Thursday, September 22, 2016

የብአዲን ጉባኤ አባላት ” ዳግማዊ ኮረኔል ደመቀ” ያሉት ጄግና ተከሰተ [ልያ ፋንታ] - See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/21645#sthash.6adFmxL5.dpuf

andn-satenaw-news-3
የአማራ ክልል ብአዲን ጉባኤውን ለአንድ ሳምንት ማለትም እስከ አለፈው አርብ ድረስ ለማጠናቀቅ እቅድ ቢንድፍም ሌላ ተጨማሪ ሶስት ቀናትን በመውሰድ ከትናንት በፊት ሰኞ እለት ባለ መስማማት በልዩነት ተጠናቅቋል።
የጉባኤው አባላት ከማዕከል ( አዲስ አበባ) የመጡት፣ በረከት ሰምኦን ፣አዲሱ ለገሰ፣ ደመቀ መኮንን ያሉበት እና ከክልሉ ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ጄምሮ፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙሁሉም የዞን እና የከተማ መስተዳደር አመራሮች የተሳተፉበት ትልቅ ጉባኤ ነበር። ስብሰባው ከአለፉት ጊዜያት በበለጠ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ የተካሄደበት በአባይ ማዶ ጫፍ ላይ በተንጣለለ ስፍራ የተሰራው አዲሱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ ሲሆን፣ከውስጥ የተሰበሰቡ የጉባኤ አባል ካድሬዎች አብዛኛዎቹ በትግራይ ክልል ተደፍረናል፣ ህዝባችን በአጋዚ በግፍ እየተገደለ ዝም ማለት አልነበረብንም በሚል ቁጭት ነበር በጉባኤው የታደመት።
የተለመደው ቅጥፈት የተመላበት ሪፖርት ከአዲስ አበባ በመጡት አመራሮች ከተደመጠ በኋላ አስተያየት በመስጠት ፖለቲካዊ ሁኔታውን እንዲገመገሙ ካድሬዎች ተጋበዙ።
በዚህ ጊዜ ካድሬው ጎን ለጎን መተያየት ጄመረ ፣ ለተወሰነ ደቂቃም ፀጥታ ነገሰ።


ከወደፊት ወንበር የቅርብ ርቀት አካባቢ ድንገት ፈቃድ ለመጠየቅ አንድ እጂ ተዘረጋ ። የሁሉም አይን በአግርሞት ከሰውየው ላይ አረፈ።
አመሰግናለሁ፣ በማለት ንግግሩን በመጄመር ወገኖቼ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ መከላከያ ፣ግምሩክ ፣ ቴሌ፣ እና ግምሩክ የመሳሰሉት በአንድ ዘር በተያዙበት ሀገር
የአማራ የመንገድ ስራ ክንውን ከትግራይ ጋር ብንመለከት፣ በኢንዱስትሪ ዘርፍ በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል ያለው ልዩነት ተጨባጭ ማስረጃዎች በአሀዝ በማቅረብ የሰማይ እና የምድር ያህል ርቀት ያለው መሆኑን ማመን አለብን። ወክለነዋል የምንለውን ህዝባችንን እስከ መቼ እየዋሼን እናታልለዋለን? በማለት መብረቅ የሆነ ንግግሩን ሲቋጭ የስብሰባው ታዳሚ እጂግ የጋለ እና ረዥም ደቂቃ በወሰደ ጭብጨባ የተናጋሪውን ሀሳብ ደገፈ።


የብአዲንን አባላትን የፍርኃት ደመና ገፍፎ ጄግንነቱን በጉባኤ አዳራሹ አወጄ፣ የጉባኤው ታዳሚ የጄግና ክብር ሲደርበው ተስተዋለ።
አድርባዩ እና የአማራ ህዝብ ጠላት የሆነው ታደሰ ጥንቅሹ ( ታደሰ ካሳ) እጁን በማውጣት ቀደም ሲል የተናገረውን ጄግና መስሪያ ቤት በመጥራት የክልሉ ህዝብ አንተ በምትሰራበት መስሪያ ቤት መጉላላት ይደርስበታል ይህን የማረም ብቃት አላሳያችሁም በማለት ለማሼማቀቅ ያቀረበውን ሀሳብ።የመጄመሪያው ጄግና ተናጋሪ በድጋሚ ተስፈንጥሮ በመነሳት።
አሁን የስራ ግምገማ ሳይሆን የክልላችንን ፖለቲካ ችግር የምንፈታበትአጄንዳ እና ግመወገማ ጊዜ ነው።


ታደሰ ንገረኝ ካለከኝ ደግሞ አንተ የጥረት የቦርድ ሰብሳቢ እያለህ ምን እንደሰራህ የማናውቅ እንዳይመስልህ በማለቱ ሁለተኛ ጊዜ የጉባኤው ተሳታፊ መስማማቱን በጭብጨባ ሲገልጽ ታደሰ ጥንቅሹ በሀፍረት ተሸማቅቋል።


ከዚያ በኋላ ልቡ የቆሰለ ካድሬ ሁሉ እየተነሳ፣ ተው እንጂ የትግራይ ገበሬ ወታደር እየሆነ ህዝባችንን እስከ መግደል መብት ተሰጥቶት እያየን ዛሬም ልትዋሹን ትፈልጋላችሁ? ህዝባችን የሚጠቃው አማራ ሆኖ በመገኜቱ ብቻ ነው። አሁን ክልል ሶስትን የሚያስተዳድር ህዋህት እንጂ ብአዲን አይደለም ። በዚህ መተማመን አለብን በማለት የመጄመሪያውን ተናጋሪ በተደጋጋሚ ስሙን በማውሳት እውነት እንደተናገረ መስክረውለታል። ጉባኤው።ቡጢ ብቻ የቀረው እስኪመስል ሀሳብ የተንሼራሼረበት እና ያለ መስማማት የተዘጋ መሆኑ ታውቋል።
የህ ከላይ የጠቀስኩት ጄግና ፍረሀትን በመግደሉ የብአዲን ካድሬዎች በሻይ የዕረፍት ጊዜያቸው ዳግማዊ ኮረኔል ደመቀ የሚል ስያሜ እንደሠጡት አንድ የብአዲን ሰው ከላኩልኝ መረጃ አረጋግጫለሁ።

ስለ መረጃው ከልብ አመሰግናለሁ
ልያ ፋንታ
ከዋሽንግተን ዲሲ
- See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/21645#sthash.6adFmxL5.dpuf

No comments:

Post a Comment