Sunday, September 18, 2016

#Ethiopia ወያኔ ነፍሶበታል። የሕዝቡን ትግል እያለሰለሱ እንዲያጣጥሉና የወያኔን ሃያልነት እንዲሰብኩ ለሚዲያዎች በጀት ሊመደብ ነው። #MinilikSalsawi

Minilik Salsawi - mereja.com - ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ባይሳካም ለስልጣኑ ርዝማኔ ተስፋ የማይቆርጠው የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በሃገር ውስጥ ላሉ ሚዲያዎች በተለይ በነጻ ፕሬስ ስም ለሚንቀሳቀሱ ጋዜጦች የ ኤፍ ኤም ራዲዮኖች የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በኣሉባልታ እንዲከፋፍሉ እንዲሁም የሕዝቡን ትግል እያለሰለሱ እንዲያጣጥሉ በጀት በመመደብ ስራ ለማስጀመር ማቀዱን የደህነት ቢሮ ምንጮች ተናግረዋል።

ለዚሁም ሪፖርተር፣ ካፒታል፣ ፎርቹን፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የ ኤፍ ኤም ራዲዮኖች ግንባር ቀደም ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ከሕዝቡ ትግል ጋር ተመሳስለው በመግባት እያለሰለሱ ሕዝቡን ተስፋ በማስቆረጥ የወያኔን ሃያልነት የሚያሰርጹ ጽሁፎችን በማተም እንዲሁም ኣጀንዳ የሚሆኑና ሕዝቡን ስጋት ውስጥ የሚከቱ ዬWስጥ ሽብር የሚፈጥሩ ጽሁፎች ከደህንነት ቢሮ ተጽፈው ሲላኩ በየኣምዶቻቸው በማውጣት እንዲሰሩ ለየጋዜጦቹ ከ150 ሺህ ብር እስከ 300 ሺህ ብር በጀት ሊመደብ መዘጋጀቱን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። ኣክለውም የግል ራዲኦ ጣቢያ የተባሉ በተለየ መልኩ ኣትኩሮት ተሰጧቸው በትጋት እንዲሰሩ ጉዳዩ የሚመለከተው ግብረ ሃይል ኣስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል የሚል ውስኔ መወሰኑ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
እንዲሁም የኦሮሞ እና የኣማራን ተቃውሞ በተመለከተ በስሱ እንዲዘግቡና ኣንዳንድ የሕዝብ ጽሁፎችን በም ኣስገባት እንዲያትሙ ጎን ለጎንም ይህንን የሚያከሽፍ ተደጋጋሚ ጽሁፍ በማውጣት ሽፋን እንዲሰጡ ታቅዷል።ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የሙስሊሞች ትግልን ኣሳንሰው ኣጠልሽተው እንዲዘግቡ 2013 G.C. ለ አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር ጋዜጣ ሰባ ሺህ ብር በኣንድ ዜና ብቻ ቢከፈላቸውም የታቀደው ሳይሳካ ቀርቶ መክሸፉና መጋለጣቸው ይታወሳል፥ http://minilik-salsawi.blogspot.com/2013/01/blog-post_9.html ኣሁን የራዲዮ ሚዲያዎችን ያካተተው ይህ የክሽፈት ዘመቻቸው ወደ ባሰ መቀመቅ ይዟቸው ይወርዳል ሲሉ የደህንነት ቢሮ ምንጮች ይናገራሉ።
የሕዝብን ትግል ማክሸፍ የሚቻለው ለሕዝብ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ በመስጠጥ ካልተቻለ ስልጣን በመልቀቅ ነው የሚሉት ምንጮች ወታደራዊው ክፍል እያጉረመረመ መሆኑን ለደህንነት ቢሮ የሚመጡ ሪፖርቶችን ጠቅሰው በተጨማሪ ተናግረዋል፥ ስርዓቱ የመጨረሻው ሰኣት ላይ ስለሆነ የሚሰራቸው የሚያወያያቸው የሚፈጽማቸው የሚያስባቸው ነገሮች ሁሉ የጥፋት መሆናቸውን ምንጮቹ ኣስረግጠው ተናግረዋል።#ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment