Thursday, September 29, 2016

ከታጋይ አርበኛና ከፍተኛ አመራር "ክፈተው አሰፋ" የተላለፈ የትግል ጥሪ\




ሃገር ቤትም ሆነ በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጰያው ምሁራን, ለመከላከያሰራዊት, ለመምህራን, ለአርሶአደሩ, ለተማሪው, ለወዝአደሩ, ጾታ ዘር ያለየ የትግል ጥሪ" በተለይ ለምሁራን÷ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት የብሄር ፖለቲካ አዘቅት ውስጥ መዞ ለማውጣት" ወዳንድ ያስተሳሰብ መንደር ለመንደርደር የግል ፍላጎት ያለው? የግል ፍላጎቱን ወደ ጎን በመተው» በተለይ ስልጣን, ዝናን, ገንዘብን የመሳሰሉ ለሰው ልጅ መጨካከንንና ሸርን የሚያስተምሩ ናቸውና እነዚህን ፍላጎቶች ወደ ጎን ትተን" ሃገርንና ህዝብን ለማዳን ተግተን በአንድነት እንስራ÷ የትጥቅም ትግልም ሆነ የሰላማዊ ትግል በተናጥል በበዛ ቁጥር ሀይላችን እየተመናመነ, እየተበታተነ ስለሚሄድ የማሸነፍ እድላችን ጥያቄ ውስጥ እንዳይገባ ካሁኑ ወዳንድ መንደር እንሰባሰብ::

ያርበኝነት ትግል እንደሆነ ውርሳችን ነው:: ኢትዮጰያ የኖረችውም በአርበኝነት ነውና:: 
ታድያ ያ አርበኝነት ዛሬም ያስፈልጋል" ለዚህም ነው ከሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሦስት ዓ. ም ጀምሮ " የኢትዮጱያ ህዝብ አርበኞች ግንባር" ወያኔን እንደወራሪ በመቁጠር ያርበኝነት ትግል ያስፈልጋል ያለው:: ምክንያቱም ወያኔ በአላማውም ሆነ በትውልዱ, በደሙ, ኢትዮጰያዊ ሆኖ አያውቅም:: አሁንም ቢሆን ከፊት ለፊታችን ትልቅ ችግር እንደተጋረጠብን ይታየኛል" ለሚቀጥለው ትውልድ የተበታተነ የፖለቲካ አጀንዳ እንዳናስተላልፍ በጥንቃቄ የፖለቲካ ውሳኔችንን እናስተካክል:: 
ስለሆነም ይህ በኢትዮጵያ ምድር የሚኖረው ህዝብ ለሃገሩ የሚያስፈልጋት ያርበኝነት ትግል ነው:: ወያኔ ወራሪ ነው እንጂ ኢትዮጱያዊ አይደለም ለዚህም መስረጃ ማቅረብ የሚያስፈልገው አይመስለኝም የተረጋገጠ ሀቅ ስለሆነ:: እናም ወያኔን ለመጣል የሚያስፈልገን የተበታተነ የትግል ስልት ሳይሆን" አንድነትን መሰረት ያደረገ የጠራ ከማንኛውም አላስፈላጊ ከሆነ ቆሻሻ አስተሳሰብ የፀዳ ግልፅ የትግል ስልት ነው::

አንድነት ሀይል ነው//
ድል ለአርበኞች ግንቦት ሰበሰት ሰራዊት በሙሉ
ሼርር ማረግ አንርሳ

2 comments:

  1. sure we have to organised and struggle to defeat them

    ReplyDelete
  2. THIS IS OROMO NOT OROMO THAT IS ANHARA NOT AMHARA THAT US SOMALAE NOT SOMALAT ETC IS NOT CURRENTLY NECESSARY.WE HAVE ONE ETHIOPIAN PEOPLES ENEMY IE WEYANAE WHO ARE KILLING THE PEOPLE.LET ME TELL WE NEVER STOP THE KILLING UNLESS WE STAND TOGETHER.TO FINALIZE THE STARTED MOVEMENT AS THE PATRIOT KEFETEW CALLING US LET GIVE HIM PRACTICAL ANSWER.OTHER WISE WE REMAIN AS SERVENT OF WEYANAEE FOREVER

    ReplyDelete