Thursday, September 29, 2016

ለአትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ ወገኖች

|« ያኔ በጤነኝነቴ ጊዜ ሩጫ ስወዳደር በክፍያ የድርጅታቸውን ዓርማ ለብሼ እንድሮጥ የጠየቁኝን ድርጅቶች እምቢ ብዬ የኢሳትን አርማ ለብሼ መሮጤ በጊዜው ለሀገራዊ ትግሉ ካበረከትኩት አስተዋጽኦ በተጨማሪ አሁን ለምገኝበት ሁኔታም ትክክለኛ ውሳኔ ነበር። ምክንያቱም በጊዜው ለሳንቲም ብዬ ብሮጥ እስካሁን ሳንቲሙን አጠፋው ነበር፤አሁን የሚደርስልኝም አይኖርም ነበር። ለማይጠፋው ሀብት ለህዝቤና ለሀገሬ በመሮጤ ግን እነሆ በክፉ ቀኔ ህዝቤ ከጎኔ ቆመልኝ። ከሀብት ሁሉ ትልቁ ሀብት ሚሊዮን ዶላር ሳይሆን ሰው ነው። ሰውን፣ወገንን የመሰለ ትልቅ ሀብት የለም።|”
በከፋ ችግር ላይ ለሚገኘው ለአትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ $11,575(አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰባ አምስት ዶላር) ደርሷል።አትሌቱ ድጋፍ ላደረጋችሁለት፣ እንዲሁም ስልክ በመደወል አለኝታችሁን ለገለጻችሁለት ሁሉ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል። ምናልባት ልትረዱት ፈልጋችሁ መረጃው የሌላችሁ ካላችሁ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን በቀላሉ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል፦

No comments:

Post a Comment