊትም አይዋጉም፡፡ በ1991 ዓ.ምና በ92 ዓ.ም የተዋጋው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ በትንሹ ከ100 ሺህ በላይ የድሀ ልጆች በከንቱ ረግፈው ቀርተዋል፡፡ ድሉ ግን የወያኔዎች ብቻ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የወያኔዎ ዕቅድና ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የትግርኛ ፕሮግራም “የኤርትራ ጉዳይ ያስተዳደር እንጂ የቅኝ ግዛት አይደልም…” በማለት ከ40 ዓመታት በኋላ ድርጅታቸው ህ.ወ.ሓ.ት አቋሙን መለወጡን ማስታወቃቸው፤ በተጨማሪም ወያኔ-ኢህአዴግ ለምርጫ ቅስቀሳ በየጊዜው የሚለቃቸው ዶክመንተሪዎች የአድዋን ድልና ሌሎችን የህዝቡን ስነ-ልቦና ማስተሳሰሪያ ጠንካራ የታሪክ ክሮች እየመዘዘ ማሳየቱ ከዛሬ 14 እና 15 ዓመታት በፊት እንደሆነው ህዝቡን ለጦርነት በማነሳሳት የድሃ ልጅ የሆኑ ወጣቶችን ደመራ በማድረግ ዳር ሆነው ለመሞቅ ነው፡፡ የሰሞኑ ፕሮፖጋንዳቸው ንፋስ ትክክለኛ አቅጣጫ ይሄ ነው፡፡ ነገር ግን በጠብመንጃ አስገድደው አፉን በማስከፈት የግፍ ገፈት እየጋቱት የሚገኘውን መከረኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደበፊቱ ዛሬም በቀላሉ ማታለል እንደማይቻል ልቦናቸው ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡
ወያኔ ፈለገም አልፈለገም ጦርነቱ አይቀሬ ነው፡፡ ህዝቡ ራሱን መጠየቅና መልስ መስጠት ያለበት ቁምነገር ቢኖር ወያኔ ጦርነት የሚገጥመው ከነማን ጋር ነው? የሚለውን ነው፡፡ ወያኔ በጥሩንባ እንደሚያስለፍፈው ጦርነቱ የምር ከኤርትራ ጋር አይደለም፡፡ ኤርትራ ውስጥና በኤርትራ ዙሪያ በሚገኙ ጀምበር እቶን እሳቷን ከምታራግፍባቸው ነዲድ የሚተፉ በረሃዎች ውስጥ ከመሸጉ የነጻነት ፋኖዎች የምንጊዜም ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች ጋር እንጂ፡፡ እነዚህ የነፃነት አርበኛ ውድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትምህርታቸውን፣ ስራቸውን፣ ስልጣናቸውን፣ ትዳራቸውን፣ አንዳንዶቹ ልጆቻቸውን… ባጠቃላይ የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ከአገርቤት፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ በረሃ የወረዱት ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ሲሉ ብቻ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት፣ ነፃነት፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ሲባል ክቡር ህይወታቸውን ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅተው በሃሩር እየነደዱ ቁራሽ ቂጣ አሸዋና ጭቃ በተቀላቀለበት ድፍርስ ውሃ አወራርደው ከዘንዶ፣ እባብና ጊንጥ ጋር እየታገሉ ውለው የሚያድሩ ናቸው፡፡ ዛሬ የዋጣቸውን ጥቅጥቅ ጨለማ ሳይሆን ከተራራው ወዲያ ከአድማስ ማዶ የምትታየውን፣ የነፃነት ጎህ የቀደደባትን፣ የነገዋን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አሻግረው እዕምሯቸው ውስጥ በሚገኙ ትልልቅ ዓይኖቻቸው እየተመለከቱ መንፈሳቸው በፅናት የተሞላና ነብሳቸው በፍስሃ የተጥለቀለቀች ታሪክ ለመስራት የሚሻሙ ሀዋሪያዎች ናቸው፡፡ ከግማሽ ምዕተ ዓመታት በላይ ሲንከባለል የመጣ የህዝብ የነፃነት ጥያቄ ከትከሻቸው ላይ ያረፈ ለህዝብ ሲባል ልክ አንደ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሞትን ገጥመው ያሸነፉ የዚህ ትውልድ አካል ናቸው፡፡ ስልጣን ፈላጊነት፣ ማናቸውም ቁሳዊ ፍላጎቶችና ልክ እንደ ደደቢቱ ህ.ወ.ሓ.ት ከህዝብ የተደበቀ ስውር ዓላማ ፈፅሞ የሌላቸው አልፋና ኦሜጋ የሆነ ታሪክ በደማቸው ለመፃፍ ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተፈጥረው በአንድ ዓላማ ዙሪያ በመሰባሰብ በአንድነት የቆሙ ንፁህና ጭቁን የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ ይሄንን እውነት የኤርትራ በረሃ ተራሮች፣ በአፅም ስብርባሪ የዳበረው አፈር፣ ሳር ቅጠሉ ጭምር አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ስልጣንና ቁሳዊ ፍላጎት ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ በኤርትራ በረሃዎች ውስጥ አይደለም፡፡ ስልጣንና ገንዘብ ለማግኘት የሚያስፈልገው ህሊናን ሸጦ ከወያኔ መጠጋት እንጂ በረሃ ወርዶ አፈር ላይ መተኛት አይደለም፡፡ ይህ ከበረዶ የነጣ ሀቅ ደግሞ ነገ በተግባር ይገለፃል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ከአንተ ተፈጥረው፣ ላንተ ነፃነት ብለው፣ አንተ የጉልበታቸውና ኃይላቸው ምንጭ ስለሆንክ በአንተ ተመክተው፣ ለአንተ ለመሞት ቆርጠው በረሃ የወረዱ ጀግኖች ልጆችህን ነው ህ.ወ.ሓ.ት ከጎኔ ተሰልፈህ ውጋቸው እያለህ የሚገኘው፡፡ ወያኔ የሚያደርገው ጦርነት አንተ ነፃ ሳትወጣ ወደፊትም በባርነት ቀንበር አንገትህን ታንቀህ በዘረኛ አገዛዝ ስር እድሜ ልክህን እየማቀቅህ እንድትኖር ሲባል የሚደረግ ነው፡፡ ይህ ነው እውነታው እወቀው…
ወያኔ በኤርትራ በረሃዎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ብረት ያነሱ የነፃነት ኃይሎችን ከኤርትራ ጋር በሚደረግ ጦርነት ስም ለመደፍጠጥ የጦርነት ፕሮፖጋንዳ ወጀብ ማስነሳቱ ያለህዝብ ድጋፍ በወታደርና ጦር መሳሪያ ብዛት አንድ ስንዝር እንደማይራመድ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ነው፡፡ አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች፡፡
ምናልባት ሁሉም ህዝብ ጠለቅ ብሎ ላያውቅ ይችላል አላጥሽ፣ ማይካድራ፣ አዲ ጎሹ፣ በረከት፣ ሉግዲ፣…. ላይ በሚመሩት ሰራዊት ላይ የነፃነት አርበኞች የፈፀሙትን የህ.ወ.ሓ.ት ጀነራሎች እነ ሳሞራ የኑስና ሳዕረ መኮንን አሳምረው ያውቁታል፡፡ በእርግጥ የእነሱ ሰራዊት ይሁን እንጂ ታጭዶ አስከሬኑ መሬት ላይ የተነሰነሰው ጭቁን የድሃ ልጅ ነው፤ ያውም በዘር ወንፊት ተነፍቶ በእሱ ደም ምኒልክ ቤተ መንግስት ለመሰንበት እሳት ውስጥ የተማገደ፡፡
በሁለትና ሦስት ታጋይ እንደበግ የሚነዳ ሰራዊት፤ ገና የጥይት ድምፅ ሲሰማ ከተኛበት ተነስቶ በውስጥ ሱሪ ብቻ ከካምፕ ወጥቶ ወደ ከተማ እግሬን አውጭኝ የሚል፤ ከሆነ ቦታ ተነስተው ታጋዮች ወደ እሱ እየገሰገሱ እንደሆነ ሲሰማ ገና ሳይደርሱበት በርቀት ከባዶ ሜዳ ተኩስ ከፍቶ ጥይቱን በመጨረስ ተኩላ እንዳየ የበግ መንጋ በርግጎ የትሙን በመበታተን የሚጠፋ… መከላከያ ሠራዊት እንደሚመሩ የህወሓት ጀነራሎች በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ሰራዊቱ በጠቅላላ ከጓድ ጀምሮ እስከ ዕዝ ድረስ ተመሳሳይ ቋንቋ በሚናገሩ የህ.ወ.ሓ.ት ታማኝ ሰዎች ተጠርንፎ ሳይወድ በግድ በጉልበት የተያዘ እንጂ እሺ ብሎ በፍላጎቱ እንደማይዋጋላቸውም ጭምር የህ.ወ.ሓ.ት ጀነራሎች በጠቅላላ ያውቃሉ፡፡
አዎ በኢሳት ቴሌቪዥን በምሬትና በወኔ ሲናገሩ የሚታዩት የነፃነት ታጋዮች እንደ አኬልዳማና ጃሃዳዊ ሀረካት ለፕሮፖጋንዳ ሲባል ብቻ የሚተውኑ የቴአትር ገፀ-ባህሪያት አይደሉም በገሃዱ ዓለም በኤርትራ በረሃዎች ውስጥ በእውን የሚገኙ እንጂ፡፡ ምሬትና ቁጭታቸው እንዲሁም ወያኔን ለመደምሰስ ያላቸው ወኔ በቴሌቪዥን ስክሪን ከሚታየው በእጅጉ የላቀ ነው፡፡
ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን እየመረጥክ በሰላም ወረዳ በማስቀረት ሌሎችን አንተ የእኔ ወገን አይደሉም የምትላቸውን ጭቁን የኢትዮጵያ ልጆች የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ ጦርነት የምትልከው “መንግስት” ወያኔ ሆይ! ለምን ኤርትራ ድረስ በመዝመት መንገድ ትመታለህ አርበኞች ግንቦት 7… አዲስ አበባ ድረስ ሊመጡልህ አይደለም ወይ…Deginetu Zewdu Abebaw

No comments:
Post a Comment