Monday, September 19, 2016

በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የኮር አመራሮች ስብሰባ ካሳ ተ\ብርሀን በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እንደታገደ ታወቀ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/66138
በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የኮር አመራሮች ስብሰባ ካሳ ተ\ብርሀን በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እንደታገደ ታውቇል።
hqdefault-1
ስብሰባው በነ በረከት ስምኦን፣በነ ተፈራ ዋልዋ፣በነ ህላዌ፣በነ ገዱ፣በነ ደመቀና ሌሎችም የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ሲሆን ተሰብሳቢዎች ከስልክ ጀምሮ ምንም አይነት የቴክኖሎጅ ውጤቶችን መጠቀም እንደማይቻሉ እና ሦስት ጊዜ ተፈትሸው እንደሚገቡ ተናግረዋል።ስብሰባው በወልቃይት ጉዳይና በህዝቡ እምቢተኝነት ዙሪያ ከሚነገረው መልስ ጋር ተያይዞ ከኮር አመራሮች ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ ከ3_7\1\09 ሊጠናቀቅ የነበረው ስብሰባ ተራዝሞ ዛሬም በመካሄድ ላይ ይገኛል።የክልሉ ስቢል ሰርቢስ ም\ሀላፊ የሆኑት አቶ ሻምበል በመረጃና ማስረጃ የህዝቡን ጥያቴ በማቅረብ ግንቦት ሰባት ነህ እስከመባል ደርሰዋል።”ህዝቡ ተጨቁኖ ቆይቷል።አሁን ግን በየቦታው ተነስቶብናል።ሊበላን ነው ምን ምላሽ እንስጥ?” ብለው ለጠየቁት ጥያቄ አቶ በረከት አርፈህ ተቀመጥ”አንተን የሚመለከትህ የሲቪል ሰርቢስ ሪፖርት ነው “በማለት መመለሱን ተከትሎ “የተሰበሰብነው በወልቃይት ጉዳይ መሰለኝ።እንጂማ አንተ የምትመራውን ኢፈርት ብናነሳ ኑሮ ከነ ድርጅትህ መግማትህን እንሰማ ነበር “በማለት ለሰጡት አፀፋ ከተሰብሳቢው የድጋፍ ጭብጨባ ተደርጎላቸዋል።


አቶ ገዱ ከአመራሮች ሁሉ” ወልቃይት የትግራይ ነው “ብለው በድፍረት ያልተናገሩ ሲሆን “እርስ በርስ መተላለቃችን አይቀርም” በማለት አሳስበዋል።”ስብሰባው ከህወሀት ተልኮ የፀዳ አይደለም።በረከት ህወሀት ነህ “የሚል አስተያየት እንደሚበዛ ተሰብሳቢዎች ተናግረዋል

No comments:

Post a Comment