Saturday, March 7, 2015

እጩ ተወዳዳሪዎቻችን እየታሰሩ ናቸው – አምዶም ገብረስላሴ,ኣቶ ብርሃን ንጉስ ተክለዝጊ የተባሉ የዓረና-መድረክ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከነ ሚስታቸውና ታላቅ ልጃቸው ታሰሩ። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39606#sthash.oEw1MCut.dpuf

ኣቶ ብርሃን ንጉስ ተክለዝጊ የተባሉ የዓረና-መድረክ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከነ ሚስታቸውና ታላቅ ልጃቸው ታሰሩ።
ኣቶ ብርሃን ንጉስ ተክለዝጊ በቖላ ተምቤን ወረዳ የወርቃ ኣምባ ምርጫ ክልል ዓረና-መድረክ ወክለው ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሁነው ቀርበዋል።
ይህ እስር የተፈፀመው በወረዳው ኣስተዳዳሪዎች፣ የሃይማኖት ኣባቶች፣ የቅርብ ዘመዶች ከውድድሩ እንዲወጡ የተሞከረው ልመናና ማባበል ሊቀበሉ ባለመቻላቸው ነው።
1545648_786839981400938_395658053806875682_nኣቶ ብርሃን ንጉስ ተኽለዝጊ በቖላ ተምቤን ወረዳ ስምረት ቀበሌ ለበርካታ ዓመታት ዋና ኣስተዳዳሪና የምሊሻ ኮማንደር ሁኖው ኣገልግለዋል። ኣስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ፍቅር ያሳደሩ ሲሆን ከስልጣናቸው ሲወርዱም ያለ ህንዝብ ፍቃድ ከወረዳ የመጣ ትእዛዝ የተደረገ ነበር።
የወረዳው ኣስተዳዳሪዎች “.. ይህ ህዝባዊ ቅቡልነቱ ተጠቅሞ ዓረና-መድረክ እንዲያሸንፍ ያስችለዋል..” የሚል ስጋት በመፍጠሩ በማሳደራቸው በራሳቸው ትእዛዝ ዛሬ ዓርብ 27 / 06 / 2007 ዓ/ምኣቶ ብርሃን ንጉስ ተኽለዝጊ፣ ባለቤቱና ታላቅ ልጁ በጉያ እስር ቤት እንዲታሰር ኣድርገዋል።
የህወሓት መንግስት የመድረክ በኣፅቢ ወንበርታ እጩ ተወዳዳሪ የሆነው ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉም “..የኣስር ወር እስር ተፈረደብህ..” በማለት ውቕሮ ወህኒ ቤት ማስገባታቸው የሚታወስ ነው።
የመድረክ እጩ ተወዳዳሪዎች እጅግ የከፋ የእስር ዛቻና እንግልት እያደረሱ ያሉ ወረዳዎች ጣንቋ ኣበርገለ፣ እምባ ኣላጀ፣ ኣፅቢ ወንበርታ፣ ቖላ ተምቤን፣ ታሕታይ ማይጨው፣ ዓዲ ግራት ናቸው።
በነዚህ ወረዳ የሚገኙ እጩ ተወዳዳሪዎቻችን ድብደባ፣ እስር፣ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛል። እነዚህ ወረዳዎች ግፉ ያበዙት ብለን የገለፅናቸው እንጂ እንደ ደጉዓ ተምቤን የመሰሉ ወረዳዎችም “..ያለ የወረዳ የድጋፍ ደብዳቤት ቅስቀሳ የሚያካሂድ፣ በራሪ ወረቀት የሚያድል ሰው ካገኛቹ እርምጃ ውሰዱበት..” የሚል ትእዛዝ ለሚልሻዎች ያስተላለፉም ኣሉ።
ያሁሉ የምሊሻ የተኩስ ልምምድ ሲያካሂ የከረመው ዓረና-መድረክ ኣባላት ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ኣልሞ ለመምታት ታሳቢ ኣድርጎ ነበር ማለት ነው።
በኢትዮዽያ ያለው የይስሙላ ምርጫው በትግራይ ያለው ሁኔታ ግን ጭራሽ የምርጫ ጭላንጭል እንዳይታይ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39606#sthash.oEw1MCut.dpuf

No comments:

Post a Comment