(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ሕዝብን ትጥቅ ለማስፈታት ተንቀሳቅሶ ሽንፈትን የተከናነበው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አጋዚ ጦር ወደ ም ዕራብ አርሲ በተመሳሳይ ተንቀሳቅሶ በሕዝብ ድባቅ እየተመታ መሆኑን እና በአሁኑ ወቅትም በም ዕራብ አርሲ ሁለት ጫካዎች ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ::
ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ለምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ እና ለአጄ ከተማ ቅርብ በሆኑት ጣጤሳ እና አርጆ ጫካ ውስጥ ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ባለበት ወቅት ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው::
የሕወሓት መንግስት ሕዝቡን ትጥቅ አስፈታሁ ብሎ ወደ ሰላማዊ ገበሬዎች ጠመንጃ የታጠቁ የአጋዚ ሰራዊቶችን መላኩን ያስታወቁት የዜና ምንጮቹ እነዚህ ወታደሮች እንደሚመጡ አስቀድሞ መረጃው የደረሰው ሰላማዊው የአካባቢው ገበሬ አድፍጦ በመጠበቅና ራሱን በመከላከል እርምጃ ወስዷል:: በዚህም መሰረት ይህን ኦፕሬሽን የመራው የአጋዚ ሰራዊት አዛዥ መኮንን የተባለ ወታደር አጄ አካባቢ የሚገኘው ጫካ ውስጥ ተገድሏል:: ፎቶም ተነስቶ ሕዝብ እንዲያውቀው ተደርጓል:: ከመኮንን ጋር አብሮ ሌሎች አራት የአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ ከሕዝቡም 3 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል::
የሕወሃት መንግስት በደረሰበት ምት ጦሩን ከነዚህ ጫካዎች አሽሽቶ ተጭማሪ ሃይል በሻሸመኔ በኩል አምጥቶ በአሁኑ ወቅት ከሕዝቡ ጋር እየተታኮሰ መሆኑን ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመልከታል::
ይህን ጉዳይ ዘ-ሐበሻ እየተከታተለች ለመዘገብ ትሞክራለች::
No comments:
Post a Comment