Wednesday, March 25, 2015

/ ጀነራል ለገሰ ተፈራ / የመጨረሻ ክፍል

/ ጀነራል ለገሰ ተፈራ / የመጨረሻ ክፍል
ጀነራል ለገሰና ጀነራል አሸናፊ ከግዳጅ መጥተው ለምሳ ሲዘጋጁ ከኮማንድ ፖስት ትእዛዝ መጣ። “......በጀነራል አብዱላሂ የሱፍ የሚመራ ከፍተኛ የሆነ ጦር በባሌ በኩል ጥቃት ከፍቷልና በፍጥነት ድጋፍ እንድትሰጡ.....” የሚል። ሁለቱም ጀነራሎች ምግብ ሳይበሉ ወደ አውሮፕላናቸው ሮጡ። የካምቤራው ( ቦምብ ጣይ ) አብራሪ መስፍን ኃይሌ ቀድሞ ተነሳ። ለገሰ እና አሸናፊ ተከታትለው ተነስተው ቦም ጣዩን አጀቡት። ቦታው ላይ እንደደረሱ ለገስ ለመስፍን ኃይሌ የጠላትን አሰላለፍ እና አቀማመጥ ለመንገር ዝቅ ብሎ መብረር ጀመረ። ሶማሌዎችም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ ተኮሱ። .....የለገሰም አውሮፕላን ተመታች።.... ለገሰም ጠላት እጅ ገባ። ሶማሌዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን አውሮፕላን መትተው ጣሉ። ሰፈራቸው ፌሽታ ሆነ። ፈነጠዙ። ኢትዮጵያን የተቆጣጠሩ መሰላቸው።
ጀግናው ለገሰ በሱማሌዎች ከተያዘ በኋላ በእስር ቤት ለአስራ አንድ አመታት ያህል ቆይቶ በ1981 ተፈታ። ለገሰ በእስር ቤት ሳለ ከፍተኛ ስቃይ ስለደረሰበት ከእስር ተፈትቶ ወደ አዲስ አበባ በመጣበት ጊዜ ሰውነቱ አልቆ ከሞት የተነሳ አጽም ይመስል ነበር፡፡ ሊቀመንበር መንግሥቱ ጄኔራል ለገሠን በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ከተቀበሉት በኋላ የሀገሪቱ የመጨረሻ ደረጃ ኒሻን የሆነውን “የህብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ” ሸልመውታል፡፡ የአሁኑም የኩባው ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮ ለገሰን ከነቤተሰቡ ጋብዘውታል።
ክብር ለጀግኖቻችን !
አመሰግናለሁ......



No comments:

Post a Comment