Saturday, March 7, 2015

በኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት …

meeting 31 regiment about administrationማእከላዊ እዝ ውስጥ የአስተዳደር ችግር እየከፋ በመሄዱ ምክንያት የእዙ ሰራዊት ሃይለኛ ጥያቄ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ከሰራዊቱ ውስጥ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ ገለፀ፣
በማእከላዊ እዝ ከየካቲት 11 እስከ 18 /2007 ዓ/ም ጀምሮ በውስጣዊ የአስተዳደር ጉዳይ ላይ የሚመለከት ስብሰባ እንደተካሄደ የገለፀው መረጃው በስብሰባው ላይ በሰፊው ከተነሱት የአስተዳደር ችግሮችም ደመወዛችንም እንኳን ኑሯችን ልንመራበት ይቅርና ለአንድ ቀንም ሊሸፍንልንም አልቻለም ሲሉ ችግራቸው እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል፣
ሰራዊቱ በየመድረኩና በየወቅቱ እያቀረብናቸው ካሉት ችግሮቻችን መፍትሄ ለምን አይደረግላቸውም?” ሲሉ መጠየቃቸውንና በሰራዊቱ ውስጥ ከ24 ሰአት ጀምሮ እስከ አመታዊ ፍቃድ እንደተከለከለ በመግለፅ ሰራዊቱም ለምን ተከለከልን ብሎ በጠየቀበት ጊዜ በስብሰባው መሪዎች አወንታዊ ምላሽ ማግኘት እንዳለተቻለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣

No comments:

Post a Comment