Saturday, March 14, 2015

ትግሉን በየፈርጁ (የዋሺንግትንና አካባቢው የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል

March 13, 2015
የኢትዮጵያ የአንድነትና የዲሞክራሲ ሃይሎች በጠላት ጥቃት ደርሶባቸው ተጎድተው ተሸማቀው አንገታቸውን እንዲቀብሩ ሲገደዱ አድርባይ ሃይሎች በመድረኩ መቧረቃቸው የሚጠበቅ ነው፤ይህንን ጊዜያዊ ክስተት እንደዘላለማዊ ሃቅ የሚወስዱ ካሉ እጣ ክፍላቸው ተስፋ መቁረጥና ጨለምተኝነት ይሆናል። ከጨለማው ባሻገር የኮከቢቱን ብርሃን የሚያዩ ግን ለወያኔ ግፍ የማይበገሩ የሃቅን አቸናፊነት የኢትዮጵያን ትንሳኤ አይጠራጠሩም።

ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል እንደሚባለው ዛሬ ወያኔ የተባለው መርገምት የጣር በትሩን በዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ላይ እያሳረፈ ይገኛል፤ ይህን የግፍ አበላ ለመቋቋም ዜጋው ሁሉ እምቢኝ አልገዛም እያለ በሁሉም አቅጣጫ ሁሉንም የትግል አይነት ያልጀመረው ለመጀመር የጀመረው ለመቀጠል ለፍልሚያው እየተሟሟቀ በሚገኝበት ሰዓት ይህን ሃቅ እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ የሚሆነው ፍጡር ያለመንቃት መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም እኛ ግን ከተስፋው መቁረጥ አለም የሌለንበት ሁሉንም ጸረ ወያኔ ሃይላት የማበረታቻ ቃል ብቻ ሳይሆን አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ለመለገስ በያለንበት ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፤ ዛሬ በሃገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች የመብት ጠያቂዎች፣ የድምጻችን ይሰማ ሚሊዮን ሙስሊሞች ሌሎች ተጠቂ ዜጎች በሙሉ እያስገመገሙት ያለ ህዝባዊ እምቢተኝነት በሌላው ፈርጅ ደግሞ ተምቹን የወያኔ ስርአት በብረት ለመፋለም ስልታቸው ያደረጉ የነጻነት ታጋዮች በሙሉ በየፈርጃቸው ይበርቱ እያልን እኛም በውጪው አለም በስደት ያለነው የጋራ ግብረሃይል አባሎች ከኢትዮጵያ ውጪ ብንሆንም ኢትዮጵያ ግን ከኛ ውጪ አይደለችምና የበለጠ ለመትጋት ያለንን አቋም በኢትዮጵያ ስም ነው የምናረጋግጠው።
እኛ በተለያዩ የትግል ስልት በሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ስር ያለንና እንዲሁም ባገርወዳድነት ስም በግልም የምንቀሳቀስ ከሌሎች የምብትና የፍትሕ ተቋሞች ጋር በጋራ እየሰራን በመጨረሻው ስዓት ባለው ግፈኛ የወያኔ ስርዓት ላይ ትግሉን ለማጧጧፍ ለምቢተኝነቱ ጧፍ በግምባር ቀደምትነት እንዳለን ስንገልጽ አበክረን የምንለው ነገር አለ፤ ለጋራ ሃገራችን ኢትዮጵያ፣ ለሁላችን ጠላት ከሆነው የወያኔ ስርዓት ለመገላገል ዋናው አብነቱ የታጋዮች ህብረቱ ነውና በጸረወያኔው የትግል አምባ የተሰለፉት ሁሉ በየፈርጃቸው እንዲተባበሩ ስንል በትሕትና እንገልጻለን።
ይህ በሆነበት በትንንሽ ነገሮችና በትግል አካሄዶች የሃሳብ ልዩነት ቢኖርንም ልዩነቱን በቤታችን እየፈታን በዋናው ጠላት ላይ እያበርን ትግላችንን እስከድል ደጃፍ እንቀጥል እንላለን።
ኢትዮጵያ ባንድነትና በነጻነት ለዘላለም በክብር ትኖራለች!
የዋሺንግትንና አካባቢው የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል።

No comments:

Post a Comment