Sunday, January 31, 2016

ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳዎች ይልቅ የሙጋቤ መልእክት ትኩረት አግኝቷል January 30, 2016


የአፍሪካ ህብረት የሊቀመንበርነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት የዚምቧቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ26ኛው የመሪዎች ስብሰባ ለተተኪያቸው ቦታቸውን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ ህብረቱን በመወከል በተባበሩት መንግስታት፣በነጮችና በባራክ ኦባማ ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡
ሙጋቤ ንግግር ለማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ሲያመሩ ከአጋሮቻቸው ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፣ ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው ከተለመደው ከፋ ባለ መልኩ ምዕራባዊያንን፣ነጮችንና የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት አብጠልጥለዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን የ91 ዓመቱ ሙጋቤን ንግግር እያደመጡ በተቀመጡበት ወንበር በጭንቀት ተውጠው ተስተውለዋል፣ ‹‹ሞተዋል አልያም በጠና ታመዋል›› የሚሉ ወሬዎች ሲነዙባቸው የሰነበቱት ሙጋቤ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ካላገኘች ድርጅቱን ለቅቃ እንደምትወጣ ዝተዋል፡፡
‹‹የጸጥታው ምክር ቤት እንዲሻሻል ደግመን ደጋግመን ጠይቀናል››ያሉት ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ‹‹አፍሪካዊያን ለውጥና ውጤት በሌለው የድርጅቱ ወሬ ተሰላችተዋል››ብለዋል፡፡
አፍሪካዊያን እውነተኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላት አይደሉም ያሉት ሙጋቤ ‹‹አባላቶቹ ባለነጭ ቆዳዎቹ ብቻ ናቸው፣ አንድ ቀን ግን አፍሪካዊያን ከወሰኑ ከድርጅቱ ጋር ገደል ግቡ ብለው ሊወጡ ይችላሉ››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
‹‹የተባበሩት መንግስታት በህይወት እንዲቆይ ከተፈለገ እኛ አፍሪካዊያን እኩል መብት ያለን አባላቱ መሆን አለብን››በማለት ተናግረዋል፡፡ሙጋቤ ጣታቸውን ወደ ባንኪሙን ቀስረውም ‹‹እርስዎ ጥሩ ሰው ነዎት ነገር ግን እኛ እንዲታገሉልን አናስገድድዎትም፣ ግዳጅዎም ይህ አይደለም ነገር ግን እኛ ስለራሳችን ማንነትና ስብዕና እንደ አፍሪካዊ እንታገላለን››ብለዋል፡፡
ለተባበሩት መንግስታት አድርሱልን በማለትም ሙጋቤ ባንኪ ሙንን ‹‹አፍሪካዊያንም መንፈስ ሳይሆኑ አለም የምትገባቸው ሰዎች መሆናቸውን ንገሩልን››ብለዋቸዋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት በኒውዮርክ መገኘቱን ‹‹ስህተት›› ያሉት ሙጋቤ ዋና ጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባላቸው አገሮች ለምሳሌ በቻይና፣በህንድ ወይም በአፍሪካ አህጉር መገኘት ይገባው ነበር ብለዋል፡፡
አፍሪካዊያንና ሌሎች በኒውዮርክ መገኘታቸውን በመጥቀስም ‹‹ነገር ግን በዚያ ነጫጭ ፊቶችና ፒንክ አፍንጫ ያላቸው ከእኛ ቀጠለው ይገኛሉ ፣እነርሱ ከእኛ ጋር በቁጥር ሲነጻጸሩ ምን ያህል ይሆናሉ?›› በማለት ባንኪሙንን ጠይቀዋል፡፡
ሙጋቤ ባንኪሙንን በንግግራቸው መሐልም ማወደሳቸው አልቀረም ‹‹አፍሪካ ኢቦላን እንድትዋጋ፣ሽብርተኝነትን እንድትከላከልና ሌሎች ቀውሶች ባጋጠሟት ወቅትም ከአፍሪካዊያን ጎን መቆምዎን አንዘነጋም›› ብለዋቸዋል፡፡

Saturday, January 30, 2016

የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል ! January 29, 2016


ኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ ቁጭቱን በቻለው መንገድ ሁሉ ሊገልጸው ሞክሯል። ነገር ግን እስካሁኗ ሰአት ድረስ መገደሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ፣ መዋረዱ አለቆመም። አገዛዙ ለአንድ ቀን በስልጣን ላይ ውሎ እስካደረ ድረስ ይኸው ግፍ ይቀጥላል።
የወልቃይት ህዝብ እኛ እንደፈለግን እንጅ አንተ እንደፈለክ አትኖርም ተብሎ ተፈርዶበት ያለፉትን 25 ዓመታት በስቃይ አሳልፏል። አሁንም እንደገና ” እኛ እናውቅልሃለን እየተባለ” መከራውን እየበላ ነው። በአካባቢው ያንዣበበው የሞት ደመና እጅግ አደገኛ ነው። እየተረጨ ያለው መርዝ ካልቆመ፣ አካባቢው በአጭር ጊዜ የግጭት አውድማ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ዘራፊው የህወሃት ቡድን ግጭትን ከማባበስ በተረፈ ችግሩን የማስቆም ፍላጎት አላሳዬም።

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው!!! አርበኞች ግንቦት 7 =========================


የወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላየ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በጅጉ ማሳስብ ጀምሯል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አሜሪካንን ጨምሮ የወያኔ ለጋሽ ሀገራት የሆኑት ምዕራባውያን ሰሞኑን በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የከፈተውን የዕብሪት ጭፍጨፋ እስራትና አፈና አስመልክቶ ችግሩን በውይይትና በስልጡን መንገድ የፈታ ዘንድ የሚያሳስቡ ግልጽና ባንጻራዊ ደረጃ ሲታዩ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል።
የደረሰውም ጥፋት ተመርምሮ ጥፋተኛ ወገን እንዲጠየቅ የሚጠይቁና ችግሩም በሰላምና በውይይት እንዲፈታ እየጎተጎቱ ይገኛሉ። ባለፉት በርካታ ዐመታት ምዕብራባውያኑ የወያኔ ጉጅሌ ይህንን አቅጣጫ እንዲከተል ተጽዕኖ የመፍጠር አቅማቸውን ተጠቅመው ያደረጉት በቂ ግፊት እንደሌለ ይታወቃል። የአሜሪካ መንግስትና ያውሮፓ ሕብረት አባል ሀገሮች ዘግይተውም ቢሆን ሀገራችን ውስጥ የተካሄደውንና እየተካሔደ ያለውን ጭፍጨፋ ማውገዛቸውና ወደፊትም በዝርዝር ተመርምሮ ተጠያቂው እንዲታወቅ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደ በጎ ጅምር እንመለከተዋለን።
ለሀገራችንና ለህዝባችን እጣ ፋንታ የምንጨነቅና የህዝቡ ጥቃት ያንገፈገፈን የሀገሪቱ ልጆች የችግሩ የመፍትሔ መጀመሪያ ይህ በጉልበቱ ህዝባችን ላይ የተጫነ መንግስት ነኝ ባይ የግፈኞች ጥርቅም በሃይል በሚደረግ ትግል ጭምር መወገድ አለበት ወደሚለው ውሳኔ የደረስነው የሰላም በርና ጭላንጭል ሁሉ በመዘጋቱ እንደሆነ ስንገልጽ ቆይተናል ። ላለፉት ሁለት ወራት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውና ከመቶ ሀምሳ በላይ ወገኖቻችን ያለቁበት ጭፍጨፋ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ተመሳሳይ ግዲያ እስራትና የተቀናቃኝን አድራሻ ደብዛ ማጥፋት እርምጃ የሚያሳየው ይህ ስርዓት የበለጠ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በፍጥነት መወገድ ያለበት መሆኑ ላይ ያለን አቋም ለሁሉም ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ነው። እንደወያኔ ያለ ከህዝብ የተጣላ የፖለቲካ ሀይል የፖለቲካ ጥቅምን የሚያየው ከራሱ ህልውናና ደህንነት አንጻር እንጂ ከህዝቡ ሰላም ብልጽግናና ነጻነት ወይም ከሀገሪቱ የረጅም ጊዜ እጣ ፋንታ አንጻር አይደለም። የወያኔን ገዥዎች የሚያስጨንቃቸው የህዝቡ ኑሮ ሳይሆን የራሳቸው የዝርፊያ ስርዓት ባግባቡ መጠበቅ አለመጠበቁ ነው። ለዚህ ነው ስርዓታቸውን ለመጠበቅ የነጻነት ጥያቄ ኮሽታ በሰሙ ቁጥር የሚባንኑት። ለዚህ ነው በሰላም መብቱን የጠየቃቸውን ሁሉ መደዳውንና በጭካኔ በጥይት የሚረፈርፉትና የተረፋቸውን እንደ እንስሳ ወህኒ በረት ውስጥ የሚያጉሩት።

Thursday, January 28, 2016

ጃዋር መሐመድ ተናገረ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ ማውጣታቸውን አቁመው ሕዝቡን የማስነሳት ሥራ መስራት አለባቸው” አለ | የሚደመጥ ቃለምልልስ

“የአውሮፓ ሕብረት መግለጫ ለኦሮሞ ሕዝብ ጭቆና ምስክርነት የሰጠበት ነው”

“ተቃዋሚዎች ስም ብቻ ደርድረው መቀመጥ ብቻ አይደለም:: ጠጠር መወርወር አለባቸው”

“መሪ ከላይ ቁጭ ብሎ ታች ያለውን ሕዝብ እንዲህ አድርግ እያለ የሚያዝበት የትግል ጊዜ አልፏል”
“ወያኔ ካሁን በኋላ የኦሮሞን ሕዝብ አስከትዬ እሄዳለሁ የሚል ከሆነ ተሳስቷል”
“የጎንደር ለም መሬት ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ወደ ጎጃምም እንዲስፋፋ…”
“ይህን ትግል የሚያንቀሳቅሱት ልጆች ከወያኔ በእውቀትም በብልጠትም የተሻሉ ናቸው”
“ለማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲዎች ልምዳችንን ለማካፈል ዝግጁ ነን”

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ ከሕብር ራድዮ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ጋር ባደረገው ልዩ ቃለምልልስ ተቃዋሚዎች የመግለጫ ጋጋታቸውን አቁመው ህዝቡ ውስጥ ገብተው እንዲሰሩና በኦሮሚያ ክልል ከተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ እንዲማሩ ጠየቀ:: “አሁን ትግሉ ከላይ ቁጭ ብለህ ታች ያለውን ሕዝብ እንዲህ አድርግ እያልክ የምታዝበት ጊዜ አይደለም… ታች ወርዶ መታገልን ይጠይቃል” ያለው ጃዋር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ ማቆሚያ የለውም ገና ይቀጥላል ብሏል:: የጎንደር ለም መሬት ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ እንደምሳሌነት ያነሳው ጀዋር የፖለቲካ ፓርቲዎች መግለጫ ማውጣታቸውን ትተው የጎንደርንም; የጎጃምንም ሌላውንም ሕዝብ ወደ ማስነሳቱ ሥራ መግባት ይኖርባቸዋል ብሏል:: ሙሉ ቃለምልልሱን አዳምጡት::http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50325
 

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው January 23, 2016


def-thumb
የወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላዩ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በእጅጉ ማሳስብ ጀምረዋል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

Thursday, January 21, 2016

ሰበር ዜና። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በሰሞኑ የሀገራችን ሁኔታዎች ላይ በርካታ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን አወጣ። January 21, 2016 ሰበር ዜና። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በሰሞኑ የሀገራችን ሁኔታዎች ላይ በርካታ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን አወጣ። በዚህም መንግስት በተገደሉት 140 ዜጎች ዙርያ ገለልተኛ አጥኚ ቡድን እንዲያቋቁምና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል። በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የተነተነውን የፓርላማውን መግለጫ ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ።

ሰበር ዜና። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በሰሞኑ የሀገራችን ሁኔታዎች ላይ በርካታ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን አወጣ።
January 21, 2016
ሰበር ዜና። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በሰሞኑ የሀገራችን ሁኔታዎች ላይ በርካታ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን አወጣ። በዚህም መንግስት በተገደሉት 140 ዜጎች ዙርያ ገለልተኛ አጥኚ ቡድን እንዲያቋቁምና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል። በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የተነተነውን የፓርላማውን መግለጫ ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ።
having regard to the press release on the meeting between the High Representative/Vice-President Federica Mogherini and the Minister of Foreign Affairs of the Federal Republic of Ethiopia, Tedros Adhanom, 13 January 2016
– having regard to the statement by the EEAS Spokesperson on elections in Ethiopia, 27 May 2015
– having regard to the press release of the UN Office of the High Commissioner for Human Rights, 10 July 2015
– having regard to press briefing note of the UN Office of the High Commissioner for Human Rights, 10 July 2015

– having regard to the universal Declaration of Human Rights
– having regard to the African Union Charter of Human and Peoples’ Rights

– having regard to the UN the International Covenant on Civil and Political Rights,
– having regard to Rule 123(2) its Rules of procedure
A.whereas over the past two months , Ethiopia’s largest region, Oromia, has been hit by a wave of mass protests over the expansion of the municipal boundary of the capital, Addis Ababa which has posed risks for farmers eviction from their land;

B.whereas security forces used excessive lethal force and killed at least 140 protesters and injured many more, in what may be the biggest crisis to hit Ethiopia since the 2005 election violence;
C.whereas on the 14 January 2016 the government decided to cancel the disputed large scale urban development plan ; whereas if implemented, the plan will expand the city’s boundary by 20 times its current size; whereas Addis Ababa’s enlargement has already displaced millions of Oromo farmers and trapped them in poverty;

ማስተር ፕላኑን ማን አጸደቀው? ማስተር ፕላኑንስ ኦፒዲኦ የማስቆም ስልጣን አለውን? | 5 ጥያቄዎች ለኦህዴድ አባላት

ማስተር ፕላኑን ማን አጸደቀው? ማስተር ፕላኑንስ ኦፒዲኦ የማስቆም ስልጣን አለውን? | 5 ጥያቄዎች ለኦህዴድ አባላት

ማስተር ፕላኑን ማን አጸደቀው? ማስተር ፕላኑንስ ኦፒዲኦ የማስቆም ስልጣን አለውን? | 5 ጥያቄዎች ለኦህዴድ አባላት

ከ- መርጋ ደጀኔ (ኖርዌይ )
ሲጀመር የአዲስ አበባ ማስተር ፕላኑን ያጸደቀው ወያኔ ነው፡ የማስተር ፕላኑንም አፈጻጸም የሚተገብረው በወያኔ ቁልፍ ሰዎች ነው፡ ሟች ጠቅላይ ሚኒስቴር የማስተር ፕላን አሰራር እንዲሁም በአዲስ አበባ የመሬት ቅርምት ውስጥ ተጠቃሚ የሚሆኑት ማን እንደሆኑ እና ማን በአስፈጻሚነት እንደሚሰሩ ቀድመው የዘረጉት መስመር ሲሆን የሟች ጠቅላይ ሚኒስቴር ራዕይ አስፈጻሚዎች ዛሬም በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።
ODDO 4




አዲስ አበባ ሁሌም በህብረት የሚኖሩባት ማንም ከማንም የማይለይባት ኢትዮጵያኖች በአጠቃላይ በአንድነት የሚኖሩባት የአንድነት ተምሳሌነት የነበረች ሲሆን በማህበራዊ ህይወት እንደ እድር፤ እቁብ የመሳሰሉትን በመጠቀም ህብረተሰቡ በደንብ የተዋወቀ እና የአንድነት እና የፍቅር ተምሳሌኔት የሆነች ከተማ ነበረች። ይህችን ከተማ አብረው ተዋውቀው ተሳስበው ህብረተሰቡ በሙሉ በፍቅር ይኖርባት የነበረውን ከተማ በማስተር ፕላን ሰበብ በማፍረስ የጀመሩ የህብረተሰቡን ቤትና ንብረት ብቻ ሳይሆን አንድነቱን ፍቅሩን ኢትዮጵያዊ ጽናቱን ጭምር እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባናል።
መቼስ ከተማ መልማትንም ሆነ ማደግን የሚጠላ ህብረተሰብ አለ ለማለት ባያስደፍርም ልማቱ እና እድገቱ ለማን ነው?የሚለው ጥያቄ ሊመለስ ብቻ ሳይሆን ተመልሶ መሄድ ያለበት ጉዳይ ነው።

UN experts urge Ethiopia to halt violent crackdown on Oromia protesters, ensure accountability for abuses


GENEVA (21 January 2016) – A group of United Nations human rights experts* today called on the Ethiopian authorities to end the ongoing crackdown on peaceful protests by the country’s security forces, who have reportedly killed more than 140 demonstrators and arrested scores more in the past nine weeks.
united nations human rights
“The sheer number of people killed and arrested suggests that the Government of Ethiopia views the citizens as a hindrance, rather than a partner,” the independent experts said, while also expressing deep concern about allegations of enforced disappearances of several protesters.
The current wave of protests began in mid-November, in opposition to the Government’s ‘Addis Ababa Integrated Development Master Plan’ to expand the capital’s municipal boundary. The ‘Master Plan’ could reportedly lead to mass evictions and the seizure of agricultural land in the Oromia region, as well as extensive deforestation.

አቶ ኃይለ ማርያም ምን ነካካቸው?

– ከተማ ዋቅጅራ
ጠቅላይ ሚንስትር ማለት፡- የቃሉ ትርጉም የሚንስትሮች ሁሉ የበላይ፣ ሁሉንም ሚንስትር የሚያዝ፣ ሁሉንም ሚንስትሮች ጠቅልሎ የሚመራ የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። እንደ ኢትዮጵያ፣ እንግሊዝ፣ ጃፓን የመሳሰሉት አገሮች የአገር መሪነት ድርሻ የጠቅላ ሚንስትሩ ነው። የአለማችን አብዛኛው አገራት የሚመሩት በፕሬዝዳንት ሲሆን ኢትዮጵያ ግን የምትመራው በጠቅላይ ሚንስትር ነው። በጠቅላይ ሚንስትር የሚመሩት አገሮች ሁሉ የሚመረጡት በህዝ የሚሾሙትም በህዝብ የሚያገለግሉትም የመረጣቸውን ህዝብ ስለሆነ ባለሙሉ ስልጣን ባለቤት ናቸው። በዚህ የተነሳ ሃገራቸውን የሚያስከብር ስራ ይሰራሉ ህዝባቸውንም የሚጠቅም ስራ ይሰራሉ። ከህዝባቸውን የተሰወረ ነገር አያደርጉም ህዝባቸውንም የሚጎዳ እና የሚያሳፍር ድርጊትም አይፈጽሙም። ስለዚህ ህዝቡ በመሪዎቻቸው ደስተኛ ነው።ኢትዮጵያ ግን እንደ እድል ሆኖ እንደዛ አይደለም። መሪው የሚመረጠው በህዝብ ሳይሆን በህውአት ሰዎች ነው። መሪ ተብዬዎች አገልግሎታቸውን የሚሰጡት ለኢትዮጵያን ህዝብ ሳይሆን ለመረጣቸው ፓርቲ ብቻ ነው። በዚህ ምክንያት ህዝባችን ቢገደል፣ ቢታሰር፣ ቢንገላታ፣ ቢራብ፣ ቢጠማ፣ የትኛውም አይነት መከራ ቢደርስበት የመረጣቸው ፓርቲን የማይነካ ከሆነ እንደ አገር መሪ ትንፍሽ ማለት አይችሉም። የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ተደፍሮ አገር ተቆርሶ ለበአድ ሲሰጥ  እንደ አገር መሪ አንድ ስንዝር የአገሬ መሬት አይሰጥም ብለው ለአገር እና ለህዝብ የቆሙ መሆናቸውን የሚያሳዩበት ንግግር ማድረግ አልቻሉም።
አጋዚ ፌድራል የተባሉ የህውአት ወታደሮች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ትዕዛዝ ውጪ ተልከው ህዝባችንን በዘግናኝ ሁኔታ  በጥይት እየመቱ ሲገድሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር በተቃውሞ ሲናወጥ እንደ አገር መሪነቶ መናገር ሆነ ለሚወሰደው እርምጃ ሙሉውን ኃላፊነት መውሰድ የሚገባቸው አቶ ኃይለ ማርያም ሆነው ሳለ በተገላቢጦሽ መግለጫ የሚሰጡትም ሆኑ መግለጫ መስጠት ያለባቸውን አካል የሚመርጡት የህውአት ሰዎች መሆናቸውን ስናውቅ ቢያሳፍረን እና ቢያሳምመንም አቶ ኃይለ ማርያምን ምን እንበላቸው? እስቲ ስም አውጡላቸው የአገር መሪ ወይንስ የአገር አማራሪ?።

Wednesday, January 20, 2016

የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝና በመላው ኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ አስመልክቶ ነገ ጠንከር ያለ አቋም ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ለውይይት የሚቀርበው ሞሽን ለኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ለልማት ተብሎ የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና ለማህበረሰቦች መፈናቀል አስተዋፅኦ ያደረገ እንዳልሆነ ቁጥጥር እንዲደረግበትም ይጠራል።

MOTION FOR A RESOLUTION: European Parliament resolution on the situation in EthiopiaThe European Parliament,

–   having regard its previous resolutions on the situation in Ethiopia
–   having regard to the statement by the EEAS spokesperson on recent clashes in Ethiopia, 23 December 20150
–   having regard to the joint statement by Federica Mogherini, High Representative for Foreign Affairs and Security Policy/Vice-President of the European Commission, and Minister of Foreign Affairs Tedros Adhanom of the Federal Republic of Ethiopia, 20 October 2015
–   having regard to the press release on the meeting between the High Representative/Vice-President Federica Mogherini and the Minister of Foreign Affairs of the Federal Republic of Ethiopia, Tedros Adhanom, 13 January 2016
–   having regard to the statement by the EEAS Spokesperson on elections in Ethiopia, 27 May 2015
–   having regard to the press release of the UN Office of the High Commissioner for Human Rights, 10 July 2015
–   having regard to press briefing note of the UN Office of the High Commissioner for Human Rights, 10 July 2015

Tuesday, January 19, 2016

Demhit Amharic Special program 4 05 2008

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ!

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ!
በገንዘብ፣በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም ይዘናል።
ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ! አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምቷል። ኢትዮጵያ የተዳከመች ሲመስላቸው ጠላቶቿ ስነሱባት መስማት አዲስ ነገር አይደለም።
አዲስ ነገር የሚሆነው በቤተ መንግስቷ በኢትዮጵያ ስም መንግስት ነኝ የሚሉ ስብስቦች የኢትዮጵያን ጥቅም ከባዕዳን ጋር ሲዶልቱ፣ሲሸጡ እና ሲያስማሙ መመልከት ነው።በገንዘብ፣ በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።
ይህ ሕሊናን የሚያደማ ብቻ ሳይሆን የመኖር እና ያለመኖር ህልውና ጉዳይ ነው።''ዳሩ ሲነካ መሃሉ ዳር ይሆናል'' የሚለው አባባል እዚህ ላይ ማሰቡ ተገቢ ነው።ይህ ሥራ በመንግሥትነት እራሳቸውን የሾሙ ስብስቦች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ልክ የት ድረስ እንደሚሄድ ብቻ ሳይሆን የከሃዲነት ደረጃቸው እና ህዝብን የመናቃቸው መጠን ምን ያክል እንደሆነ ማሳያ ነው።
አቶ ኃይለማርያም በድንበሩ አካባቢ የሚያርሱ ገበሬ ኢትዮጵያውያንን የህዝብ ተወካይ ነኝ ባሉ ምክር ቤት ስም ''ሽፍቶች'' እያሉ የተሳደቡትን ስድብ የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እብራሂም ጋንዱር ለአልጀዝራ በሰጡት መግለጫ ላይም ደግመውታል።
ኢትዮጵያውያንን እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በስልጣን ላይ የተቀመጠው የኢትዮጵያ መንግስትም እንደሚገልላቸው ሲገልጡ ''ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሱዳን ግዛት ላይ የሰፈሩትን ሽፍቶች (gangs) በመግታት የድንበር ማካለሉን ሥራ በአንድነት እየሰሩ ነው'' ነበር ያሉት። አሁን የንግግር እና የወሬ ጊዜ አይደለም። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በሙሉ መለየት አለበት።ኢትዮጵያን ከሸጡ ጋር ነህ ወይንስ አይደለህም? ጥያቄው ይህ ነው።ኢትዮጵያን የከዳ በሙሉ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት።

Monday, January 18, 2016

የሱዳን መሬት በኢትዮጵያ መያዙን የኢትዮጵያ መንግስት አምኖአል” ሲሉ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ


ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ጋንዱር ለአልጀዚራ እንደተናገሩት "ኢትዮጵያ አልፋሽጋ የሚባለው ግዛት የሱዳን መሆኑን እንደምትቀበልና ለማስረክብ መቁረጧን" ተናገሩ። ለሱዳን ይሰጣል የተባለው መሬት 250 ካሬ ኪሎሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ ለም የሆነ መሬትና በርካታ የውሃ ተፋሰሶች ያሉት ነው። የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ አርሶአደሮች መሬቱን ሰጥቷቸው ሲያርሱት ነበር ያሉት ባለስልጣኑ፣በዚህ አመት ውስጥ መሬቱን ኢትዮጵያ ለሱዳን ልታስረክብ መሆኑን ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ንግግር፣ አቶ ሃይልማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሰጡትን መግለጫ የሚያጠናክር ነው። አቶ ሃይለማርያም የኢትዮጵያ ባለሃብቶችና አርሶአደሮች ወደ ሱዳን ገብተው እያረሱ መሆኑንና የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳንን መንግስት ለምኖ እስካሁን በቦታው ላይ እንዲቆዩ ማድረጉን aተናግረው ነበር። የሱዳን መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰጡት መግለጫ ከኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ጋር መመሳሰሉ የተጠቀሰው መሬት ለሱዳን እንደሚሰጥ ማረጋገጫ ነው። በድንበሩ አካባቢ ያሉ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ግን መሬቱ የኢትዮጵያ መሆኑን ይናገራሉ። የኢህአዴግ መንግስት መሬቱ የሱዳን መሆኑን አምኖ ከተቀበለ ቀሪው ነገር አለማቀፋዊ ህጋዊነትን ማላበስ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ ሁለቱም መንግስታት ተስማምተው ስምምነታቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከገለጡ፣ መሬቱን መልሶ ለማግኘት ጉዳዩን ውስብስብ ሊያደርገው ይችላል። የመንግስት ቃለአቀባይ ጌታቸው ረዳ እና ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የድንበር ጉዳይን ለማየት የተቋቋመ ኮሚቴ እንደሌለ፣ መሬት ለመስጠት ምንም ዝግጅት እንደሌለ ሲገልጹ ቆይተዋል። ይሁን እንጅ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሪዎች ደረጃ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩ እየታየ መሆኑን ገልጸዋል። የኮሚቴው ሰብሳቢ አብደላ አል ሳድቅ ኮሚቴው ስራውን ያለምንም ችግር እያከናወነ መሆኑን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ላለፉት ሁለት ወራት የደህንነት መስሪያ ቤት (ኢንሳ) መሬቱን የአየር ላይ ፎቶ ሲያነሳ ከርሟል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄ የደህንነት መስሪያ ቤቱ "የመሬቱ ልኬቱ የሚካሄደው ለልማት የሚውለውን መሬት ለመለየት ነው" የሚል መልስ ሲሰጥ ቆይቷል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ መሬቱን የማስረከብ ሃላፊነት መውሰዱን ምንጮች ገልጸዋል።

በደሃው ወታደር ደም የአሜሪካ ጥቅም የወያኔ ስልጣን ሊጠበቅ ነው ? እስከ መቼ ?

Barak Obama of The White House says no to US ground forces to combat Shabaab: “We don’t send our marines in to do the fighting. The Ethiopians are tough fighters.”በሶማሊያ ምድር በአልሸባብ ለተገደሉ ለተማረኩ ወታደሮች ቤተሰቦች እንኳን ካሳ ሊከፈል የጡረታ መብት አልተከበረላቸውም::የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን እንዳይጎናጸፍ አሜኬላ እሾህ ከሆኑት አንዱ የአሜሪካ መንግስት እና መሪዎች ናቸው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
…… አሉ እርሳቸው እርግጥ አቋማቸው ያው ነው የውጪ ጉዳይ ፖሊሲያቸውም አልተለወጠም::ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ደሆችን እና መንግስታቶችን አስመልክቶ የተናገሩት እንዳለ ነው::የአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም እስከተከበረ ድረስ በማንኛውም የአምባገነን አገዛዝ ሂደት ውስጥ እጃቸውን እሳቸው ይሁኑ አገራቸው እንደማያስገቡ….ስለምርጫ እና ዲሞክራሲያዊ ተግባራት ይልቅ የደሆች መሰረታዊ ፍላጎት መጠበቅ አለበት ከዛ በኋላ ህዝቡ ራሱ ነጻነቱን መፈለግ ይችላል እንጂ አሜሪካ … ምናምን .. ጣልቃ አትገባም .. ይህ የኦባማ ፕሪንሲፕል አሁንም ጽኑ እንደሆነ ከስልጣን ሊሰናበቱ ነው::
ታዲያ የአሜሪካ ጥቅም እስከተከበረ ድረስ የኢትዮጵያ ደሃ ወታደር በሶማሊያ ምድር ቢያልቅ ምን አገባቸው::ወታደር ማለት የአንድ ሃገር ሉአላዊነት አካል ነው::ይህን ደሞ ኦባማም ያምናሉ::ስለዚህም ነው የአሜሪካ ወታደሮች ወደሶማሊያ አይላኩም የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ተልከው ያልቃሉ:: የኢትዮጵያ ወታደሮች ምርጥ ተዋጊዎች ናቸው::የአሜሪካ ምርጥ ተዋጊዎች አይደሉም? ማነው በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠነው? በደሃው የኢትዮጵያ ወታደር ደም የአሜሪካ ጥቅም ማስጠበቅ ሌላ ሕዝባዊ ጥያቄ እንዲነሳ በሩን ያንኳኳል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ የደሃው ወታደር ደም በሽብርተኝነት መዋጋት ሰበብ ለአሜሪካ ጥቅም የተገበሩ ወታደሮች ጎን ለጎን የወያኔ አምባገነን ሌቦች ስልጣን እንዲረዝም ሌላ አስታውጾ አድርጓል::የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን እንዳይጎናጸፍ አሜኬላ እሾህ ከሆኑት አንዱ የአሜሪካ መንግስት እና መሪዎች ናቸው::ይህንን ደሞ በጋራ ልንታገለው እና ልናሸንፈው የሚገባ የኛ የኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳይ ነው::የአሜሪካ መንግስት ብሄራዊ ጥቅሙ እስካልተነካ ድረስ ወያኔ 100 አመት ስልጣን ላይ ቆይቶ ቢያስር ቢገድል ቢያሳድድ አይመለከተውም::በተዘዋዋሪ ደሞ እንደ ኦባማ አይነቱ ብሄራዊ ጥቅሙን ለማስከበር የሚሄድበት መንገድ የአምባገነኖችን እድሜ ማራዘሚያ የፖለቲካ ስልት ነው::
የደሃው ወታደር ደም በሶማሊያ ምድር በአልሽባብ ጥይቶች ሲዝራ ከአሜሪካ የሚመጣው ዶላር ኪሳቸውን የሚያደልበው ይወያኔ ባልስልጣናትን ነው:;በሶማሊያ ምድር በአልሸባብ ለተገደሉ ለተማረኩ ወታደሮች ቤተሰቦች እንኳን ካሳ ሊከፈል የጡረታ መብት አልተከበረላቸውም::ከዚሁ ዘመቻ ጋር በተያያዘ እጅግ ከፍትኛ ችግር ውስጥ የገቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የደሃው ወታደር ቤተሰቦች ቤት ይቁጠረው::ስለዚህ ወታደሮች ይሁን ቤተሰቦቻቸው ይህንን የአሜሪካንን ጥቅም ለማስከበር ለኢትዮጵያ ፋይዳ አልባ ለሆነው ጦርነት ራሳቸውን አስልፈው ከመስጠታቸው በፊት ሊያስቡበት እና ሊመክሩበት ይገባል::አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ከፈለገች ወታደሮቿን ታዝምት::በደሃው ወታደር ደም የአሜሪካ ጥቅም የወያኔ ስልጣን ሊጠበቅ ነው? እስከመቼ ? በጋራ ቆመን በመቻቻል መንፈስ እየታገልን ነጻነታችንን እናረጋግጥ !!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬http://www.mereja.com/amharic/462106

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል፣ አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ፣ አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ

Hibir Radio Coverየህብር ሬዲዮ ጥር 8 ቀን 2008 ፕሮግራም
<...አዲሱ የፈጠራ ፊልምን ዶክመንተሪ አልለውም ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ብለው በከንቱ የደከሙበት ነው …የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያን ከሃያ አምስት ዓመቱ የወያኔ ስልጣን በፊት ለረጅም ዘመን አብሮ የኖረ ነው። በየጊዜው በህወሃት ማሸበሪያ የውሸት ፊልም የሚጋጭ አይደለም…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ <<የማንቂያ ደውል>> ስለተሰኘው የአገዛዙ ዶክመንተሪ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
በሎስ አንጀለስ የጥምቀት በዓል አከባበር(ቆይታ ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር)

በዘንድሮ ታክስ አሰራርና የሕክምናና ለበጎ አድራጎት ወጪ የሆኑትን በተመለከተ ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች (ውይይት ከአትላንታ ከአቶ ተካ ከለለ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር ሙሉውን ያዳምጡት)
<...ከ140 በላይ ንጹሃን ከተገደሉና በርካቶች ከታሰሩ፣ከቆሰሉ ፣በርካቶች ከተደበደቡ በሁዋላ ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ የሚለውን ቀልድ ነው። ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ማለት ያለበት ሕጉን ያወጣው የኦሮሚያ ም/ቤት ነው። የኦሮሚያ ክልል አሁንም በወታደራዊ እዝ ስር ነው ።አ መቼ ቀረ?ሕዝቡ ተቃውሞውን ቀጠለው በቂ መልስ ስላላገኘ ነው...ምዕራባውያን ተገቢውን ተጽዕኖ እየፈጠሩ አይደለም። ገዢው ፓርቲ አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ እየመራት መሆኑን ያውቃሉ ችግሩ ያው ጠመንጃ ከያዘው ጎን የመለጠፋቸው ነው። አሁን አገሪቱ መስቀለኛ ሁኔታ ላይ ነች። ሰራዊቱም ቢሆን… > ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦህዴድን ማስተር ፕላኑ ቀርቷልና የቀጠለውን ተቃውሞ በተመለከተ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከአገር ቤት ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

Sunday, January 17, 2016

ሰበር ዜና – በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኝታ እየተቃጠለ ነው


ሰበር ዜና – በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኝታ እየተቃጠለ ነው
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የቀጠለው ሕዝባዊ ቁጣ እየተባባሰ በመጣበት ባሁኑ ወቅት በዛሬው ዕለት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኝታ ቤት እየተቃጠለ መሆኑ ተሰማ::
ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የእሳት አደጋው አንዱን የተማሪዎች ህንፃ እያወደመው ይገኛል::
እሳት አደጋውን ያስነሳው ምክንያት እና ምን እንዳስነሳው የተረጋገጠ ነገር የለም:: ሆኖም ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰበች ትገኛለች::

Home » ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም... » “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ) “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ) ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል።http://ecadforum.com/Amharic/archives/16098/
Ethiopian Border Affairs Committee
በዚህ ወቅት የፈለቀችው ይህች ጦማር፤ ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ድንበር የተሸከመችው ሀሳብ የራሴ ፈጠራ አይደለም። በሱባዔ፣ በህልም የተከሰተልኝ አይደለም።አልበቃሁምና መንፈስ ቅዱስ ገለጾልኝም አይደለም። የቅኔ ችሎታቸውን ከመንደር ቧልትና ነገረ ዘርቅ ያላቀቁ ሊቃውንት የህዝቡን አሉታ እየተመለከቱ፤ በሰረዙ ቅኔያቸው ሲዘርፉበት የተማርኩት ነው። የትርጓሜ መምህራንም ባንድምታ ትርጉማቸው የሚያመሠጥሩት፤ ለእለታዊ ጥቅም ተልእኳቸውን ያልሸጡ ቀሳውስትም በጸሎታቸው ሲገልጹት የሰማሁትና “ድንበር ሲፈርስ መሐሉ ዳር ይሆናል፤ የዛፍ ጫፉ ሲጨፈጨፍ ግንዱ ጫፍ ይሆናል”እያሉ የመንደር አዛውንትም ሲናገሩ የሰማሁትን ነው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]1 ድንበር “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ nigatuasteraye@gmail.com ጥር ፳፻፰ ዓ.ም. ማሳሰቢያ ስለኢትዮጵያ ድንበር መፍረስ፤ መገሰስና መጠገን በተደረጉበት ዘመናት ሁሉ የነበረች አሁንም ታፍና በመታዘብ ላይ ያለች፤ ወደፊትም የምትኖር ይህች ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤ አሁን ህዝቧ ስለሚነጋገርበት ስለ ድንበር ምን ትላለች? የሚለውን ለመዳሰስ ይህችን ጦማር ሳዘጋጅ በውስጧ የተሸከመቻቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ አቅርቤያቸዋለሁ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘረውን አፈና ለመከላከል የጠቀስኳቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ በማቅረቤ (ግእዙን ግን ትርጉሜዋለሁ) ይቅርታ በመጠየቅ ያጎደልኩትን እየሞላችሁ፤ የተሳሳትኩትን እያረማችሁ ታነቧት ዘንድ በታላቅ ትህትና አቀረብኩላችሁ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራዲዮ የብአዴን ባለስልጣናት የወጣቶች ሊግ እያሉ ያደራጇቸውን ወጣቶች በስብሰባ ጠምደዋቸው ዋሉ፡፡ ———————————————————————



Amdemariam Ezra's photo.
Amdemariam Ezra's photo.

አገዛዙ በአራቱም የአገሪቱ አቅጣጫ የተነሳበትን ህዝባዊ ቅዋሜ እና አርበኞች ግንቦት 7 እያካሄደ ያለውን ሁለገብ ትግል መቋቋም ተስኖት ከላይ ከታች እየረገጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ጥር 5/2008 ዓ.ም ባህርዳር ከተማ ላይ ከዘጠኙ ክፍለ-ከተመ የተወጣጡ የወጣቶች ሊግ እያሉ ያደራጇቸውን ወጣቶች የብአዴን ባለስልጣናት በስብሰባ በመጥመድ፡-
‹‹በከተማችን የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት በመሰግሰግ በራሪ ወረቀ ቶችን በገፍ እየበተኑ ነው!!እናም ህዝቡን ከእኛ ለይተውታል!! በመሆኑም ይህ ሁሉ ሲሆን እናተ ምን እየሰራቹህ ነው?››እያሉ ያፋጠጡባቸው፣የገላመጡጧቸው መሆኑን ታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ወጣቶቹ የባለ-ስልጣናቱን ቁጣ የተሞላበት ጥያቄ፡- ‹‹ታዲያ ህዝቡ ከእኛ ከተለየ እንዴት አድርገን በግድ ቅረበን እንለዋለን? ደግሞስ እናተ ያል ቻላቹህትን እዴት እኛ ማሳመን እንችላል? ለምን የራሳቹህን ችግር ወደ እኛ ታላካላቹህ?›› በማለት ለባለስልጣናቱ ጥያቄ ጥያቂያዊ መልስ ሰጥተዋል፡፡
በአጠቃላይ ስብሰባው በጫጫታ እና በሁከታ ያላንዳች ስምነት መጠናቀቁን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራዲዮ ዜና ምንጮች ከቦታው ዘግበዋል፡፡

Friday, January 15, 2016

ሂውማን ራይትስ ወች “መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መሰረዙ ለተቃዋሚዎች ትልቅ ድል ቢሆንም ውሳኔው ዘግይቷል” አለ


ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሂውማን ራይትስ ወቹ ፍሊክስ ሆርን ፣ ደም አፋሳሽ ከሆነው የ9 ወራት ተቃውሞ በሁዋላ መንግስት ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመሰረዝ መልስ ቢሰጥም፣ ኦሮምያን ለማረጋጋት ግን የዘገየ ውሳኔ ነው ብሎአል።
መንግስት ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ መልስ መስጠቱ ያልተለመደ ነው የሚለው ሆርን፣ ለተቃዋሚዎች ደግሞ ትልቅ ድል ነው መሆኑን ገልጿል።
በመጀመሪያ ተቃውሞው ስለ አዲስ አበባ መስፋፋት ነበር፣ይሁን እንጅ መንግስት ዜጎችን በስፋት ሲያስር፣ ሲገድልና ሌሎችን ጭካኔ የተሞላባቸው እርምጃዎች ሲወስድ፣ ተቃውሞው ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አልፎ ሌሎችም ጥያቄዎች ማካተቱን ገልጸዋል።ምንም እንኳ የተወሰኑ ግጭቶች ቢኖሩም፣ አብዛኞቹ ተቃውሞዎች ሰላማዊ ናቸው።መንግስት ጭካኔ የተሞባለት እርምጃ መውሰዱ ተቃዋሚዎቹ ታሪካዊ ብሶቶችን ሁሉ እንዲያነሱ እንዳደረጋቸው ሆርን ገልጸዋል።
ምንም እንኳ መንግስት ማስተር ፕላኑን መተውን ቢያስታውቅም ፣ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ግን አልቀየረም። በእየለቱ ሰዎችን መግደልና ማሰሩ፣ በተለይም በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ቀጥሎአል።
ብዙዎቹ ተቃዋሚዎች መንግስት እቅዱን ይሰርዘዋል የሚል እምነት የላቸውም። ነገር ግን እቅዱ ኖረ አልኖረ መንግስት፣ፖሊሲውን እስካልለወጠ ድረስ አርሶአደሮቹን ማፈናቀሉን አያቆምም። መንግስት የአካባቢውን ሰዎች እንደ ልማት አጋር አድረጎ በመውሰድ ካላማከረ፣ የመሬት ባለቤትነታቸውን መብት ካልጠበቀና ጸረ ልማት የሚለውን አመለካከቱን ካልቀየረ እንዲህ አይነት ተቃውሞዎች ሊቀጥል እንደሚችል ሆርን በጽፋቻው አመልክተዋል።
መንግስት ለጊዜው ሁኔታውን ለማረጋጋት ከፈለገ የታሰሩትን በአስቸኳይ መልቀቅ አለበት የሚሉት ሆርን፣ የሚታመን አጣሪ ኮሚቴ በማቋቋም የደረሰውን አደጋ መመርመር አለበት። በኦሮሞ ህዝብ ላይ እስከዛሬ የደረሰውን የመብት ጥሰት በመመርምር መልስ መስጠት እንዳለበትም ሆርን አስታውሰዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎችን ዒላማ ያደረጉ የቦምብ ፍንዳታዎች በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መካሄዳቸው በመንግስት የተቀነባበሩ ናቸው የሚለውን ጥርጣሬ እያጎላው መጥቷል።
በሚያዚያ 2006 ዓ.ም የማስተር ፕላኑን ዕቅድ በመቃወም በ11 በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲዎች ተቃውሞ ተቀስቀሶ ከ20 በላይ ተማሪዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ በወቅቱ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ በቴሌቪዥን እየተመለከቱ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የተወረወረ ቦምብ ፈንደቶ አንድ ተማሪ ወዲያውኑ ሲሞት 70 ያህል ተማሪዎችን ቆስለው ነበር።
በቅርቡ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተ የቦምብ ፍንዳታ ሁለት ተማሪዎች ሲሞቱ ስድስት ያህሉ መቁሰላቸው የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ በያዝነው ወር መጀመሪያ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ምሽት ላይ በተወረወረ ቦምብ ከ30 ያላነሱ ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል።
መንግስት ሁሉንም ፍንዳታዎች ጸረ ሰላም ሃይሎች አደረሱት የሚል ተደጋጋሚ መግለጫ ቢሰጥም ፣እስከዛሬ አንድም ሰው አለመያዙ ጥቃቱ በመንግስት የደህንነት ሃይሎች የተቀነባበረ ሳይሆን አይቀርም የሚለውን የብዙዎች ግምት አጠናክሮታል።
ተቃውሞ በበረታባቸው ዩኒቨርሲዎች እንዲህ ኣይነት ጥቃት በመንግስት ሃይሎች ከተሰነዘረ በሃላ እንደገና ራሱ መንግስት ሰላምና መረጋጋት አምጪ ሆኖ በመቅረብ ተማሪዎች በፍርሃት ዝም እንዲሉ የሚጠቀምበት ስልት ነው የሚል
ግምት እንዳላቸው ዘጋቢያችን የተማሪዎችን አስተያየት አሰባስቦ የላከው ዘገባ ያመለክታል።

በኦሮምያ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ በምስራቅ ሃረርጌ በበደኖና በአንዳንድ አካባቢዎች ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በበደኖ በነበረው የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ተማሪዎች ተቃውሞ፣ በርካታ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደብድበዋል። ከ30 በላይ ተማሪዎች መታሰራቸውን አንድ የአይን እማኝ ገልጿል።

ESAT Tamagn Guest With Alebachewu Dessalegn Part 3 of 3 Dec 2015

Ethiopia: Al Jazeera covers the arrest of opposition leader Bekele Gerba in Ethiopia | Video

Ethiopia: Al Jazeera covers the arrest of opposition leader Bekele Gerba in Ethiopia | Video

Thursday, January 14, 2016

ESAT Special Documentary Oromo protests Jan Part 1 2016 ED

በዘረኞች ከሚደርስብን ለጆሮ ከሚቀፍ ሰቆቃ ለመላቀቅ የሁላችንንም ተሳትፎ ይጠይቃል

በዘረኞች ከሚደርስብን ለጆሮ ከሚቀፍ ሰቆቃ ለመላቀቅ የሁላችንንም ተሳትፎ ይጠይቃል
በመላው ሃገራችን ስብዕናችንን አዋርዶ፤ ህይወታችንን ዋጋቢስ አድርጎ በባርነት እየገዛን፡ ለመናገር እንኳ የሚሰቀጥጥ ሰቆቃ በመላው ህዝባችን ላይ የሚፈጽመውን የአፓርታይድ ስርዓት
ከጫንቃችን አሽቀንጥሮ ለመጣልና ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ የሁላችንንም (የሁሉንም ክልሎች፡ የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮችን) ተሳትፎ ይጠይቃል።

እኛ የ ኢትዮጵያ ህዝብ ሁላችንም በጋራ ተባብረን ለዘመናት አንቆ ከያዘን በጠመንጃና በሃይል ከመገዛት አረንቋ መውጣት አለብን፡ አብዛኛዎቹ የአፓርታይድ ህወሃት መሪዎች ህዝባቸውን፤ አገራቸውን፤ አህጉሯን ጭምር አዋርደዋል ለውድቀት ዳርገዋል። አይወድቁ አወዳደቅ ወድቀወዋል፤ የስንቱን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሰላምና በተስፋ የመኖር ህልሙን አጨልመዋል።
ይቺን እንደ ሃገር ያለመቀጠልና የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባትን ሃገራችንን ለመታደግ መዋቅራዊ ቀውስንና ሰብአዊ ቀውስን ተዛምዶ በጥልቀት መረዳት ያሻል። መዋቅራዊ ቀውስ ኢፍትሃዊ በሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚ የሚፈጠር ሲሆን ሰብአዊ ቀውስ ደግሞ ለማንነት ቀውስ፤ ከቤተሰቦቻችን፤ ከማህበረሰባችንና ከብሄራችን ባህርይ እና የሞራል ጥንካሬ ጉድለት የሚመጣ ነው: እኛ ኢትዮጵያውያን ልንክደው የማንችለው ሃቅ ትንሿን ነገር እንኳ እርስ በርስ መከባበር፡ ለሌሎች ዋጋ መስጠት እንኳ ተስኖናል።
በአኝዋክ አንድ ባህላዊ አባባል አለ፡ "ወደ ኮረብታ በመውጣት ምርጥ መሬት አናገኝም" ወደ ኮረብታ ሲወጣ ከፍታ ቦታ ከመደረሱ በፊት በሸለቆና በሜዳ መጓዝን ይጠይቃል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከፍታ መሬት ወይም ገዢ መሬት ያስፈልገናል፡ ይህን ለማግኘት ደግሞ ሩቅ መጓዝ ወይም ሩቅ ቦታ ፍለጋ መሄድ እይጠበቅብንም።

በረሃብ ምክንያት በሰሜን ወሎ ወረዳዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች ቀያቸውን እየለቀቁ ወደ ባህርዳር በመፍለስ ላይ ናቸው



ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢያቸው በተከሰተው ድርቅ የሚበሉትና የሚቀምሱት እንዳጡ የሚናገሩት ስደተኞች፣ ሰሞኑን ባህርዳር ገብተዋል፡፡ በየመንገዱ በመለመን የእለት ምግባቸውን ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን በፎቶ አስደግፎ ዘጋቢያችን የላከው መረጃ ያሳያል፡፡ የክልሉ መንግስት ምንም አይነት እገዛም አላደረገላቸውም፣ ማረፊያ ቦታም አላዘጋጀላቸውም ፡፡ አብዛኞቹ ስደተኞች ሴቶችና ህጻናት ናቸው። ህብረተሰቡ ለዜጎቹ እገዛ በማደረግ ላይ ቢሆንም፣የአለማቀፍ ድርጅቶችም ሊጎበኙዋቸው እንደሚገባ ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል። በሌላ በኩል ግን በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ወደከፋ የረሃብ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያሰራጩት ወሬ ገንዘብ ለማግኛ እንጂ ትክክለኛ አይደለም በሚል ኮምሽነር ምትኩ ካሳ አስተባብለዋል፡፡ በቅርቡ በአዲስ መልክ የተቋቋመው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ማክሰኞ ዕለት የመንግስትን አንድ ኣመት የስራ ዕቅድ ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት ድርቁ ወደከፋ ደረጃ መሸጋገሩን የዓለም ምግብ ፕሮግራምን (ፋኦ) የመሳሰሉ ኣለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያሰራጩት ወሬ ዕርዳታ ለማሰባሰብ እንዲጠቅማቸው እንጂ እውነታው እነሱ እንደሚሉት አለመሆኑን እነሱም ያውቁታል በሚል አስተባብለዋል፡፡ በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንም ይህንኑ በማስተጋባት ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ችግሩ ከመንግስት አቅም በላይ አልሆነም በሚል በተናገሩበት በዚሁ መድረክ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመንግስት ይፋዊ የእርዳታ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ትልቁን ድርሻ ብቻውን እየተወጣ ያለው መንግስት ነው በማለት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ያስታወሱት ኮምሽነሩ፣ ድርቁን ለመከላከል ለቀጣይ አንድ ኣመት ብቻ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ወይንም 30 ቢሊየን ብር ገደማ እንደሚያስፈልግ ይፋ አድርገዋል፡፡ ከኣለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶችና መንግስታት የተገኘው ድጋፍ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ መንግስት በራሱ አቅም እስካሁን 300ሚሊየን ዶላር ገደማ ወጪ መድቦ ችግሩን ለመቋቋም እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ቀሪውን 1 ቢሊዮን 100 ሚሊዮን ዶላር ማን እንደሚሸፍነው ግን ያሉት ነገር የለም። ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች የተረጂውን ቁጥር ወደ 20 ሚሊየን የሚያደርሱት ሲሆን ችግሩን ለመቋቋም በመንግስት አቅም የሚደረገው ጥረት በቂ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ችግሩ በአጭር ጊዜ ሊባባስና ወደከፋ ቀውስ ሊሸጋገር እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል፡፡ መንግስት የረድኤት ድርጅቶቹን ማሳሰቢያ ተከትሎ አፋጣኝ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ችግሩን ወደመሸፋፈን ማድላቱ በራሱ ቀውሱን ያባብሳል በሚል እየተተቸ ነው፡፡ በሌላም በኩል ኦክስፋም እና ዩኒሴፍ በቅርቡ ባወጡት የጋራ መግለጫ ድርቁን ተከትሎ በሁሉም ክልሎች ያለዕድሜ ጋብቻ እየጨመረ መምጣቱን ይፋ አድርገዋል፡፡ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመታደግ ሲሉ ያለዕድሜያቸው ለመዳር እየተገደዱ መሆኑን እንዲሁም ሴቶችና ህጻናት ውሃ ፍለጋ ብዙ ርቀት ሲጉዋዙ ለጾታ ጥቃቶች እየተጋለጡ መሆኑን በቅርቡ ባካሄዱት ጥናት ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እንቢ ትበል!!! January 13, 2016


def-thumb
ሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ ከ150 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በአማራ፣ በጋምቤላና Aበሶማሌ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ በሌሎችም ክልሎች ወገኖቻችን እየተገደሉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ታስረዋል። የህወሓት አገዛዝ ዜጎች መግደል፣ መደብደብና ማሰር መደበኛ ሥራው አድርጎታል።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየቀጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት እና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሁላችንም ተሳትፎ የሚሻ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትናንሽ የገጠር ከተሞችን ሳይቀር ያዳረሰ መሆኑ የበርካታ ሕዝብ ስሜትንና ጥቅምን የሚነካ አጀንዳ በፍጥነት እንደሚሰራጭና ሕዝብን እንደሚያደራጅ አመላካች ነው። ከዚህ ሕዝባዊ ትግል በርካታ ድሎች የተገኙ ቢሆኑም ሁለቱ መሠረታዊ በመሆናቸው አጽንዖት ሊሰጣቸው ይገባል።

ኮለኔል ደረሰ ተክሌ “ሠራዊቱ ከሕዝቡ ጎን በመቆም ጠመንጃውን ወደ ዘረኛው አመራር ማዞር አለበት” አሉ | ሊደመጥ የሚገባ

ኮለኔል ደረሰ ተክሌ “ሠራዊቱ ከሕዝቡ ጎን በመቆም ጠመንጃውን ወደ ዘረኛው አመራር ማዞር አለበት” አሉ | ሊደመጥ የሚገባ

Wednesday, January 13, 2016

መምህር ግርማ ወንድሙ ከ76 ቀናት እስር በኋላ ተፈቱ – በ4 ክሶች 240 ሺህ ብር ዋስ አስይዘዋል

መምህር ግርማ ወንድሙ ከ76 ቀናት እስር በኋላ ተፈቱ – በ4 ክሶች 240 ሺህ ብር ዋስ አስይዘዋል

ድርቁ አስፈሪ ገጽታ እየያዘ መሆኑ ተጠቆመ

ድርቁ አስፈሪ ገጽታ እየያዘ መሆኑ ተጠቆመ
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ አስፈሪ ገጽታን እየያዘ መሆኑን ዓለም አቀፍ ለጋሾች እየገለጹ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትና ከአርባ በላይ ለጋሾች በተጣመሩበት የጋራ የሰብዓዊ የዕርዳታ ጥሪ፣ በአገሪቱ 10.2 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልገው አስታውቀው ነበር፡፡ ይህ በተገለጸ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በድርቁ አጠቃላይ ይዞታ ላይ የተናጠል ዳሰሳ እየሠሩ የሚገኙ ለጋሽ ድርጅቶች፣ ችግሩ አስፈሪ ገጽታን እየተላበሰ እንደሆነ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረቱን የኢትዮጵያ አሳሳቢ ድርቅ ላይ ማድረግ ባለመቻሉ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
አገሪቱ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት አይታው የማታውቅ የአየር ንብረት መዛባት ያመጣውን ድርቅ ለመቋቋም ለለጋሾች የ1.4 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥሪ ቢቀርብም፣ እስካሁን የተገኘው በጣም ትንሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የምግብ ችግር ስለሚያጋጥም ረሃብ እንዳይከሰት ፍራቻ አለ፡፡ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ ችግሩ እንዲሁ ከቀጠለ የአስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥርም ይጨምራል ተብሏል፡፡
የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ያነጋገሩዋቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢኮኖሚ ባለሙያ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ፣ ነገር ግን እስካሁን የራሳቸውን የምግብ ክምችት ሲጠቀሙ የነበሩ ዜጎች ጥሪታቸውን እያሟጠጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ከመጪዎቹ መጋቢት እስከ ሚያዝያ ባሉት ወራት የአስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት በበኩሉ በአሁኑ ወቅት ለ10.2 ሚሊዮን ተረጂዎች ያስፈልጋል የተባለው አንድ ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ቢሆንም፣ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት የሚያስፈልገው ስንዴ መጠን በእጥፍ እንደሚያድግ ትንበያ አቅርቧል፡፡
ዓለም አቀፍ ለጋሾች በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ቀውሶች መጠመዳቸው፣ ለኢትዮጵያ ድርቅ ትኩረት እንዳይሰጡ እንዳደረገም የኢኮኖሚ ባለሙያው ይገልጻሉ፡፡

Tuesday, January 12, 2016

ህወሃት/ኢህአዴግ የዘር-ፍጅት በመቀስቀስ ላይ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገለጹ

ህወሃት/ኢህአዴግ የዘር-ፍጅት በመቀስቀስ ላይ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገለጹ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008)
በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሁለት ወራት ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የዘር ፍጅት በመቀስቀስ የተቃውሞውን አቅጣጫ ለመቀየር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ታማኝ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። 
የዘር ፍጅት እቅዱ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች በተለይም በአማሮች ላይ የተነጣጠረና የተቀነባበረ ጥቃት በመሰንዘር፣ የሌላ አካባቢ ተወላጆች በስጋት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ በማድረግ ሁኔታውን ወደ እርስ-በእርስ ግጭት በመውሰድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። 
ወደ ኢትዮጵያ የሚሰራጩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) በኢትዮጵያ ስርጭታቸው መታወኩ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የታቀደውን ጥፋት በቀላሉ ለማስፈጸም ይቻላቸዋል የሚል ግንዛቤ መያዙንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያብራራል። 
በመንግስት የደህንነት ሃይሎች የተቀነባበረው ጥቃት፣ በህዝቦች መካከል ግጭት ከመጋበዝ ባሻገር፣ በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የተቀነባበሩ የቦንብ ፍንዳታዎች ጭምር ለማከናወን መታቀዱንና የቀደሙ ዕርምጃዎች የዚህ ውጤት መሆናቸው ተመልክቷል። 
ድርጊቱን ለማስፈጸም የተመለመሉ የኦህዴድና የብአዴን ሰዎች ጭምር መዘጋጀታቸውንም ለመረዳት ተችሏል። 
ለኢሳት መረጃውን ያደረሱት ወገኖች ህዝብን ለፍጅት ለመዳረግ በመንግስት የደህንነት ተቋም እየታቀደና እየተወሰደ ያለውን እርምጃ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በትኩረት እንዲከታተሉና መረጃውን በማድረስ እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢሳት የሳምንቱ እንግዳ- ጋዜጠኛና መምህር ሪዮት አለሙ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር

ኢሳት የሳምንቱ እንግዳ- ጋዜጠኛና መምህር ሪዮት አለሙ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር

የኢሳት ዜና

በሠርጉ ዕለት ዋዜማ ጭንቅላቱን በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ በመቱ ሆስፒታል ቆይቶ ለቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልኮ የሚረዳው አጥቷል። ጥቁር አንበሳ በበኩሉ ምንም እርዳታ ሳያደርግ ወደ አለርት ሆስፒታል ቢልከውም አለርት ሆስፒታል በተመሳሳይ መልሶ ወደ ጥቁር አንበሳ ልኮታል። ተገቢ ሕክምና የተነፈገው ፍጹም ደሙ በየዕለቱ እየቀነሰ ከመምጣቱ የተነሳ በሞት አፋፍ ላይ ነው።
*በአርባምንጭ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ ሁለት ወጣቶች በፌደራል ተይዘው እርቃናቸውን ተደርገው ወደ ማዕከላዊ ተወስደዋል። እነዚህ ወጣቶች ከዚህ በፊት ተይዘው የግንቦት 7 አባል ነኝ ብላችሁ እመኑ ተብለው ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። በርካታ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ። ከወር በፊት ተመሳሳይ እስር ሲፈጸም የ70 ዓመት እናት ታስረው እንደነበር ይታወሳል
ኢሳት ሬዲዮን ያድምጡ !

Monday, January 11, 2016

ወደ የመን በጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ 122 የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጡ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መነሻቸውን በሶማሌላንድ ሳናጋ ግዛት አድርገው በተጨናነቀ ጀልባ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ባሕር አቆራርጠው ወደ የመንና የገልፍ አገራት ለመግባት ሲጓዙ ከነበሩት ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን ዜጎች ውስጥ አብዛኞቹ መሞታቸውንና ከሟቾቹ ውስጥ 122 የሚሆኑት አስከሬናቸው በባህር ዳርቻዎች መገኘቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ከአደጋው ሕይወታቸው የተረፈ 80 ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውንና በድንበር ጠባቂዎች መያዛቸውን ዘገባው ገልፆ ፣ ከተያዙት ውስጥ አብዛኞቹ በምግብ እጦትና በውሃ ጥም ድርቀት ሳቢያ አሳሳቢ የጤና እክሎች ያሉባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በበርበራ የወደብ ዳርቻ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑም ሆርስ ሚዲያ አክሎ ዘግቧል።
የሳናጋ ግዛት አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አህመድ አብዲ ፋላይ ሶስት በአካባቢው ተራራ ጥግ ተደብቀው የነበሩ ጀልባዎች መያዛቸውን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በአራቱም የዓለም ማእዘናት መፍለሳቸውን አላቋረጡም። ገዥው መንግስት Aኤኮኖሚያዊ ለውጥ አምጥቻለው እያለ ሌት ከቀን ቢናገርም፣ ዜጎችን ከሶማሊያና በጦርነት ከምትታመሰው የመን ስደት እንኳን ያልታደገ ለውጥ መሆኑ የሚያሳየው ወጣቶች ምን ያህል በአገራቸው ተስፋ ማጣታቸውን አመላካች መሆኑን እንደሚያሳይ ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራል

“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራል

“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራል



“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ 

 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49886

“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራ