Saturday, September 24, 2016

#Boycott_TPLF_Apartheid campaign ~ ለወገን ጥሪ የወገን ምላሽ ~


ህዝባችን ለፍትህ ፤ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚያካሂደውን ትግል በሃይል ለመደፍጠጥ ህወሃት ልዩ ቅልብ ሠራዊቱን በማሰማራት ፋሽስታዊ ጭፍጨፋበወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ይገኛል። የ25 ዓመቱ የግፍ አገዛዝ የመረረው ህዝባችን ግን ለዚህ የአጋዚ ጭፍጨፋ ሳይበገር ግንባሩን ለጥይት በመስጠት መተኪያ የሌለውን ህይወቱን ለነጻነቱ ሲል እየገበረ ነው። እኛ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵዩያዊያን ወያኔ ወገኖቻችንን ለመግደል የሚጠቀምበትን መሳሪያ መግዣ ለማሳጣት በሚከተሉት ጥቅማጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ እንመታበታለን። የጎንደር ህዝብ የዳሸን ቢራን ከተጫነበት አውርዶ ሰባበረው እንጂ ለመጠጣት እንኳን አልጓጓም። እኛ በተሻለ ደረጃ የምንገኝ ወገኖቹ አማራጭ እያለን የወያኔን ምርቶች በመግዛት ወያኔን አናጠናክርም ።በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ በግልም ሆነ በቡድን የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውሰድ የትግል አጋርነታችንን እንገልጻለን።
1. ወያኔ እና ግብረአበሮቹ ከኢትዮጵያ እያስመጡ የሚሸጡዋቸው ሸቀጦችን፣ እንጀራ፣ቡና፣ መጠጥ፣ ጤፍ ድቄት፣ የመሳሰሉትን አንገዛም፣
2. ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ የታሰቡ እቅዶቻችንን እንሰርዛለን ወይም ለሌላ ጊዜ እናስተላልፋለን፣

3. ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስትመንት ለማድረግ የሚያስቡ ኢትዮጵያዊያን ፤ የውጭ ዜጎችና ድርጅቶች እቅዳቸውን እንዲያዘገዩ እናግባባለን፣
4. ህወሃት ለህዝባችን ፍቃድ እስኪንበረከክ ድረስ ለወያኔ ባለሥልጣናትና ለሥርዓታቸው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠቀም እናቆማለን። አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞን ወደ አገር ቤት ለመጓዝ ከተገደድን ሌላ አየር መንገዶችን እንጠቀማለን፣
5. በወያኔና የጥቅም ሸሪኮቹ የሚሰጡ ማናቸውም ዓይነት አገልግሎቶች ከመጠቀም እንቆጠባለን፣
6. የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ከአገዛዙ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ካላቋረጡ ከየትኛውም ማህበራዊ ግንኙነት እናገላቸዋለን፣
7. የህወሃት ባለሥልጣናት ከአገር ዘርፈው ወደ ውጪ የሚያሸሹት ገንዘብና ንብረት እየተከታተልን እንመዘግባለን፤
8. ህዝባችንን የሚያስጨፈጭፉ ፤ የሚያሳስሩና የሚያስገርፉ ወደ ውጭ ሲመጡ እግር እግራቸውን እየተከታተልን እናጋልጣቸዋለን፤ እናሸማቅቃቸዋለን!

No comments:

Post a Comment