Sunday, March 8, 2015

( ወያኔ የረጨው መርዝ ) አማረ ፣ ኦሮሞ የሚሉት በሽታ - ግርማ ካሳ

( ወያኔ የረጨው መርዝ )
አማረ ፣ ኦሮሞ የሚሉት በሽታ - ግርማ ካሳ
እስቲ እነዚህን ፎቶዎች ተመልከቱ። አንዱ የኦነግ ካርታ ነው። ሌላው ደግሞ የአማራ መንግስት ብለው ያወጡት ነው። የኦነግ ካርታ እንዳለ ቀድሞ የሸዋ ክፍለ ሃገር ተብሎ የሚጠራዉን እንዲሁም በርካታ መሬቶች ከወሎ ያጠቃልላል። የአማራ መንግስት ካርታ ደግሞ የቀድሞ የቤጌምድር፣ የጎጃም፣ የሸዋና የወሎ ክፍለ ሃገራትን፣ አሁን ወደ ትግራይ በሃይል የተጠቃለሉ ሁምራ፣ ወልቃት፣ ጠገዴን ፣ ጨለምታና አላማጣን ያጠቃልላል።
የኦነግ ካርታ ከሞላ ጎደር አሁን ኦሮሚያ ተብል የምትጠራዋን በኋይል በሕዝቡ ላይ የተጫነችዋን ክልል ትመስላለች። ለምን ቢባል. ኦሮሚያ የምትባል ክልል ስትፈጠር፣ ኦነግ የመንግስት አካል ስለነበረ።

እንግዱ ሁለቱም ካርታዎች አዲስ አበባን እና የሸዋ ክፍለ ሃገርን ወደ እነርሱ ቀላቅለዋል። ካርታዎቹ ተግባራዊ ይሁኑ ከተባለ፣ ሸዋን እና አዲስ አበባን የአማር መንግስት ዉስጥ ለማድረግ፣ ወይንም በኦሮሚያ ዉስጥ እንድትቀጥል ለማድረግ፣ ከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ሊደረግ ነው ማለት ነው። አማራ የሚባሉት አሁን ያለችዋን ኦሮሚያ መቼም አይቀበሉም። ኦሮሞ የሚባሉት ሸዋ ወደ አማራ መንግስት መግባቱን በጭራሽ አይቀበሉም።
አምስት ሚሊዮን የሚሆነውን የአዲስ አበባና አካብቢው ነዋሪን ኦሮሚያ የሚሉ ሰዎች ገፍተው ወደ ጎንደርና ጎጃም ሊጥሉ ወይም እንዳለ ሊፈጁት ነው ኦሮሚያ የሚሉት። አይሆንም። አይሰራም። ትርፉ የርስ በርስ ጦርነትና የዘር መተላለቅ ነው።
እነዚህ ሁለቱም ካርታዎች ሕዝቡን ወደ ጦርነት የሚመሩ ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ሰላም ካርታዎች ናቸው። አማራ፣ ኦሮሞ እየተባሉ ለሚጠሩት ወግኖች የሚጠቅም አይደለም። ይሃ አይንቱን ካርታም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ይለዉምም። ለምሳሌ ሸዋ አማራ አይደለም ፣ ኦሮሞም አይደለም። ሸዋ ሸዋ ነው። ሸዋ ግማሹ አማርኛ ተናጋሪ፣ ግማሹ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ነው። የሸዋ ሕዝብ ከጥንት ተፋቅሮና ተዋልዶ የኖረ ነው። ሁለቱንም ቋንቋዎች የሚናገሩ የሸዋ ነዋሪዎች ብዙ ናቸወ፡፡
እነዚህ ካርታዎች ላይ የምናየዉን እብደት ትተን ፍቅርና መስማማት ሊያመጣ የሚችል መፍትሄ ማስቀመጥ አለብን። ለምሳሌ አማርኛም፣ አፋን ኦሮሞ የሥራ ቋንቋ የሆነበት የሽዋ ክልል በማበጀት ፣ በፍቅርና በመተባበር መቀጠል ይቻላል።
ሌላው እነዚህ ኦሮሞ ነን፣ አማራ ነን የሚሉ መርሳት የሌለባቸው ነገር አለ። ኦሮሞም አማራም የሆኑ፣ የተደባለቁ፣ ኦሮሞም አማራም ያልሆኑ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንዳሉም መርሳት የለባቸው።
በዚህ ጽሁፍ ላይ ሸዋን እንደምሳሌ ጠቀስን እንጂ ተመሳሳይ ሐሳብ በሌሎች ቦታዎችን ማንሳት ይችላል። ይሄ ዘር ላይ ያተኮረ አስተሳሰብ በሽታ ነው። ዘረንኘት በሽታ ነው። የሚያዋጣው ተከባብረን ፣ ተስማምተን ለሁላችንም የሚበጅ፣ የሁላችንም መብት የተከበረናት አገርን መመስረት ነው።
ይሄ እንዳይሆን አሁን ያለው ዘረኛው የሕወሃት መንግስት እንቅፋት እንደሆነ፣ አሁን እያየን ያለነው የዘር በሽታ እንዲስፋፋ ፍላጎት እንዳለው የታወቀ ነው። አማራ ፣ ኦሮሞ እያለ፣ በተናጥል ሁለቱን እየመታ፣ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርገዉን ጥረት መቀጠሉ አይቀርም። ሆኖም መንቃት አለብን። “እኛ እና እነርሱ ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ “ ወዘተረፈ ማለታችንን አቁመን “እኛ” ማለት መጀምር አለብን። እያንዳንዳችን በዘራችን ሳይሆን በስብእናችንና በተግባራችን መመዘን አለብን። መታወቂያችን ላይ ዜግነታችን እና የትዉልድ ቦታችን ብቻ ከተጻፈ ይበቃል።

No comments:

Post a Comment